በመንፈስቅዱስ መጠመቅ
መንፈስቅዱስ በማንኛውም ክርስቲያን ውስጥ ይኖራል መጽሐፍቅዱስ ደግሞ የሚያስተምረን በመንፈስቅዱስ መሞላት እንደምንችልና ለአገልግሎት ተጨማሪ ኃይልን መቀበል እንደምንችል ነው በዚህ ርዕስ መጽሐፍቅዱስ የሚለንን እስቲ እንመልከት
መንፈስቅዱስ በአሮጌው ኪዳን
በብሉይ ኪዳን መንፈስቅዱስ በእርግጠኝነት በሕዝቦች ላይ መጥቶ ለአገልግሎቱ ኃይል ይሞላቸዋል ይሁን እንጂ መንፈስቅዱስ በሁሉም ሕዝቦች ላይ አይመጣም እንደገናም እንደ ሐዲስ ኪዳኑ በቋሚነት ከእኛ ጋር ሊኖር አይመጣም ሙሴ ሕጉን ከእግዚአብሔር ሲቀበል በመንፈስቅዱስ ኢምፓወርድ ነበር ማለትም የመንፈስቅዱስን ሥልጣን ያገኘ እና የተቀዳጀ ነበር ጌታ እግዚአብሔር በአንድ ነገር ላይ የሙሴ ሽማግሌዎች በመንፈስቅዱስ ሥልጣን እንዲያገኙ ወሰነ ስለዚህም ሙሴ ሕዝብን የመምራት ሸክሙን ለሽማግሌዎቹ አከፋፈለ
ዘኊልቊ 11 ፥ 24 _ 29 ፤ ዘኊልቊ 24 ፥ 2
መንፈስቅዱስ በእነርሱ ላይ በመጣ ጊዜ ሽማግሌዎቹ ምን ሆነው ነበር ?
መንፈስቅዱስ በሽማግሌዎቹ ላይ በመጣ ጊዜ የሙሴ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር ?
መንፈስቅዱስ በሐዲስ ኪዳን
የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 1 _ 8 ይነበብ
በሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 5 ላይ ኢየሱስ ያመሳከረው አዲሱ ጥምቀት ምን ነበር ?
መንፈስቅዱስ በእኛ ላይ በመጣ ጊዜ ምን ተቀበልን ?
የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 1 _ 3 ይነበብ
ደቀመዛሙርቱ በመንፈስቅዱስ በተሞሉ ሰዓት ምን ሆኑ ?
የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 14 _ 21 ይነበብ
በመጨረሻው ቀን የራሱን መንፈስ ሲልክ እግዚአብሔር ምን ተስፋ ገባ ?
የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 37 _ 39 ይነበብ
የመንፈስቅዱስን ስጦታዎች ስንቀበል ሁኔታዎቹ ምንድናቸው ?
የመንፈስቅዱስ ተስፋ ለዛ ትውልድ ብቻ ነበር ?
የሐዋርያት ሥራ 8 ፥ 14 _ 21 ይነበብ
ጴጥሮስና ዮሐንስ በሰማርያ ለአዳዲስ አማኞች ለምን ጸለዩ ?
የሚታይ የመንፈስቅዱስ ምልክት በሳምራውያን ላይ የመጣ እንደነበር እንዴት አወቅን ?
በጌታ የእጁ ሥራ ላይ ሲሞን በመዋሸቱ ጴጥሮስ ዕድል ፈንታ ወይም ክፍል የለህም ለምን አለው ?
የሐዋርያት ሥራ 10 ፥ 34 _ 46 ይነበብ
በዚህ ምንባብ መሠረት እግዚአብሔር አብልጦ መውደዱን አሳየ ?
በአሕዛብ ላይ የመንፈስቅዱስ ስጦታ መፍሰሱን የአይሁድ አማኞች እንዴት አወቁ ?
በልሣን መናገር በመንፈስቅዱስ ለተጠመቁ ሰዎች መጽሐፍቅዱሳዊ ፓተርን የተከተለ ማለትም መጽሐፍቅዱሳዊ ይዘትና ቅርጽ ያለው ነገር ነው በልሣን መናገር የመንፈስቅዱስ ተጠማቂ ለመሆን የመጀመርያ የሚታይ ማስረጃ ነው ይህ ልምምድ የሚረዳው በአዲስ ኃይል ክርስቲናኖች እንዲያገለግሉ ለማስቻል ነው ይሁን እንጂ በመንፈስቅዱስ መሞላት ብዙ ቢሆንም በመንፈስቅዱስ መጠመቅ ግን አንዴ ነው
ኤፌሶን 5 ፥ 18 _ 20
እንድንሞላ ምን ታዘዝን ?
ሰዎች ሲጠጡ በተጽእኖ ሥር ወይም በአልኮል ቊጥጥር ሥር እንዳሉ ይናገራሉ ይህን በንጽጽር ሥር ስናየው በመንፈስቅዱስ መሞላት ውጤቱ ምንድነው ?
ገላትያ 5 ፥ 16 _ 25 ይነበብ
የመንፈስቅዱስ ፍሬ በመንፈስቅዱስ ለመራመዳችን የበለጠ ማስረጃ ነው በገላትያ 5 ፥ 22 _ 23 መሠረት የመንፈስቅዱስ ስጦታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል
ስንደመድመው በመንፈስቅዱስ ለመሞላት ያለማቋረጥ በተከታታይ መፈለግ ያስፈልገናል በቀላሉ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት በመሄድ በእርሱ መንፈስ ለመሞላት እርሱን መጠየቅ እራስንም ለእርሱ ማስገዛት ተገቢ ነው እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ለልጆቹ ለእኛ የተሻለ ነገር ይፈልጋል ለአገልግሎቱም በመንፈሱ ኃይል ይሞላናል እንደገናም እግዚአብሔር የመንፈስ ፍሬ ማስረጃ በሕይወታችን እንዲኖረን አጥብቆ ይፈልጋል
No comments:
Post a Comment