Monday, 31 July 2017
የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ሰባት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ሰባት ) የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሰባት ትምህርቴ ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ አማላጅነት ዙርያ እንደተለመደው የተሳሳቱ ሰዎች የተሳሳተ ማብራርያ እንዲህ ሲሉ ሰጥተዋል ምልጃ የፍጡር ሥራ ነው ሊያውም የጻድቃን ፣ የሰማዕታትና የመላዕክት ሥራ ነው እንጂ የክርስቶስ ሥራ አይደለም ክርስቶስ የጸለየው ፣ የሰገደው ለእኛ አብነት ሊሆነን ነው በአጠቃላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ያደረጋቸው ሥራዎች ወይንም የፈጸማቸው ተግባሮች ሁሉ ለአብነት ፣ ለአርአያ ያደረጋቸው ናቸው ክርስቶስ ለእኛ ሲል በለበሰው ሥጋ የተቀበለው መከራ እንዳልተሰማው ያሳያል ነገር ግን አማላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ? ሲል የጸለየው ጸሎት በለበሰው ሥጋ ሥቃይ ተሰምቶት ሳይሆን መከራ በደረሰባችሁ ጊዜ እናንተም እንደዚሁ ጸልዩ ለማለት የተደረገ ምሳሌ እንደሆነ ያመለክታል ሲሉ አስተምረዋል ይህ ነው እንግዲህ አውጣኪነት በፍጹም ሰውነቱ የሰራቸውን የአስታራቂነት ሥራዎች ለአርአያነት ብቻ የተደረጉ አስመስሎ ማለፍ የሰው ልጆችን ደኅንነት ከንቱ ያደርጋል በእርግጥም ከተፈጸሙት የደኅንነት ሥራዎችና የምልጃ ተግባሮች ጀርባ አርአያነታቸውም ጎልቶ ታይቷል እውነቱ ይሄ ሆኖ ሳለ ታድያ ሰዎቹ አሁንም የተሳሳተ መረዳታቸውን ቀጥለውበት ጌታችን በዲያብሎስ የተፈተነው ዲያብሎስ ከአጠገቡ የሚደርስ ሆኖ አይደለም ለአርአያነት ወይንም ለምሳሌነት ብቻ ሳይሆን ለአብነትም ጭምር ያደረገው ነው ፤ የጸለየውም የሚጎድለው ነገር ኖሮት ለማሟላት ሳይሆን ለአርአያነት እንደሆነ እናምናለን በአጠቃላይ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት የዘጋውን ገነት ለመክፈት ጸሎት ልመና ያላስፈለገውን ጌታ ፈያታዊ ዘየማን ከአዳም አስቀድሞ ገነት እንዲገባ የፈቀደ አምላክ እንዴት ዝቅ ያለ ሥራ ሠራ ለማለት ተሞከረ እንደገናም አምላክ ሰው ሆነ ማለት ፍጡር የነበረውን ሥጋ ተዋሃደ እንላለን እንጂ ፍጹም ሰው ሆነ አንለውም የሚሉትንና ሌሎችንም ሃሳቦች እነዚሁ ሰዎች ሰንዝረዋል እነዚህን ሃሳቦች በትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል በመመዘን ምልጃው አስታራቂነቱና ፍጹም ሰው መሆኑ እንዴት እንደሆነ ቅድሚያውን ወስደን ከመጽሐፍቅዱሳችን ፣ አያይዘንም የአባቶች መጽሐፍ ከሆኑት ሃይማኖተ አበው ፣ ቅዳሴ ፣ ሰዓታትና ጾመ ድጓ ከተባሉት ኦርቶዶክስ ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት ውስጥ እነዚሁ ሃሳቦች ማለትም ምልጃው አስታራቂነቱና ፍጹም ሰው መሆኑ እንዴት እንደሆነ እንደ ቃሉ እውነት ተጽፈውና ሰፍረው የተገኙ በመሆናቸው ከቃሉ ጋር በማመሳከርና ትክክለኛውን መልስ በመስጠት እንደሚከተለው በዚሁ ቪዲዮ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ ታድያ ይህንን ትምህርት በመስማት በዚሁ ትምህርት እንደምትባረኩ አምናለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርከው ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment