የሚመራ መፈለግ
Seeking
Guidance
ሀ _ የቃሉ ተማሪ መሆን
Become a
student of the word
Take not
ክፍል አራት
እግዚአብሔር የቃሉ ተማሪ እንድንሆንለት ይፈልጋል በዘጸአት 4 ፥ 12 ላይ እንግዲህ አሁን ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ አለው ይለናል በመጽሐፈ ኢዮብ 33 ፥ 33 ላይ ደግሞ ያለዚያም እኔን ስማ ዝም በል፥ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ በመዝሙረ ዳዊት 32 ፥ 8 ላይም አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ ይለናል ጌታ እግዚአብሔር ሊያስተምረን ሲፈልግና ሲያስተምረን ማድረግ የሚገባን ነገር በቅድሚያ ዝም ማለት ነው እንደገናም እርሱን መስማት ነው ያንጊዜ ከዚሁ ጌታ ጥበብን መማር ይሆንልናል ይህ በሚሆንበት ጊዜ በምንሄድበት መንገድ ሁሉ ይመራናል ዓይኖቹንም በእኛ ላይ ያጸናል ይህ ካልሆነ ግን ማለት እርሱ ሊያስተምረን ሲፈልግ እኛም ከእርሱ ልንማር ስንል
ዝም ማለት ካልቻልንና እርሱንም ለመስማት ካልወደድን ፍጹም የምንማረው ነገር አይኖርም እርሱም ዓይኖቹን በእኛ ላይ አያጸናም ማለት እንደ መልካም ተማሪም ሊከታተለን አይወድም ለዚህ ነው ዘማሪ ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ ማለዳ እየመጣህ ስታነቃኝ ጆሮዬን ከፍተህ ስትናገረኝ በማስተዋል መንገድ ስትመራኝ ከሕይወት ምንጭ ውሃ ስታረካኝ ለምልሞ ነበር ሕይወቴ እንዲህ አልዛለም ጉልበቴ እባክህ አስበኝ አንተ ነህ መድኃኒቴ መቼ ነው ነቅቼ ድምጽህን የምሰማው ለነፍሴ መጎብኘት መጽናናት የሚመጣው በሌሊት ስነሳ ከእንቅልፌ ስምህ ነው የሚመጣው ፈጥኖ በአፌ ሕመሜን ለአንተ እናገራለሁ ድምጽህን አሰማኝ እማራለሁ ጌታ ሆይ መቃተቴን ስማ ነፍሴ እንደዚህ ተዳክማ እንደምን ትዘልቃለች ትካዜን ተሸክማ እያለ ይህን አስደናቂ መዝሙር የዘመረልን ሙሉውን ስንኝ እናንተ ፈልጋችሁ በማግኘት ዘምሩት መዘመር ብቻም አይደለም ተማሩበት ለሌሎችም አስተምሩት ዘማሪውና መጋቢው እንደዘመረልን አንዳንድ የምናልፍባቸው የማይመቹ የሚመስሉ የሕመም መንገዶች ፈቅደን ሳይሆን ሳንፈቅድና ግድም ሆኖብን ድምጹን ወደ መስማት የምንመጣበት ብሎም የምንማርበት መንገዶች ናቸው ከጌታ ለመማር በማንፈቅድበትና የመማርያ ጊዜም ሙሉ በሙሉ በምናጣበት ሰዓት እነዚህ ነገሮች የግድ በሕይወታችን ይሆናሉ
በሆሴዕ መጽሐፍ ላይ ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ ይለናል ትንቢተ ሆሴዕ 2 ፥ 16 ያን ጊዜ ነው እንግዲህ ለነፍሳችን መጎብኘትና መጽናናት የሚመጣው ከዚያ ውጪ ግን መጽናናት የሚባል ነገር ከቶ የማይታሰብ ነውና ብንፈልግም አናገኝም በዚህ አጋጣሚ እንግዲህ ስለዚህ የተባረከው አስተማሪ ስለሆነው መዝሙሩ ወንድማችንን ጌታ አብዝቶ ይባርከው ለማለት እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር ጆሮ ከፍቶ እንደሚናገር በትንቢተ ኢሳይያስ 50 ፥ 4 _ 9 መመልከት እንችላለን እንግዲህ የቃሉ ተማሪ በምንሆንበት ጊዜ በመጀመርያ ማድረግ የሚገባን ማስታወሻ መውሰድ ነው ይህ የሚረዳው ቁልፍ ሃሳቦችን ፣ ተገናኝ የሆኑ ጽሑፎችን ለማስታወስ ነው አንዳንድ ሰዎች በቁልፍ ሃሳቦች ላይ ማስመርን ይጠቀማሉ ይህም የሚረዳው ዋና ዋና ሃሳቦችን ይበልጥ ለመረዳት ነው በመሆኑም በማንኛውም የክፍል ትምህርት ሙሉ እርዳታን ይሰጣል ማስታወሻ በምንወስድበት ጊዜ በቂ መረጃን እናገኝበታለን በእንዲህ ዓይነት መንገድ የእግዚአብሔርን የቃሉን እውነት በምንከታተልበት ጊዜ እውነተኛ የሆነ የደቀ መዝሙር ሕይወት እንይዛለን በማቴዎስ ወንጌል 28 ፥ 19 _ 20 ላይ መጽሐፍቅዱሳችን እንዲህ በማለት ይናገራል እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ እንግዲህ ሰዎችን እያጠመቅን ጌታ ያዘዘንንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማርን ደቀመዛሙርት ስናደርግ እንዲሁ ሊሆን አይገባን የተማሩትን በትክክል እንዲይዙ የማስታወሻ ደብተር እንዲኖራቸውና ማስታወሻም እንዲጽፉ ልናደርጋቸው ይገባል ይህን ስናደርግ ነው እንግዲህ ሰዎችን የተማሩትን የሚጠብቁ እውነተኛ የጌታ ደቀመዛሙርት የምናደርጋቸው የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብና ለማጥናት ኃይልን አጠናክሮ ትልቅ ጥረት ማድረግ መጽሐፍቅዱስ የሚነግረንና የሚደግፈው አጠቃላይ የሕይወታችን መመርያ ነው ታድያ ይህንን መመርያ በሕይወታችን የምንተረጉም የተማርነውንም በማስታወሻ ደብተራችን ለመጻፍ ለማጥናት ለማሰላሰል ሰፊ ጊዜ የምንሰጥ እና ማስታወሻ ደብተሩም ያለን ስንሆን ነው ታድያ ይህን የምናደርግ ስንቶች እንሆን ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢዎች እተዋለሁ በመጽሐፈ መክብብ 9 ፥ 10 ላይ አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ ይለናል ስለዚህ ማወቅም ሆነ ጥበብ ማግኘት ካለብን እጃችንም ለማድረግ የምናገኘውን ሁሉ እንደ ኃይላችን ማድረግ የምንችለው አሁን ነው
With the right approach strive to become a
dedicated student of the word of God it is a matter of applying what you learn
ጌታ ይባርካችሁ
No comments:
Post a Comment