Saturday, 5 November 2016

2ኛ ) የፈሪሳውያን ዝምታን መምረጥ ( ዝምታ ) የማርቆስ ወንጌል 3 ፥ 1 _ 6 ፤ የሉቃስ ወንጌል 14 ፥ 1 _ 6የትምህርቱ ዋና አርዕስት ፦ የቅን ፍርድ መታጣት ምክንያቶችና ውጤቶቹ የትምህርት መነሻ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ዮሐንስ ወንጌል 5 ፥ 15 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 7 ፥ 24 ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ዛሬ ለእናንተ ለወገኖች የቅን ፍርድ መታጣት ምክንያቶችና ውጤቶቹ በሚለው ዋና አርዕስት ዙርያ በተለያዩ ንኡሳን አርዕስቶች የሚቀርቡ የቪዲዮ መልዕክቶችና ትምህርቶችን ወደ እናንተ ይዤ ቀርቤያለሁ የሚለቀቁትን ትምህርቶች እንደሚገባ መከታተል እንድትችሉ ጥቂት ማብራርያዎችን ለእናንተ ለአድማጮች መስጠት እፈልጋለሁ የተነሳሁበት የምንባብ ክፍሎች እንደሚያሳዩት 38 ዓመት የአልጋ ቁራኛ የነበረውን ሰው ኢየሱስ በሰንበት ፈወሰው ሰውየውም ያዳነው ኢየሱስ እንደሆነ ለአይሁድ ነገረ ስለዚህም በሰንበት ይህንን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር ይለናል ታድያ ኢየሱስን ለመግደልም ሆነ ለማሳደድ መነሻ ያደረጉት የኢየሱስ ይህንን ሰው መፈወስ ሳይሆን በሰንበት ቀን መፈወሱን ምክንያት አድርገው ሰንበትን ሻረ በሚል ሃሳብ ተነስተው ነው ኢየሱስ ይህንን ሰው ፈወሰ ብለው ቢቃወሙ እንዴት ታድያ የሰዎችን መፈወስ ትጠላላችሁ ትቃወማላችሁ ?ተብለው ሕዝብ ሊነሳባቸው ነው ስለዚህ በዚህ መንገድ የኢየሱስን አገልግሎት ቢቃወሙ የማያዛልቃቸው እንደሆነ ስለተገነዘቡ ሰንበታችንን በመሻር በሰንበት ፈወሰ ሲሉ ኢየሱስን ለማሳደድና ለመግደል ይፈልጉት ጀመር ዋናው ተቃውሞአቸው ግን ሰንበታቸው በሰዎች መፈወስ ምክንያት ስለተሻረ ፣ ኢየሱስም ሰዎችን በሰንበት ስለፈወሰ የሰንበት መሻር ጉዳይ ግድ ብሎአቸውና አስጨንቋቸው ሳይሆን የኢየሱስን አገልግሎት ስላልተቀበሉ በኢየሱስም የፈውስ አገልግሎት ስለቀኑ ከቅንዓትና ከምቀኝነት በመነሳት ነው ኢየሱስማ በሰንበት ፈወስክ ለሚለው ጥያቄያቸው ከእናንተ በሬው በጉድጓድ ቢገባበት የማያወጣው ማነው ? መልሱልኝ ሲል በጥያቄ አሳፍሯቸዋል ምክንያቱም በሬም ሆነ አህያ በሰንበት ጉድጓድ ቢገባባቸው ያወጡታልና ነው ከዚህም ሌላ እነርሱ በሰንበት ሰውን እንደሚገርዙ ከጠቆማቸው በኋላ የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሕጻን በሰንበት የሚገረዝ ከሆነ የሰውን ሁለንተና በሰንበት ስለፈወስሁ ለምን በእኔ ላይ ትቆጣላችሁ ? የሰውን ፊት በማየት መፍረድ ትታችሁ ቅን ፍርድ ፍረዱ ይላቸዋል ይህንን አባባል በመደበኛው መጽሐፍቅዱስ ስንመለከተው ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ ማለቱን ያመለክታል በመሆኑም እንግዲህ ቅን ፍርድ ሲጠፋ ብዙ የሚሰጥ ምክንያት አለ ለምን ስንል ሰዎች በቀላሉ ይህንን ቅን ፍርድ ማጥፋት ስለማይችሉ ስለዚህ ሰዎች ይህንን ቅን ፍርድ ለማጥፋት ሲሉ ብዙ ብዙ ምክንያቶችን ይዘው ይቀርባሉ ምክንያቶቹ ደግሞ ውጤቶችን ይዘው የሚመጡ ስለሆኑ ኢየሱስን ማሳደዱና ለመግደል መፈለጉ ከነዚህ ሁኔታዎች የተነሳ ነው ይለናል ትምህርቱ እንደገናም በዚህ ውስጥ ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለመግደል አመቺ ጊዜን ከመፈለግ አኳያ ኢየሱስ ለጠየቃቸው ትክክለኛ ጥያቄ ቅን እውነተኛና ተገቢ የሆነውን መልስ ላለመስጠት ዝም ያሉበት ጊዜ እንደነበር ትምህርቱ ያብራራልናል ኢየሱስም እስከ ግድያ ያደረሳቸውን ተቃውሞና ማሳደድ በመመልከት አባቴ እስከ ዛሬ ይሰራል እኔም እሰራለሁ አለ ፣ አገልግሎቱን አላቆመም ወይም አልተወም አብ የሰጠውን ሥራም እንደሚገባ ፈጸመ የተወደዳችሁ ቅዱሳን ትምህርቶቹ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ ያጠነጠኑ ሲሆን ለትምህርቶቹ እንደ መነሻ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ንኡሳን አርዕስቶች ተዘጋጅተው ስላሉ እነዛን አርዕስቶች እንደሚከተለው ለእናንተ ማቅረብ እወዳለሁ የመጀመርያውን ክፍለ ጊዜ የሚይዘው የትምህርት አርዕስት 1ኛ) የቅን ፍርድ መታጣት ምክንያቶችና ውጤቶቹ 2ኛ ) የፈሪሳውያን ዝምታን መምረጥ ( ዝምታ ) 3ኛ ) አገልግሎትንም ሆነ የክርስትናን ጉዞ አለመተው ፣ አለማቆም ( Give up አለማድረግ ) 4ኛ) አገልግሎታቸውንም ሆነ የክርስትና ጉዞአቸውን ያቆሙ ሰዎችና ችግሮቻቸው ( Give up ያደረጉ ) 5ኛ ) የሰጠንን ሥራ ፈጽመን እግዚአብሔርን በምድር ማክበር የሚሉት ናቸው እነዚህ ትምህርቶች እንግዲህ በቪዲዮ እንደሚገባ ተዘጋጅተው የቀረቡ ስለሆኑ አዳምጧቸው ከዚህ በተጨማሪም ለዚህ አገልግሎት መስፋፋት ከልባችሁ በቤታችሁ ሆናችሁ ጸልዩ እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ በሚመጡት ቃሎች ያንጸናል ተባረኩልኝ በክርስቶስ ፍቅር ወዳችኋለሁ ጸልይላችኋለሁ ዘመናችሁ ይባረክ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ Show less

No comments:

Post a Comment