Monday, 18 September 2017
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ( ክፍል አስራ ስድስት ) ቊጥር ፪ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ( ክፍል አስራ ስድስት ) ቊጥር ፪ የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው በሚለው በክፍል አስራ ስድስትና በቊጥር ፪ ትምህርታችን ላይ ዛሬም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነበትን ብዙ የሆኑ የመጽሐፍቅዱስ አስረጂ ጥቅሶችን አቅርቤያለሁ ነገር ግን ከዚህ የቊጥር ፪ ትምህርት ውስጥ ዋና ክፍል ነው ብዬ የጠቀስኩትን ሃሳብ በጥቂቱ ላቀርብላችሁ እወዳለሁ እናንተ ግን ሙሉውን የቪዲዮ መልዕክት ልትከታተሉ ትችላላችሁ ይሄ ዋና ሃሳብ የተባለው ግን አባት እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የልጅነት እውቅናን የሰጠበት እውነት ነው እርሱን ነው ላብራራው የፈለኩት ታድያ ይህ አባት እግዚአብሔር ለጌታችን ኢየሱስ የልጅነት እውቅናን የሰጠው መጽሐፉ በሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 33 ላይ እንደሚነግረን ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ ተብሎ እንደተጻፈ ኢየሱስን አስነስቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና ስለሚለን የኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የተረጋገጠው ኢየሱስ በሥጋ በተገለጠበት ጊዜና ሕጻን ሆኖም ሳለ በእናቱ እቅፍ ውስጥ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሔር አብም በሰማይ ሆኖ ለኢየሱስ ምስክርነት በሰጠበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን የሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 33 መጽሐፍ በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ ብሎ በጠቀሰልን በመዝሙር 2 ፥ 7 እና 8 በግዕዙ ቃል እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ ሰአል እምኔየ እሁበከ አሕዛበ ለርስትከ ይለናልና ወደ አማርኛው ስተረጉመው እግዚአብሔር አለኝ ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ ይለናልና ኢየሱስ በቅድምና የእኛን ሥጋ ለብሶ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ከመሆኑ በፊት በዚሁ በተጠቀሰልን በመዝሙሩ ቃል መሠረት ይሄው ኢየሱስ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ ነው የዕብራውያን መጽሐፍም ይህንን ሃሳብ ሲያጠናክረው ከመላዕክትስ ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ደግሞም እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው ? በማለት የኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነቱ የብቻው መሆኑን በሚገርም ሁኔታ ገለጸልን ዕብራውያን 1 ፥ 5 ለዚህም ነው ዮሐንስ በወንጌሉ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ያለን ዮሐንስ ወንጌል 3 ፥ 16 ን እንመልከት በመሆኑም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር አብ አንድያ የባሕርይ ልጁ ነው ክብር ለእርሱ ይሁንለት እንደገናም ኢየሱስ ክርስቶስ በዘላለማዊ ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ ነው እንዴት ? ስንል በዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 18 ላይ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው ይለናልና ስለዚህ ኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም በሥጋ ተወልዶ በቤተልሔም በግርግም ውስጥ በእናቱ እቅፍ ውስጥ እንደነበረ ሁሉ በቅድምናም በማይታየው በባሕርይ አባቱ በእግዚአብሔር እቅፍ ውስጥም የነበረ መሆኑን መጽሐፉ በሚገባ አብራርቶልናል ለዚህም ነው ያላየነውንና ልናየውም የማንችለውን እግዚአብሔርን በአባቱ እቅፍ ያለው አንድ ልጁ እርሱ ተረከው የሚለውን የቃሉን እውነት ያነበብነው በመሆኑም ይህንን መሠረት አድርጋ ጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በ፫፻፲ወ፰ቱ ርቱዓነ ሃይማኖት በተወሰነ የኒቅያ ጉባኤ ጸሎተ ሃይማኖት በተሰኘው የእምነት መግለጫዋ ላይ ወነአምን በአሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ዋሕድ ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ብርሃን ዘእምብርሃን አምላክ ዘእም አምላክ ዘበአማን ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ያለችው ወደ አማርኛው ስተረጉመው ዓለም ሳይፈጠር የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን እርሱም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የሚሆን የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሆነ በማለት ይህንኑ የእምነት መግለጫዋን መሠረት አድርጋ ነገረችን « ድንቅና ይበል የሚያሰኝ የእምነት መግለጫ ነው !! » ታድያ ሌላ ነገር ሳንጨምርና ሳንቀንስ ይህንኑ የእምነት መግለጫ ብቻ ለእምነታችን መቆም ብንማር ዛሬ ሕዝባችን የት በደረሰ ታድያ ምን ያደርጋል አሁን ግን ሕዝባችን እንዲህ አይደለም እና ያለው እጅግ በጣም ያሳዝናል ልብንም ይሰብራል ወደ ትምህርቱም ስመለስ ከቃሉ ጋር በተገናዘበ መልኩ ይኸው የኦርቶዶክሱ የእምነት መግለጫው እንዳለን ኢየሱስ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ሆኖ ሳለ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ነው የምናነበውን ቃል እግዚአብሔር ይባርክልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment