Friday, 29 April 2016
Lesson one የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 Part 3 የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ኃይልን ማበርታት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በብዙ አስፈላጊ ነገር ነው ኃይልን ማበርታት በዚህ ምድር በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ገብቶ ለመኖር ፣ ኃይልን ማበርታት ለተልዕኮና ለእግዚአብሔር ሥራ በእርግጠኝነት ይጠቅማል ኃይላቸውን ያላበረቱ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር በአግባቡ መኖር አይችሉም ወሳኝ በሆነ የሕይወት አቁዋም ላይ ሲቀለበሱ ፣ ሲንሸራተቱና ሲያስመስሉ አልፈው ሄደውም በግብዝነት ያልሆኑትን ሲሆኑ ሌሎችንም ሊመስሉ ሲሳቡና በደቦም ሲጉዋዙ ይስተዋላሉ ገላትያ 2 ፥ 11 _ 14 ኃይላቸውን ያበረቱ ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ሊፈጽሙ ዳር የሚያደርሱና ሥራውንም ሳያዝረከርኩ በትክክል የሚወጡ ናቸው ለዚህም ነው ሚክያስ በትንቢቱ እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ ያለን ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 ለምን ስንል አሁንም ሚክያስ በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው፦ ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል ይለናል ትንቢተ ሚክያስ 2 ፥ 1 ታድያ አሁንም ኃጢአትን ኃጢአት በደሉንም ሳያሽሞነሙኑ በደል ነው ብለው ሊናገሩ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልተው የሚገለጡ ሰዎች ሲመጡ በመኝታቸው ላይ በደልን አስበው እና ሊፈጽሙም ተቀስቅሰው የሚመጡ ሰዎች ይከለከላሉ 1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 20 እና 2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 1ን በሙሉ ይመልከቱ ወደ ሐዲስ ኪዳንም ሄደን ስንመለከት ዮሐንስ መጥምቁ በሄሮድስና በቤተመንግሥቱ የበደል ሥራ ውስጥ ተገልጦ ያደረገው ነገር ይህንን ነው ዮሐንስ ሄሮድስን፦ የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና ይለናል የማርቆስ ወንጌል 6 ፥ 18 ከዚያም አልፎ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል በማለት ይነግረናል የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 17 ይሁን እንጂ ታድያ መንፈስንና ኃይልን ካለማበርታት የተነሳ ዛሬ ላይ የቤተክርስቲያን መልዕክት ተንቆ ፣ ቀዝቅዞና ተለሳልሶ በምትኩ በደልና መተላለፍ ከፍ ብሎ ነግሦ በዓለማችንም ሆነ በቅዱሳን መካከል ይታያል ፣ በጉልህም ይንጸባረቃል ይህንንም በደል ለመቀነስ ሲባል አሁንም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል የሚሄድ እንደ ዮሐንስ ያለ ነገሥታት የሚሰሙት ፣ ለመልዕክቱም ታዘው ምን እናድርግ የሚሉት ፣ አንዳንዶችም ሰምተው የጌታን መንገድ ለመከተል ሲሉ በመልዕክቱ ኃይል ተነክተው ለመወሰን በልባቸው የሚያመነቱበት ሰው አልተገኘም ከዚህም ሌላ በዚሁ መንገድ ጻድቅና ቅዱስ እንደሆነ ተቆጥሮ የሚፈራና የሚጠበቅም እንደ ዮሐንስ ያለ ሰው ሊገኝ በፍጹም አልቻለም ይልቁንም አሁን ላይ ያለው መንፈስ የኤልያስ መንፈስ ሳይሆን የኢየሱስን የኪዳኑን ሕጎች የሚያጸና በማከናወንም የሚገልጣቸው መንፈስ ነው ያለው ነገር ግን ክንውኑን ሊገልጹ በእግዚአብሔር ቃል እውነት ፣ በተወለደ ማንነትና ባደገ ስብእና ከመንፈሱ ጋር የሚፈሱ ሰዎች በዚያን ዘመን ቢኖሩም በዘመናችን ግን ለዚህ መንፈስ የተገቡ ከጥቂት ሰዎች በቀር በአብዛኛው ለዚህ የተዘጋጀን ባለመሆናችን ዛሬ በጋብቻ ዙርያ ፣ በዘመን መካከል ባለ የትውልድ የግንኙነትና የልብ መቀባበል ዙርያ ፣ የጻድቃን ጥበብ በሚሆን ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ዙርያ ሰዎችን አልደረስናቸውም ፣ አላገኘናቸውምም ስለዚህ አሁን ላይ ባለ ዘመን ሁሉም ነገር ምስቅልቅሉ ወጥቶ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው በነዚህ በዘረዘርኩዋቸው ጉዳዮችና ሌሎችም ባልጠቀስኩዋቸው ነገሮች ውስጥ የሰፋ ክፍተት አለ መረንነት ፣ ሕግ አልበኝነት ፣ ማናለብኝነት ፣ አለሌነትና ዋልጌነት ገዝፎ ከፍቶና ሰልጥኖ ዓለማችንን ወርሮአል ትምህርቱ እነዚህን ይዘቶች በተገቢ መልኩ የሚጠቃቅስና መፍትሔዎቻቸውንም የሚጠቁም በመሆኑ በቪዲዮ ተዘጋጅቶ ተከታታይነትና ቀጣይነት ባለው መልእክት ይደመጥ ዘንድ ቀርቦአል በዚህ ትምህርት ሁላችሁም እንደምትባረኩበት አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment