Friday, 28 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ስድስት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ስድስት ) በክፍል ስድስት ትምህርታችን በተደጋጋሚ በአንጋፋዋና ሐዋርያዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተክርስቲያኒቱ ተገፍተው በወጡ አገልጋዮች በሚሰጠው የኢየሱስ የአማላጅነት ትምህርት ተጽዕኖ ሥር የወደቁ አንዳንድ ሰዎች ከመጽሐፍቅዱሱም ሆነ በመደበኛነት በግዕዙ ካለ ቃልና የአባቶች ትምህርት ነጻ የሆኑ ሰዎች በመሆናቸው እንዲሁ ተጠቅቼ ፣ መልስም አጥቼ ፣ ባዶ የቀረውን እጄን ከምሰጥ ሲሉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ብቻ ተይዘውና ተውተርትረው ለወረወሩት የፈሪ ዱላ የተሰጠ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስ ነው እንደገናም ቤተክርስቲያኒቱ የመጽሐፍቅዱሱን እውነተኛ አስተምህሮ ለመቀበሏ ማረጋጋጫ የሚሆን እንደ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍና ከመሣሠሉት መጽሐፎች ተጠንቶ በማስረጃነት የቀረበ በመሆኑ ከትምህርቱ ጋር በተያያዥነት ቀርቧል ይሄ ትምህርት ታድያ እንዲህ ላሉ ሰዎች ትክክለኛውን ምላሽ ከትክክለኛው ማብራርያ ጋራ የሰጠ ቢሆንም ከዚህም ባሻገር ቤተክርስቲያኒቱ የዛሬን አያድርገውና ከዚህ በፊት በነበረው መረዳቷ ትክክለኛ መሠረት ላይ እንዳለች ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ማብራርያ ሰጪና ጠቋሚ የሆነ ትምህርትም ነው የተወደዳችሁ ወገኖቼ የክርስቶስ ኢየሱስ የአማላጅነቱን ትምህርት ዛሬ ላይ ላቅርበው እንጂ ማንኛውም በልዩ ልዩ ርዕስ የቀረበ መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርት ሁሉ በትክክለኛው መንገድ በሚሰጥበት ጊዜ ሁልጊዜም ተጽዕኖ አለው ተጽዕኖም ፈጣሪ ነው ይህንን ከመጽሐፍቅዱስ በብዙ ሥፍራዎች ላይ ልንመለከት እንችላለን በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን ? እነሆም ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል ፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ? ብለው የጠየቁ በተጽዕኖ ሥር የወደቁ ሰዎች ናቸው በሌላም ክፍል ላይ ሄደን ስንመለከት በጌታ ዘመንና በጌታም የወንጌል ትምህርት ጊዜ የነበሩ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፦ አንድ ስንኳ ልታደርጉ እንዳይቻላችሁ ታያላችሁን ? እነሆ፥ ዓለሙ በኋላው ተከትሎት ሄዶአል ተባባሉ ይለናል የሐዋርያት ሥራ 5 ፥ 28 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 12 ፥ 19 ን እንመልከት ታድያ እነዚህንና የመሣሠሉት በዘመኑ የነበሩ የሕግ መምህራን ሮሮዎችና ጩኸቶች ሁሉ ከእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ጫና የተነሣ የመጡ የምሬት ድምጾች ናቸው ይህንን ተጽዕኖ ለመከላከለም ሆነ ለመቋቋም አቅም ያጡ ሰዎች ያስተጋቡት የፍርሃት ድምጽ ፤ ታድያ ይሄ ድምጽ በየዘመናቱ እነዚህን ዓይነት በመሠሉ ሰዎች ሲስተጋባ ታይቷል ዛሬም ድረስ በተመሣሣይ መልኩ በመስተጋባት ላይ ይገኛል ይህ እንግዲህ የሚያሳየን ወገኖቼ የወንጌሉ ሬሾ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ከፍ እያለ እያደገም መምጣቱን ነው ስለዚህ እኛ እውነተኞቹ የወንጌል አገልጋዮችም ስለሆነው ነገር በብዙ ደስ ሊለንና ጌታንም ልናመሰግን ይገባል ስል ለእግዚአብሔር ባሮች ፣ የመከሩም ሥራ ተሳታፊዎች ሁሉ መልእክቴን ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ ከዚህም ሌላ ሥራችንንም ከዛሬ ይልቅ ነገ በተቀላጠፈ ሁኔታ በከፍተኛም የእግዚአብሔር ብርታትና ኃይል በመንፈስቅዱስም ጉልበት መቀጠል እንዳለብን ይሰማኛል የዚሁ ቀጣይ የክፍል ሰባት ትምህርት በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ይቀርብላችኋል እስከዚያው ተባረኩ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment