እምነትን ማካፈል
እምነትን ለሌሎች ማካፈል የክርስቲያን የሕይወት ክፍል ነው እምነታችንን ለሌሎች ማካፈል በኢየሱስ መታዘዝ የተሠራ እና የተከናወነ ታላቁ ተልእኮ ነው ኢየሱስ ለተከታዮቹ ወደ ዓለም ሁሉ እንዲሄዱ እና ሰዎችን ደቀመዛሙርት እንዲያደርጉ መመርያ ሰጥቶአቸዋል እምነታችንን ስለ ማካፈል መጽሐፍቅዱስ ምን እንደሚል እንመልከት
የማቴዎስ ወንጌል 28 ፥ 18 _ 20 እንመልከት
ኢየሱስ በተናገረው መሠረት የቤተክርስቲያን መልዕክትም ሆነ ተግባር ምንድነው ?
ወንጌል ለማን ነው ?
የዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 44 ይነበብ
ሰው ወደ ኢየሱስ ሊመጣ ምን መሆን ያስፈልገዋል ?
1ኛ ጢሞቴዎስ 2 ፥ 1 _ 4
በዚህ ምንባብ መሠረት እግዚአብሔር የዳኑ ሰዎችን ለማየት ምን ፈለገ ?
ጨውና ብርሃን መሆን
እምነታችንን ወደማካፈል ስንመጣ ሰዎችን ብቻ የምንጠራና ለሰዎችም የምንመሰክር አይደለንም በተለወጠው ሕይወታችንና በምንኖረው ሕይወታችንም ለሰዎች የምንመሰክር ነን
በማቴዎስ ወንጌል 5 ፥ 13 _ 16 መሠረት
ጨውና ብርሃን መሆን ስንል ምን ማለታችን ነው ?
በ2ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 2 _ 3 መሠረት
አማኞች በእያንዳንዱ ሰው የሚነበቡና የሚታወቁ ናቸው ስንል ይህ ምንባብ ምን እያለን ነው ?
ወንጌልን ማወጅ
ምስክርነታችንን ለሌሎች በራሳችን የአኗኗር ዘይቤዎች ማድረስ ትክክለኛነት ነው እንደገናም የራሳችንን ሃሳብ አፍልቀን ወይንም የመነሻ ሃሳብ ጥወስደን ወንጌልን ለሌሎች በቃል በንግጝር ማካፈል እንችላለን ጥቂት ምንባቦችን ከመጽሐፍቅዱስ ከወንጌል መልዕክት እንመልከት
ሮሜ 3 ፥ 9 _ 20 ፣ 23 ይነበብ
በዚህ ምንባብ መሠረት ማነው ኃጢአተኛና ከእግዚአብሔር ክብር የወደቀ ?
የዮሐንስ ወንጌል 3 ፥ 16 _ 21
በምን ተነሳሽነት ነው እግዚአብሔር ልጁን የሰጠው ?
እግዚአብሔር ልጁን ለማን ነው የሰጠው ?
ሰዎች በኢየሱስ ካላመኑ ከእግዚአብሔር ፊት ምን ሊያደርጉ ይነሳሉ ?
በዚህ ምንባብ መሠረት ሰዎች ወደ ኢየሱስ መምጣትን የሚጠሉትና የማይቀበሉት ስለምንድነው ?
የሐዋርያት ሥራ 17 ፥ 29 _ 31 ይነበብ
በቊጥር 30 መሠረት እግዚአብሔር ንስሐ እንዲገባ የጠራው ማንን ነው ?
ሮሜ 5 ፥ 17 ይነበብ
እምነታችንን በክርስቶስ ላይ ባደረግን ጊዜ ምን ዓይነት ስጦታ ተቀበልን ?
የራሳችንን ምስክርነት ወይም ታሪክ እናካፍል
የሐዋርያት ሥራ 26 ፥ 1 _ 29 ይነበብ
በዚህ ምንባብ ይህንን ምስክርነት ያካፈለው ማነው ?
በቊጥር 29 መሠረት የእርሱን ምስክርነት ከሰሙት ጳውሎስ አጥብቆ የፈለገው ምንድነው ?
ሌሎችን መጋበዝ
የዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 43 _ 51 ይነበብ
ናትናኤል ስለ ኢየሱስ ተጠራጣሪ በሆነ ጊዜ ፊልጶስ ምን መልስ ሰጠው ?
ስንደመድመው ሁላችንም እምነታችንን ልናካፍል የተጠራንና በታላቁ ተልዕኮ ክፍል ያለውን ድርሻችንን ልንወጣ የተጠራንን ነን ይህንን ማድረግ እንድንችል ብዙ መንገዶች አሉ ይህንን የምናደርገው ጨውና ብርሃን ሆነን ነው በዚህ መንገድ ሕይወታችንን ለሌሎች ማኖር አለብን በቃልና በንግጝር ወንጌልን ማካፈል እንችላለን ምስክርነታችንን ማካፈል እንችላለን ወደ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ሌሎችን መጋበዝ እንችላለን ወይንም ክርስቲያኖች ወደተሰበሰቡበትም ልንጋብዛቸው እንችላለን ስለሌሎች መዳን ሁልጊዜ መጸለይ እነርሱንም በፍቅር ማነሳሳታችንን እርግጠኞች መሆናችንን መረዳት ያስፈልገናል
No comments:
Post a Comment