Tuesday, 8 November 2016
እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን ( ክፍል አንድ )እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ክፍል አንድ ኢንተገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ትርጉም፦ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን ( ምንጭ አመክንዮ ዘሐዋርያት ወዘሠለስቱ ምዕት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የእምነት መግለጫ ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ምዕመናን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናት አረጋውያን አባቶችና እናቶች እንዲሁም እህቶቼና ወንድሞቼ በሙሉ እንደምን ሰንብታችኋል ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ እንደሚታወቀው የፊት መጨማደድ የሌለባትን እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል እውቀት በክርስቶስም ትምህርት ለራሱ ለሙሽራው ለክርስቶስ የሚያዘጋጅና የሚያቀርብ ቢሆንም በዚያው መጠን ደግሞ ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊቷን ቤተክርስቲያን ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ ወንጌል እንድትመለስ የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማርና በመስበክ የሚያገለግል ነው ከላይ በትምህርት ርዕሴ ላይ እንዳሰፈርኩላችሁ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን የሚል ቃል በእምነት መግለጫዋ ላይ ተጽፎአል በመሆኑም ዛሬ ለእናንተ ለወገኖቼ ይህንን ሃሳብ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማስተያየት ትክክለኛውን እውነት ለማስጨበጥና ግንዛቤም ለመስጠት ይህንን ትምህርት ይዤ ወደ እናንተ ቀርቤያለሁ ይህቺ ቤተክርስቲያን በእምነት መግለጫዋ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ስትል አይሁድን ማንሳት የፈለገችበትን ምክንያት ትምህርቱ በስፋት ይተነትናል ከዚህም ሌላ ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ መጽሐፉ በምዕራፍ 5 ቊጥር 2 ላይ ናሁ አነ ጳውሎስ እብለክሙ እምከመ ትትገዘሩ በኀበ ክርስቶስ ኢይበቊዐክሙ ምንተኒ ብሏል ወደ አማርኛው ስተረጉመው እነሆ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም አለ ይለናል ታድያ ጳውሎስ ለምን ይህን ተናገረ ? ስንል አሁን ማዳን የግዝረት ሳይሆን የእግዚአብሔር ስለሆነ የአምላካችን ማዳንና ኃይል የክርስቶስም ሥልጣን ሆኗል እንደገናም በቀንና በሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሰን የወንድሞች ከሳሽ ተጥሎአል ተብሎ የተጻፈልን ነውና የወንድሞች ከሳሽ የተጣለው በግዝረት ሳይሆን በበጉ ደም ነው ስለዚህም እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት ነፍሳቸውንም እስከሞት ድረስ አልወደዱም ይለናል ራዕይ 12 ፥ 7 _ 13 በመሆኑም ይሄ ትምህርት በአሁኑ ሰዓት የሚረዳው በዚሁ ቃል መሠረት ሐዋርያዊት የሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በእምነት መግለጫዋ ላይ እንዳስተላለፈችው እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን ብላለችና እኛም እንደ አይሁድ አንገረዝም ስንል ከመገረዝ ሠፈር ወጥተን በአጠቃላይ ማዳንን ወደ ሰጠን ወደ በጉ ደም በመምጣት መዳናችንን አሁኑኑ ለማረጋገጥ እንድንችል የቀረበ ትምህርት በመሆኑ ይህንን የቃል እውነት አምነን እንድንቀበል ኢየሱስንም ከግዝረትና ከሌሎችም ሥርዓቶች ጋር ሳንቀላቅለው ብቸኛ የሕይወታችን አዳኝና ጌታ አድርገን በመወሰን ዛሬውኑ ወደሕይወታችን እንድንጋብዘው ፣ የእርሱና የእርሱም ብቻ ሆነን እንድንድን ለማድረግ ነው መዳን በኢየሱስ ብቻ ስለሆነ የመዳን ቀን አሁን ነው የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 2 ነው ትምህርቱ በዚህ ሳያበቃ በክፍል ሁለት ቀጥሎ ግዝረት ማለት ምን ማለት እንደሆነና ግዝረት የሚከተሉትን ሦስት ነገሮች እንደሚያመለክት በትንታኔ ያቀርባል ስለዚህ ይህ ትምህርት ሳያመልጣችሁ እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ከተከታተላችሁ በኋላ ደግሞ ለሌሎች ሰዎች ሼር በማድረግ ተባበሩ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment