Saturday, 27 August 2016

ግንኙነት Connecting

ግንኙነት    Connecting



Image result for connecting pictures


እግዚአብሔር የሰውን ዘር የፈጠረው ጥገኛ  ወይንም የሚወሰን  አድርጎ ነው በመጀመርያና በላቀ ሁኔታ እኛ ለእግዚአብሔር አስፈላጊዎች ነን እግዚአብሔርም እኛን የፈጠረን እርስ በእርሳችን ለመጠቃቀም ነው እግዚአብሔር አማኞች በፍቅር እና በዓላማ አንድ እንዲሆኑ እቅድ አለው ግንኙነታችንን ከሌሎች አማኞች ጋር ማሳደግ  ለመንፈሳዊ ዕድገትና ብስለት በጣም አስፈላጊ ነው አንዱና ትልቁ የክርስቲያን ሕይወት ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር  የፍቅር ሕዝብ የመሆን ክፍል ነው ከሌሎች ጋር መያያዝን በተመለከተ መጽሐፍቅዱስ ምን እንደሚል እስቲ እንመልከት 


ዘፍጥረት 2 15 _ 18 እንመልከት 



በቁጥር 18 ለሰው መልካም አይደለም ሲል እግዚአብሔር ምን እያለ ነው ?




1ኛ ሳሙኤል 18 1 _ 3




ዮናታን ታማኝ ጓደኛ በነበረበት ወቅት ለእኛ ትልቅ ምሳሌ ነው ዮናታን ዳዊትን ሲወድ ከብዙዎች መሐል እንደማን ሰው ነው ?




1ኛ ሳሙኤል 23 15 _ 18


Image result for Jonathan loved David pictures




ዳዊት ትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳለ ሳኦል ስላወቀ ሊገድለው ወጣ ዮናታን ደግሞ ለዳዊት የሚያበረታታ ቃል አቀረበለት  ጥንካሬን መፈለግን  በተመለከተ ዳዊትን የረዳው ዮናታን ምን አደረገ  ?     

Image result for Jonathan encouraged David for strength in pictures


ምሣሌ 27 ፥ 17 ይነበብ 




አንድ ሰው ሌላውን ሲስለው ማለት ምን ማለት ነው ?




የማቴዎስ ወንጌል 18 ፥ 19 _ 20 ይነበብ




አማኞች በኅብረት በጸለዩ ጊዜ በጸሎት ኃይል እንዳላቸው ኢየሱስ አስተምሮአል ?




ሁለትና ሦስት ሆነው በስሙ በተሰበሰቡ ጊዜ ኢየሱስ የት አለ ?




የዮሐንስ ወንጌል 17 ፥ 20 _ 23 ይነበብ 




አማኞች ኅብረት ኖሮአቸው አንድ እንዲሆኑ ኢየሱስ አጥብቆ ይፈልጋል ?



Image result for christian unity



አማኞች በአንድነት ሲሄዱ ምን ይሆናል ?




የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 42 _ 47 ይነበብ 





በቁጥር 42 መሠረት ብዙዎቹ ለወንጌል ምላሽ ከሰጡ በኋላ ደቀመዛሙርት ምን አደረጉ ?






እንዲህ ዓይነት ፍላጎት ያላት ቤተክርስቲያንና ማልዳ , ቀደም ወይንም ፈጠን ብላ የምትነሳ ቤተክርስቲያን ምን ማድረግ አለባት ?






ከመቅደሱ ሌላ በመጀመርያ ላይ ያሉ ደቀመዛሙርት የት ነው የሚገናኙት  ?





1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፥ 12 _ 27 ይነበብ 






የአማኞችን አንድነት ለማብራራት ጳውሎስ ምን ተጠቀመ ?











የየግል አማኞችን በልዩ ልዩ የሰውነት የአካል ክፍል ውስጥ ካሉ አማኞች ጋር ጳውሎስ አወዳደረ እያንዳንዱ የአካል ክፍል ዓላማ አለው ታድያ በቤተክርስቲያን ውስጥ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሚና ወይም ጠቀሜታ አለውን ?





ሌላው ክርስቲያን ሲሰቃይ ወይንም ሲከብር ክርስቲያኖች መልሳቸው ምን ይመስላል ማለትም እንዴት ይመልሳሉ ?






ዕብራውያን 10 ፥ 24 _ 25 ይነበብ







በዚህ ጥቅስ መሠረት ማድረግ የሌለብን ምንድነው ?








በአንድ ላይ ስንገናኝ ምን ማድረግ ያስፈልገናል ?





ክርስቶስ በቅርበት ሲመለስ ሳለ ክርስቲያኖች በበለጠ ወይም ባነሰ ሁኔታ መገናኘት ጠቃሚ ነውን ?




ስንደመድመው ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመደበኛነት ግንኙነት ለማድረግ መፈለግ አለብን ይህ ደግሞ ራሳችንን ለማበረታታትና ሌሎችንም ለማበረታታት ይፈቅድልናል በቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች ስጦታቸውን ሲያካፍሉ ሁሉም ወደ ብስለት ይመጣል እግዚአብሔር የፈጠረን ከእርሱ ጋር ላለ ግንኙነትና ለእርስ በእርስ ግንኙነት ነው ዛሬ ወይንም አሁን የግንኙነት ቡድን ፈልግ  

























































Saturday, 13 August 2016

እምነትን ማካፈል

እምነትን ማካፈል    









እምነትን ለሌሎች ማካፈል የክርስቲያን የሕይወት ክፍል ነው እምነታችንን ለሌሎች ማካፈል በኢየሱስ መታዘዝ የተሠራ እና የተከናወነ ታላቁ ተልእኮ ነው ኢየሱስ ለተከታዮቹ ወደ ዓለም ሁሉ እንዲሄዱ እና ሰዎችን ደቀመዛሙርት እንዲያደርጉ መመርያ ሰጥቶአቸዋል እምነታችንን ስለ ማካፈል መጽሐፍቅዱስ ምን እንደሚል እንመልከት 




የማቴዎስ ወንጌል 28 18 _ 20 እንመልከት







ኢየሱስ በተናገረው መሠረት የቤተክርስቲያን መልዕክትም ሆነ ተግባር ምንድነው ? 




ወንጌል ለማን ነው ? 



የዮሐንስ ወንጌል 6 44 ይነበብ




ሰው ወደ ኢየሱስ ሊመጣ ምን መሆን ያስፈልገዋል ?




1ኛ ጢሞቴዎስ 2 1 _ 4




በዚህ ምንባብ መሠረት እግዚአብሔር የዳኑ ሰዎችን ለማየት  ምን ፈለገ ?




ጨውና ብርሃን መሆን 








እምነታችንን ወደማካፈል ስንመጣ ሰዎችን ብቻ የምንጠራና ለሰዎችም የምንመሰክር አይደለንም በተለወጠው ሕይወታችንና በምንኖረው ሕይወታችንም ለሰዎች የምንመሰክር ነን 



በማቴዎስ ወንጌል 5 13 _ 16 መሠረት 


ጨውና ብርሃን መሆን ስንል ምን ማለታችን ነው ?




በ2ኛ ቆሮንቶስ 3 2 _ 3 መሠረት 




አማኞች በእያንዳንዱ ሰው የሚነበቡና የሚታወቁ ናቸው ስንል ይህ ምንባብ ምን እያለን ነው ?




ወንጌልን ማወጅ



ምስክርነታችንን ለሌሎች በራሳችን የአኗኗር ዘይቤዎች ማድረስ ትክክለኛነት ነው እንደገናም የራሳችንን ሃሳብ አፍልቀን ወይንም የመነሻ ሃሳብ ጥወስደን ወንጌልን ለሌሎች በቃል በንግጝር ማካፈል እንችላለን ጥቂት ምንባቦችን ከመጽሐፍቅዱስ ከወንጌል መልዕክት እንመልከት 



ሮሜ 3 9 _ 20 23 ይነበብ 




በዚህ ምንባብ መሠረት ማነው ኃጢአተኛና ከእግዚአብሔር ክብር የወደቀ ?



የዮሐንስ ወንጌል 3 16 _ 21 




በምን ተነሳሽነት ነው እግዚአብሔር ልጁን የሰጠው ?




እግዚአብሔር ልጁን ለማን ነው የሰጠው ?




ሰዎች በኢየሱስ ካላመኑ ከእግዚአብሔር ፊት ምን ሊያደርጉ ይነሳሉ ?




በዚህ ምንባብ መሠረት ሰዎች ወደ ኢየሱስ መምጣትን የሚጠሉትና የማይቀበሉት ስለምንድነው ?




የሐዋርያት ሥራ 17 29 _ 31 ይነበብ





በቊጥር 30 መሠረት እግዚአብሔር ንስሐ እንዲገባ የጠራው ማንን ነው ? 




ሮሜ 5 17 ይነበብ 





እምነታችንን በክርስቶስ ላይ ባደረግን ጊዜ ምን ዓይነት ስጦታ ተቀበልን ?





የራሳችንን ምስክርነት ወይም ታሪክ እናካፍል 



የሐዋርያት ሥራ 26 1 _ 29 ይነበብ 




በዚህ ምንባብ ይህንን ምስክርነት ያካፈለው ማነው ?




በቊጥር 29 መሠረት የእርሱን ምስክርነት ከሰሙት ጳውሎስ አጥብቆ የፈለገው ምንድነው ? 




ሌሎችን መጋበዝ 








የዮሐንስ ወንጌል 1 43 _ 51 ይነበብ 



ናትናኤል ስለ ኢየሱስ ተጠራጣሪ በሆነ ጊዜ ፊልጶስ ምን መልስ ሰጠው ?





ስንደመድመው ሁላችንም እምነታችንን ልናካፍል የተጠራንና በታላቁ ተልዕኮ ክፍል ያለውን ድርሻችንን ልንወጣ የተጠራንን ነን ይህንን ማድረግ እንድንችል ብዙ መንገዶች አሉ ይህንን የምናደርገው ጨውና ብርሃን ሆነን ነው በዚህ መንገድ ሕይወታችንን ለሌሎች ማኖር አለብን በቃልና በንግጝር ወንጌልን ማካፈል እንችላለን ምስክርነታችንን ማካፈል እንችላለን ወደ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ሌሎችን መጋበዝ እንችላለን ወይንም ክርስቲያኖች ወደተሰበሰቡበትም ልንጋብዛቸው እንችላለን ስለሌሎች መዳን ሁልጊዜ መጸለይ እነርሱንም በፍቅር ማነሳሳታችንን እርግጠኞች መሆናችንን መረዳት ያስፈልገናል 

Thursday, 11 August 2016

ፈተናን መቋቋም Resisting temptation

ፈተናን መቋቋም  Resisting temptation





እያንዳንዱ ክርስቲያን ፈተናን ፊት ለፊት የሚገጥም ሊሆን ይገባል ማለትም ፈተናን መሸሽ ወይም መራቅ የለበትም  መፈተን ኃጢአት አይደለም ለፈተና ስንገኝ ብቻ ግን በኃጢአት እንወድቃለን ስለዚህ ፈተናን አሸናፊዎች እንድንሆን እግዚአብሔር በመንፈሱና በቃሉ እየሞላን ያዘጋጀናል መጽሐፍቅዱስ በቃሉ ስለዚህ ርዕስ ምን እንደሚለን እስቲ እንመልከት 





ያዕቆብ 1 13 _ 15 ይነበብ




እግዚአብሔር ክፉ እንድናደርግ ይፈትናል ?




በቊጥር 14 መሠረት እኛ እንዴት ተፈተንን ? 




1ኛ ቆሮንቶስ 10 13 ይነበብ





ፈተናዎች በሙሉ ለሰው ዘር የተለመዱ ናቸው ? 





ፈተናን ስንገጥም በምን መንገድ እግዚአብሔር ለእኛ ታማኝ ነው ?




የማቴዎስ ወንጌል 4 1 _ 11 ይነበብ




 ፈተናን ሲቋቋም ኢየሱስ ምን የተጠቀመ ነበር ?




የማቴዎስ ወንጌል 26 41 ይነበብ




በፈተና መውደቅን እንዲያስወግዱ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው ምን ነበር ?





ዕብራውያን 4 14 _ 16 ይነበብ




በፈተና ውጊያ ስንሆን ስለምን ኢየሱስ ከእኛ ጋር ማውራት ቻለ ?




በሚያስፈልገን ጊዜ እግዚአብሔር ምን ሊሰጠን ይፈልጋል ?




2ኛ ቆሮንቶስ 10 4 _ 5




ምርኮኛን ለመውሰድና ለክርስቶስም እንዲታዘዝ ለማስቻል ምን ማድረግ አለብን ?




ምሳሌ 3 7 ይነበብ 




በዚህ ጥቅስ መሠረት በዓይኖቻችን ጥበበኞች ከምንሆን ይልቅ ምን ማድረግ ያስፈልገናል ?




ኢሳይያስ 48 17 _ 18




በዚህ ምንባብ መሠረት እግዚአብሔር አጥብቆ የሚፈልገው ለእኛ የተሻለ ነገር ምንድነው ?



ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት የመታዘዝ ውጤቱ ምንድነው ?





በኃጢአት ብንወድቅ አሁንም ለእኛ ተስፋ አለን ? 




1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 1 9  ይነበብ




እኛ ታምነን ኃጢአታችንን ከተናዘዝን እግዚአብሔር በታማኝነት ምን ያደርጋል ?




መዝሙር 103 13 _ 14 ይነበብ 




በምድር ላይ እንዳለ አባት ሊሆን እግዚአብሔር በምን መንገድ የተናገረ ነው ?




በቊጥር 14  እግዚአብሔር ከፍ ያለ ርህራሄ ሊያሳየን የፈለገበት ምክንያቱ ምንድነው ?









ስንደመድመው ክርስቲያን ፈተናን ሲገጥም ኃይል የሌለው አይደለም እግዚአብሔር እንድናሸንፍ መንፈሳዊ መዋግያ መሣርያ ሰጥቶናል እኛም በውጊያ ውስጥ ነን እግዚአብሔር ለእኛ የተሻለው ነገር ምን እንደሆነ አጥብቆ ይፈልጋል በቅድስና መራመድ ሰላምንና የእግዚአብሔርን ደስታ ያመጣል እንደገናም ኃጢአትን ማስወገድ ከብዙ የግል ያልተፈለገ ቊስለት ይጠብቀናል ክርስቲያን ኃጢአት ካደረገ ንስሐ መግባት መቻል አለበት እግዚአብሔርም ይቅር እንዳለው እረፍትም እንደሰጠው ማረጋገጥ አለበት ከእርሱም ጋር የነበረውን ኅብረት ማደስና መመለስ አለበት 

Wednesday, 10 August 2016

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: በመንፈስቅዱስ መጠመቅ

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: በመንፈስቅዱስ መጠመቅ: በመንፈስቅዱስ መጠመቅ መንፈስቅዱስ በማንኛውም ክርስቲያን ውስጥ ይኖራል መጽሐፍቅዱስ ደግሞ የሚያስተምረን በመንፈስቅዱስ መሞላት እንደምንችልና ለአገልግሎት ተጨማሪ ኃይልን መቀበል ...

Tuesday, 9 August 2016

ማገልገል Serving

ማገልገል   Serving






እያንዳንዱ ክርስቲያን የአገልግሎትን ሁኔታ ይጠብቃል እግዚአብሔር በስጦታና በችሎታ በጥበብና በብልሃት በመንፈሳዊ ስጦታም እያንዳንዱን ሰው ማዘጋጀት ይፈልጋል እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ዓይነት ስጦታን እንድንጠቀም አጥብቆ ይፈልጋል እንድናገለግለውም ስጦታውን ሰጥቶናል ስናገለግልም የኢየሱስን ዱካ እየተከተልን ልናገለግል ይገባል እንደገናም በቤተክርስቲያን ስናገለግል ለሕይወታችን ቅድሚያ ሰጥተን  በእግዚአብሔር ደስታ ውስጥ መግባትና በመንፈሳዊ ብስለት ማደግ አለብን ስለ አገልግሎት መጽሐፍቅዱስ ምን እንደሚል ለማየት ወደ መጽሐፍቅዱስ ሃሳብ እንመለስ 



በኤፌሶን 2 10 መሠረት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርነው ምን ለማድረግ ነው ?




በኤፌሶን 4 11 _ 13 በዚህ ምንባብ መሠረት ኢየሱስ ሕዝቡን ለመርዳትና ለማዘጋጀት ሲል የሰጠው ምን ነበር ?




ለአገልግሎት ሥራስ የተዘጋጀው እና የታጠቀው ማን ነው ?



የእግዚአብሔር ሕዝብ ለአገልግሎቱ ሥራ የተዘጋጀ ሲሆን ውጤቱ ምንድነው ?





ሮሜ 12 6 _ 8 1 ጴጥሮስ 4 7 _ 11 ይነበብ 






በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት ሁሉም ክርስቲያን አንድ ዓይነት ስጦታ አላቸውን ?




እግዚአብሔር በሰጠን ስጦታ ምን ማድረግ ያስፈልገናል ?




ስለ አገልግሎት ኢየሱስ ምን እንደተናገረ በመቀጠል እንመልከት 


የዮሐንስ ወንጌል 13 1 _ 17 እንመልከት 






ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ተግባራዊ እያደረገ ነበር ወይንስ መንፈሳዊ ትምህርትን ለማስተማር እየሞከረ ነበር ?




አንዱ የአንዱን እግር ሊያጥብ ያስፈልገዋል ሲል ኢየሱስ ምን ለማለት የፈለገ ነው ?




በቊጥር 17 መሠረት በረከትን ስለሚያመጣው ነገር ኢየሱስ ምን አለ ?




የዮሐንስ ወንጌል 12 26 ይነበብ




ኢየሱስ የትኛውን ምሣሌ በእርግጠኝነት መከተል እንዳለብን ተናገረ ?




አባቱን ስለማክበር ኢየሱስ ምን አለ ?




የማርቆስ ወንጌል 10 42 _ 45 ይነበብ




በእግዚአብሔር ዓይን ትልቅ የመሆን አንዱ ጉዳይ እንዴት ነው ?




ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው ታድያ ኢየሱስ ለማገልገል የመጣ ነው ወይንስ እንዲያገለግሉት ?




ኤፌሶን 6 7 _ 8 ይነበብ 



በሙሉ ፈቃድና ልብ እንድናገለግል የነገረን ማን ነው በእውነተኝነትስ  ያገለገለ ማን ነው ?




የሉቃስ ወንጌል 10 38  _ 42  ይነበብ




ማርታ እያገለገለች ሳለች ስሕተት ነበረች ?




ማርያም በኢየሱስ የታዘዘችው ስለምን ነበር  ?




ከዚህ ምንባብ ምን ዓይነት ጠቃሚ ትምህርት ልንማር ችለናል ?







ስንደመድመው በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እርሱ የሰጠንን ችሎታና ስጦታ በመጠቀም እርሱን ለማገልገል ጊዜን ማዘጋጀት አለብን እርሱን በሕይወታችን መጀመርያ እንድናደርግ እግዚአብሔር አጥብቆ ይፈልጋል ይህ ማለት ለማገልገል ጊዜን መውሰድ ማለት ነው ጠቃሚ በሆነው የሕይወታችን ክፍል ሌሎችን ስናገለግል እና የኢየሱስን ዱካ ስንከተል በመንፈሳዊ ሕይወታችን እናድጋለን በአገልግሎት ሌሎችን ስንባርክ እግዚአብሔር ደግሞ እኛን ይባርከናል 

Monday, 8 August 2016

በመንፈስቅዱስ መጠመቅ

በመንፈስቅዱስ መጠመቅ




መንፈስቅዱስ በማንኛውም ክርስቲያን ውስጥ ይኖራል መጽሐፍቅዱስ ደግሞ የሚያስተምረን በመንፈስቅዱስ መሞላት እንደምንችልና ለአገልግሎት ተጨማሪ ኃይልን መቀበል እንደምንችል ነው በዚህ ርዕስ መጽሐፍቅዱስ የሚለንን እስቲ እንመልከት



መንፈስቅዱስ በአሮጌው ኪዳን 






በብሉይ ኪዳን መንፈስቅዱስ በእርግጠኝነት በሕዝቦች ላይ መጥቶ ለአገልግሎቱ ኃይል ይሞላቸዋል ይሁን እንጂ መንፈስቅዱስ በሁሉም ሕዝቦች ላይ አይመጣም እንደገናም እንደ ሐዲስ ኪዳኑ በቋሚነት ከእኛ ጋር ሊኖር አይመጣም ሙሴ ሕጉን ከእግዚአብሔር ሲቀበል በመንፈስቅዱስ ኢምፓወርድ ነበር  ማለትም የመንፈስቅዱስን ሥልጣን ያገኘ እና የተቀዳጀ ነበር ጌታ እግዚአብሔር በአንድ ነገር ላይ የሙሴ ሽማግሌዎች በመንፈስቅዱስ ሥልጣን እንዲያገኙ ወሰነ ስለዚህም ሙሴ ሕዝብን የመምራት ሸክሙን ለሽማግሌዎቹ አከፋፈለ 

ዘኊልቊ 11 24 _ 29 ዘኊልቊ 24



መንፈስቅዱስ በእነርሱ ላይ በመጣ ጊዜ ሽማግሌዎቹ ምን ሆነው ነበር ?




መንፈስቅዱስ በሽማግሌዎቹ ላይ በመጣ ጊዜ የሙሴ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር ?




መንፈስቅዱስ በሐዲስ ኪዳን




የሐዋርያት ሥራ 1 1 _ 8  ይነበብ 





በሐዋርያት ሥራ 1 5 ላይ ኢየሱስ ያመሳከረው አዲሱ ጥምቀት ምን ነበር ?




መንፈስቅዱስ በእኛ ላይ በመጣ ጊዜ ምን ተቀበልን ?




የሐዋርያት ሥራ 2 1 _ 3 ይነበብ 






ደቀመዛሙርቱ በመንፈስቅዱስ በተሞሉ ሰዓት ምን ሆኑ ?




የሐዋርያት ሥራ 2 14 _ 21  ይነበብ




በመጨረሻው ቀን የራሱን መንፈስ ሲልክ እግዚአብሔር ምን ተስፋ ገባ ?




የሐዋርያት ሥራ 2 37 _ 39  ይነበብ 




የመንፈስቅዱስን ስጦታዎች ስንቀበል ሁኔታዎቹ ምንድናቸው ?




የመንፈስቅዱስ ተስፋ ለዛ ትውልድ ብቻ ነበር ?




የሐዋርያት ሥራ 8 14 _ 21 ይነበብ 




ጴጥሮስና ዮሐንስ በሰማርያ ለአዳዲስ አማኞች ለምን ጸለዩ ?




የሚታይ የመንፈስቅዱስ ምልክት በሳምራውያን ላይ የመጣ እንደነበር እንዴት አወቅን ?




በጌታ የእጁ ሥራ ላይ ሲሞን በመዋሸቱ ጴጥሮስ ዕድል ፈንታ ወይም ክፍል የለህም ለምን አለው  ?




የሐዋርያት ሥራ 10 34 _ 46  ይነበብ 




በዚህ ምንባብ መሠረት እግዚአብሔር አብልጦ መውደዱን አሳየ ?




በአሕዛብ ላይ የመንፈስቅዱስ ስጦታ መፍሰሱን የአይሁድ አማኞች እንዴት አወቁ ?





በልሣን መናገር በመንፈስቅዱስ ለተጠመቁ ሰዎች መጽሐፍቅዱሳዊ ፓተርን የተከተለ ማለትም መጽሐፍቅዱሳዊ ይዘትና ቅርጽ ያለው ነገር ነው በልሣን መናገር የመንፈስቅዱስ ተጠማቂ ለመሆን የመጀመርያ የሚታይ ማስረጃ ነው ይህ ልምምድ የሚረዳው በአዲስ ኃይል ክርስቲናኖች እንዲያገለግሉ ለማስቻል ነው ይሁን እንጂ በመንፈስቅዱስ መሞላት ብዙ ቢሆንም በመንፈስቅዱስ መጠመቅ ግን አንዴ ነው 



ኤፌሶን 5 18 _ 20




እንድንሞላ ምን ታዘዝን ?



ሰዎች ሲጠጡ በተጽእኖ ሥር ወይም በአልኮል ቊጥጥር ሥር እንዳሉ ይናገራሉ ይህን በንጽጽር ሥር ስናየው በመንፈስቅዱስ መሞላት ውጤቱ ምንድነው ?




ገላትያ 5 16 _ 25 ይነበብ 




የመንፈስቅዱስ ፍሬ በመንፈስቅዱስ ለመራመዳችን የበለጠ ማስረጃ ነው በገላትያ 5 22 _ 23 መሠረት የመንፈስቅዱስ ስጦታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል 






ስንደመድመው በመንፈስቅዱስ ለመሞላት ያለማቋረጥ በተከታታይ መፈለግ ያስፈልገናል በቀላሉ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት በመሄድ በእርሱ መንፈስ ለመሞላት እርሱን መጠየቅ እራስንም ለእርሱ ማስገዛት ተገቢ ነው እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ለልጆቹ ለእኛ የተሻለ ነገር ይፈልጋል ለአገልግሎቱም በመንፈሱ ኃይል ይሞላናል እንደገናም እግዚአብሔር የመንፈስ ፍሬ ማስረጃ በሕይወታችን እንዲኖረን አጥብቆ ይፈልጋል