Tuesday, 14 February 2017
የመልዕክት ርዕስ ፦ በባሰው ነገር ላይ ብሶ መገለጥ ( የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 13 _ 31የመልዕክት ርዕስ ፦ በባሰው ነገር ላይ ብሶ መገለጥ የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 13 _ 31 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው መልዕክቴ በባሰው ነገር ላይ ብሶ መገለጥ የሚል ነው በዚህ የመልዕክት ርዕስ መሠረት የባሰው ነገር ምንድነው ? ብሰንስ የምንገለጠው በምን በምን ጉዳዮች ላይ ነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን እናነሳ ይሆናል ለዚህ መልዕክት የምንመለከተው የመጽሐፍቅዱስ ክፍል የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 13 _ 31 ነው በክርስትናችን ወደፊት ሄደን ፣ የጌታንም ሥራ ሰርተን ፣ በጌታ ፊት እንዳንሸለም የሚከለክሉ ብዙ የከፉና በክፋትም እየባሱ የመጡ ነገሮች በሐዋርያት ዘመን ነበሩ ፣ በእኛም ዘመን አሉ ፣ ከእኛም ዘመን በኋላ ባለ ዘመን ሁሉ እነዚህ ነገሮች ይኖራሉ በዚህ የመጽሐፍቅዱስ ክፍል ይህ የመፈወስ ምልክት የተደረገለት ሰው ከአርባ ዓመት ይበልጠው ነበር ይለናል ማለትም በዚህ ተአምር የተፈወሰውም ሰው ዕድሜው ከአርባ ዓመት በላይ ነው ማለትን የሚያመለክት ነው እስከዚህ ዓመቱ ድረስ ግን ሽባ ሆኖ በሚያሳዝን ሁኔታ የኖረ ነው እነዚህ ሐዋርያት ታድያ በጌታ በኢየሱስ ስም ከፈወሱት በኋላ ከሰው ጋራ የተቀላቀለ ሰው ነበር መጽሐፉም እንዲህ ሲል የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ በማለት ይነግረናል የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 14 ታድያ ይህንን በጌታ በኢየሱስ ስም የተደረገውን የተገለጠና እነርሱም ሳይቀር ሊደብቁት ያልቻሉትን እውነት ነው እንግዲህ እንደገና እነዚህ አይሁድ በሐሰት ቀምመው ለመሸፋፈን ሲሉ በእነዚህ ሐዋርያቱ ላይ የዛቻ ቃልና የማስጠንቀቅያ ናዳ ያወረዱባቸው ይሁን እንጂ የዚህ ሰው ፈውስ ያልተደበቀ በመሆኑ ሰዎች ሁሉ ስለሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር ይለናል እንደገናም እነዚሁ ሐዋርያት ተፈተው ወደ ወገኖቻቸው ከተቀላቀሉ በኋላ አብረው በጸለዩ ጊዜ ተሰብስበው የነበሩበትን ሥፍራ መንፈስቅዱስ አናወጠው ወጥተውም የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥነት ተናገሩ ይለናል በባሰ ነገር ላይ ብሶ መገለጥ ማለት እንግዲህ ይሄ ነው እነዚህ ሐዋርያት በባሰውና በከፋው በአይሁድ ተንኮል ላይ የእግዚአብሔርን ቃል ገልጦ በመናገር ብሰው ተገለጡ በየዘመናቱ ያለ ክፋትና ተንኮል የእግዚአብሔርን የተገለጠ ተአምራታዊ ሥራውንም ሆነ የቃሉን እውነት ደብቆ መያዝ አይችልም ቃሉ በግልጥነት እንደ ወትሮው ይነገራል ፣ ይሰበካል ፣ ሕሙማን ይፈወሳሉ ፣ አጋንንቶች ይወጣሉ ብዙ የሆነው ተአምራታዊ ኃይሉም ያለመያዝ ይለቀቃል በዚህ ትምህርት ውስጥ የኤልዛቤል የባሰው ክፋትዋ ፣ የሐማ በመርዶክዮስና በአይሁድ ሕዝብ ላይ ያሳየው የበዛ ክፋትና የእግዚአብሔር የበቀል እርምጃ ምን እንደሚመስል በሰፊው ተገልጧል በተለይም የሐማ የበዛው ክፋቱ በውርደት የተለወጠው ንግሥት አስቴር ለግብዣ ንጉሥ አርጤክሲስንና ሐማን በጠራችበት ጊዜ ነው ሕይወቴ በልመናዬ ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል ለመደምሰስም ተሸጠናልና ብላ ለንጉሥ አርጤክሲስ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት ንጉሡም አስቴርን ይህን ያደርግ ዘንድ በልቡ የደፈረ ማነው ? እርሱስ ወዴት ነው ? ብሎ ተናገራት አስቴርም " ያ ጠላትና ባለጋራ ሰው ክፉው ሐማ ነው አለች " ይለናል በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ሐማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት ደነገጠ የሚለን ከዚያ በኋላም ሐማ አቅል ያጣና ቀልቡ የተገፈፈም ሰው በመሆኑ ክብሩ እየወረደና እያሽቆለቆለ መጣ ይህ ብቻ አደለም ከዚህ ውርደቱም ለመውጣት ሲል ከንግሥቲቱ አስቴር ሕይወቱን ይለምን ዘንድ በጀመረ ጊዜ ከቤቱ የአትክልት ሥፍራ የተመለሰው ንጉሥ የሐማን አስቴር ባለችበት አልጋ ላይ ወድቆ የሚያደርገውን ነገር አይቶ ሊታገሰው ባለመቻሉ በቤቴ በእኔ ፊት ንግሥቲቱን ይጋፋታልን ? አለ ታድያ ሐማ ራሱ በጠመጠመውና ባጣመመው ነገር እርሱም እጅግ የተወሳሰበ ፣ የተጠመጠመና የተጣመመ ነገር ውስጥ ገብቷልና ንጉሡም ሊረዳው አልቻለም በመሆኑም በእንዲህ መልኩ ከንጉሡ አፍ የወጣው ቃል የሐማን ፊት ሸፈኑት ይለናል ከዚህ የተነሳም ነው ሳይቸግረው በመርዶክዮስ ላይ ነገሩን እያባሰው የመጣው ሐማ በሕይወቱም ሆነ በሥልጣኑ እንደገናም በብዙ ልመናውም ጭምር ሊመልሰው ወደ ማይችለው የከፋ ነገር ውስጥ የገባው ታድያ ከነዚህ ሁኔታዎች የተነሣ ሐማንም ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሰቀሉት የንጉሡም ቁጣ በረደ የሚል ቃል ተጽፎልን እናገኛለን መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ 7 ን በሙሉ ተመልከቱት ወገኖቼ በሕይወታችን የሚመጡ አንዳንድ ነገሮች የሚሆኑት እንደዚህ ነው ልንመልሳቸው ፣ ማጣፍያና መቋጫም ልናበጅላቸው ይቸግሩናል ፣ ያቅቱናል በዚህም ምክንያት እነዚህ አሳፋሪ ሁኔታዎቻችን ሥር ሳይሰዱ በጊዜ ዕልባት ያልሰጠንባቸው ጉዳዮች በመሆናቸው ሕይወታችንን ወደሞት ጎዳና እያጣደፉ በብዙ ይዘዉት ይነጉዳሉ ከዚህም ነገር ሊያስጥለን የሚችልም ሆነ የሚያወጣን ማንም የለም ቅዱሳን ወገኖች በቪዲዮ የተለቀቀው መልዕክት እንግዲህ የሚጠቁመንም ሆነ የሚያስተምረን ይህንን ነው ሳያመልጣችሁ የቪዲዮውን መልዕክት እንደሚገባ ተከታተሉ ተባረኩበት ተጠቀሙ ብትችሉ ደግሞ መልዕክቱን ለሌሎች ሰዎች ሼር አድርጉት በጌታ ፍቅር እወዳችኋለሁ አከብራችኋለሁ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ተባረኩ ሰላም ሁኑ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ )
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment