የግጥም መነባንብ
የግጥሙ ርዕስ ፦ መብራቱ አይጠፋም
የግጥም መነባንብ
የግጥሙ ርዕስ ፦ መብራቱ አይጠፋም
የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ነገ ማለዳ በካናዳ ኦታዋ የሰዓት አቆጣጠር 10 ሰዓት 10:00 In the morning ላይ የሚጀምር እግዚአብሔርን መከተል በሚል ርዕስ 15ኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ላይ ደርሰናልና ይህንን ትምህርት ይዤላችሁ በሰዓቴ እቀርባለሁ አምናለሁ ጌታ መንፈስቅዱስ ጥሩ ጊዜ ሰጥቶን በቃሉ ይገነባናል ትምህርቱ በፌስቡክ ላይቭ ነውና የሚተላለፈው ሳያመልጣችሁ በመስመሩ ላይ ገብታችሁ እንድትከታተሉ ላበረታታችሁ በጌታ ፍቅር እወዳለሁ ተባረኩልኝ ደግሞም በጌታ ወገኖቼ የሆናችሁትን የፕሮግራሜ ታዳሚዎችና ተከታታዮች ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ ፣ አከብራችኋለሁ ደግሞም እጸልይላችኋለሁ እናንተም ለዚህ አገልግሎት ጸልዩ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከዚህ በመቀጠል ግን ለነገው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንደ መሰናዶ ወይንም እንደ ማነቃቂያ የምትሆን እኔ ጋር ምሽት ስለሆነ ከሽ ከሽ የምታረጓትንና የምታጣጥሟትን እንደ እስናክ የእራት መክሰስ ዓይነት የሆነች አጠር ብላ እየጣፈጠች ወደ ውስጥ የምትገባ ግጥም እነሆ ብያለሁ አንብቧት ፦_________________
የግጥሙ ርዕስ መብራቱ አይጠፋም የሚል ነው
መብራቱ አይጠፋም
ይለኮሳል እንጂ መብራቱ አይጠፋም
የሚቀሰቀሰው ሳሙኤል አልተኛም
የነኤሊ ዓይኖች ማየት ሲሳናቸው
በኃጢአት በድካም የፈዘዙ ሆነው
አጥርቶ የሚያይን ጌታ ያዘጋጃል
መቅደስ የተኛውን ሳሙኤልን አይቷል
ብርቅ የሆነውም ቃል ያ የእግዚአብሔሩ
ሊገለጥ ሊነገር በሀገር በምድሩ
ጊዜው ደረሰና ሳሙኤል ተጠርቶ
እነሆኝ እያለ ከተኛበት ነቅቶ
ቃሉ በቤርሳቤህ በዳን ሲደርስለት
ሳሙኤል ሆይ አንተ ነቢይ ነህ አሉት
አውቀውት አምነውት ተስማምተውም ጠሩት
ከስማችን በፊት መልዕክቱ ሲደርስ
የተላከ ሆኖ በመንፈስቅዱስ
ተብለን ልንጠራ ለሰዎች ሳይቸግር
ሐዋርያ ነቢይ መጋቢ አምባሳደር
ሊጠሩን ሲነሱ በሙሉ አፋቸው
ያለማስታወቅያ ፈቃደኛ ሆነው
ጸጋችን ተገልጦ ለሰው የሚታየው
ያን ጊዜ ጌታችን ከፍ ብሎ ይከብራል
ምስጋናን ሊቀበል በምድር ይነግሣል
ከዕንቅብ በታች ሆኖ የጋን ውስጥ መብራት
መሆን ይቀርና ለሰው የሚያታክት
አይቀር ተደብቆ ሆኖ በልባችን
የዓለም መድኃኒት የዓለም ብርሃን
ይበራል ይደምቃል የጌታችን መብራት
በእኛ ላይ ሲመጣ የመንፈሱ እሳት
ይበራል ይደምቃል የጌታችን መብራት
በእኛ ላይ ሲመጣ የመንፈሱ እሳት
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment