ከእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የሚመራ መፈለግ
Seek
Guidance from God`s Church
ክፍል ሦስት
ይህ በ Joshua
Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry
ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው
በማንኛውም የጥናት ዘገባ ሁልጊዜ ውጤታማ ከሆኑ ሰዎች ወይም ካሟሉ ሰዎች እርዳታን መፈለግ በጣም ጥሩ ነው እግዚአብሔር ባርያዎቹን ሙሉ ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ሕዝቡን እንዲመሩ ኮሚሺን ሰጥቷቸዋል ኮሚሺን አንድ ነገር እንዲደረግ ሥልጣን መስጠትን የሚያመለክት ነው ታድያ የእግዚአብሔር ባርያዎች ኮሚሺን ከእግዚአብሔር በአደራ መልክ የተሰጠ ኮሚሺን ነው መጽሐፍቅዱሳችን ሲናገር መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል ይለናል መጽሐፈ ምሳሌ 11 ፥ 14 እንደገናም በመጽሐፈ ነህምያ 8 ፥ 8 ላይ የእግዚአብሔርንም ሕግ መጽሐፍ አነበቡ ዕዝራም እግዚአብሔርን ማወቅ ያስተምርና ያስታውቅ ነበር፥ ሕዝቡም የሚነበበውን ያስተውሉ ነበር ይለናል ስለዚህ ሰው ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ከሚያስተምር ሰው እግዚአብሔርን ማወቅ በሚማርበት ጊዜ ማስተዋሉም ሆነ በጎ የሆነው
ድርጊቱ እየጨመረ ይመጣል ምክንያቱም መዝሙረ ዳዊት 111 : 10 ላይ የጥበብ መጀመሪያ
እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋል
አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል ይለናል ይህንኑ ቃል በእንግሊዘኛው መጽሐፍቅዱስ ሄደን ስንመለከተው ይበልጥ በግልጽነት ሠፍሮና ተብራርቶ
እናገኘዋለን The fear of the Lord is the beginning of wisdom all those
who practice it have a good understanding He praise endures forever ነው የሚለን ነገር ግን ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ካላወቀ
እግዚአብሔርን ማወቅ አይችልም በመጽሐፈ ምሳሌ 30 ፥ 3 ላይ ጥበብንም አልተማርሁም፥ ቅዱሱንም አላወቅሁትም ይለናል እንደገናም ሰው እግዚአብሔርንና ቃሉን ካላወቀ ካልተማረም
ሕይወቱ ይህንን የሚመስል ነው በ2ኛ ዜና መዋዕል 15 ፥ 1 _ 6 ላይ የእግዚአብሔርም መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ ሆነ አሳንም ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል ብትተዉት ግን ይተዋችኋል እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር በመከራቸውም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው በፈለጉት ጊዜ አገኙት በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረም፥ በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ነበረ እግዚአብሔር በመከራው ሁሉ ያስጨንቃቸው ነበርና ወገን ከወገን ጋር፥ ከተማም ከከተማ ጋር ይዋጋ ነበር ይለናልና በመሆኑም እንዲህ ዓይነቱ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ካለመማሩና
ከለማወቁም የተነሳ ሕይወቱ በረብሻ የተሞላ ስለሆነ ሰላም የሌለው በታላቅ ሁኔታ የሚደነግጥ እግዚአብሔር ሳይቀር በመከራው ሁሉ የሚያስጨንቀው ወገን ከወገኑ ማለት እርስ በራሱ ከተማ ከከተማ ጋር ሳይቀር የሚጣላ የሚጠላላና የሚዋጋ ይሆናል ለዚህ ነው ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ የሚለን ኦሪት ዘሌዋውያን 25 ፥ 18 በ1ኛ ተሰሎንቄ 4 ፥ 10 _ 12 ላይ ደግሞ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለንም ይለናል ስለዚህ ጸጥታ ስለራስ ጉዳይ መጠንቀቅና ከሌላው ወይንም የሌላውን አንዳች ሳይፈልጉ በየገዛ እጆች የራስን ሥራ እየሠሩ በውጪ ባሉት ዘንድ በአገባብ መመላለስ እግዚአብሔርንና ቃሉን ከሚያውቅ ሰው የምንጠብቀው ነው በመሆኑም ይህ እንዲሆን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በሕይወታቸው ሳይቀር የሚያሳዩ የሚተገብሩ የሚያውቁና ይህንኑ የእግዚአብሔርንም ቃል ገልጠው የሚያስተምሩን ያስፈልጉናል የእግዚአብሔርን ቃል እየተማርን የእግዚአብሔር ቃል እየተገለጠልን ሲመጣ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች ከፊት ይልቅ ልትበዙ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ ………… እንደተባሉት የእኛም ነገር እንዲሁ ከፊት ይልቅ እየበዛና እየጨመረም ይመጣል በሐዋርያት ሥራ 18 ፥ 24 _ 28 ላይ በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፥ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ፥ ወንድሞቹ አጸናኑት፥ ይቀበሉትም ዘንድ ወደ ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና ይለናል ስለዚህ ስለዚህ ዛሬም የአጵሎስ ነገር ብቻ ሳይሆን የእኛም የሰዎች ነገር ከፊት ይልቅ እየተገለጠ የሚመጣው የሚጨመረውና ውጤት ላይ ደርሶም ለተግባር የሚበቃው ይህን እውነት የተረዱ ለእኛ ከፊት ይልቅ ሲገልጡ ብቻ ሳይሆን እንደ መንፈስቅዱስ ፈቃድ ሰዎችን አግኝተው ባገኟቸው ሰዎች ውስጥም ጅማሬም ሲያደርጉ ነው የሐዋርያት ሥራ 8 ፥ 30 እና 31፣ ሮሜ 10 ፥ 14 እና 15 ጅማሬ ስንል ደግሞ የወንጌል ጅማሬ ብቻ አይደለም ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል ስለሚል መጽሐፈ ኢዮብ 8 ፥ 7 እግዚአብሔር በእኛ በሚጀምረው ሥራ እስከፍጻሜው ድረስ መሄድ ነው በምናነበው ቃል እግዚአብሔር ይባርከን አሜን
በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና
ፊልጵስዩስ 1 ፥ 6
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
|
No comments:
Post a Comment