Thursday, 14 April 2016
(ትምህርት ሁለት) የትምህርቱ ርዕስ :- ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም ( ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ትን...ትምህርት ሁለት ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ ወቅታዊ እና ትምህርት አዘል መልዕክት ነው የትምህርቱ ርዕስ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም የሚል ሲሆን :---------------- የምንባቡ መነሻ ሃሳብ ደግሞ የኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት ውስጥ ኃይልን ስለመታጠቅ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ትምህርቶች መካከል የተወሰደና ጥቂቱን ሃሳብ የያዘ ነው ሙሉውን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት የማቀርበው ይሆናል በዚህ አጋጣሚ ግን የፓልቶክን አገልግሎት ለማታውቁ በየሳምንቱ ማክሰኞ በእኔ የሰዓት አቆጣጠር ከ 10 ፥ 30 ማለዳ ላይ ጀምሮ በዚሁ ሩም በእኔ በባርያው የሚተላለፍ ትምህርት ስላለ እርሱን እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናሁን ማሳሰብ እወዳለሁ ሩሙ ማለትም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ስለዚህ ጊዜ ያላችሁ ወገኖች በእነዚህ ሰዓታቶች ሁሉ እየገባችሁ መካፈል የምትችሉ መሆናችሁን ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ በመቀጠልም ወዳዘጋጀሁት የትምህርት ሃሳብ ስመጣ ይህንን ጸሎት ኤርምያስ እንዲህ ሲል የጸለየው ጸሎት ቢሆንም በትላንትናው ዘመን በኤርምያስ ብቻ ሳይሆን አሁንም ላይ ባለ ዘመንና እስከ ለዘላለሙም ከእግዚአብሔር ያለፈ ፣ ከእግዚአብሔርም የሚያቅት ምንም ነገር የሌለ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ይጠቁማል ለዚህም ነው እንግዲህ ኤርምያስ አሁንም በትንቢቱ አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ሲል የነገረን ትንቢተ ኤርምያስ 10 ፥ 6 የእግዚአብሔር ታላቅነት በየት በየት ቦታ እና ለምን ለምን ጉዳይ ተገለጠ ስንል ደግሞ በቪዲዮ የሚለቀቀው ትምህርት ስላለ እርሱ ሰፊውን ሃሳብ ይዞ ይመልስልናል ከዚህም ባሸገር የዚህ ትምህርታዊ መልዕክት ዋናውና አንኳሩ ሃሳብ እነዚህ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር እንደሌለ የተረዱ እና የተባሉትን ነገር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚቃኝ ሲሆን ከተባሉት ነገር ውጪ ያደረጉ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ትምህርቱ በሰፊው አብራርቶ ይዘረዝራል ይህ ትምህርት ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ መካከል ባለ የሥራ ዘርፍ ፣ በቤተክርስቲያንና በመሣሠሉት የሃላፊነት ቦታዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተግባርና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጭምር በምን መንገድ ሊወጡት እንደሚገባ በሰፊው የሚያብራራ ፣ የሚያትትና የሚያስተምርም ነው ታድያ ይህንን ትምህርት አስተውለን እንደሚገባ ከተከታተልነው በተገቢው መንገድ እንደምንጠቀም ሕይወታችንም በዚሁ ቃል በብዙ እንደሚለወጥ እምነቴ ነው ውድ የቃሉ አድማጮች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እንግዲህ ይህን በቪዲዮ የሚለቀቀውን ትምህርት ከሰማችሁ በኋላ ለሌሎች ሊሰሙ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ሼር በማድረግ ትምህርቱን እንድታሰሙ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment