Monday 2 April 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 5 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነን የውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ማርያምን መካከለኛ ሊያደርጉ የፈለጉ ሰዎች ድንግል ማርያም ሰው ከመሆንዋ የተነሣ ከዳዊት ወገን ለሆነው ለዮሴፍ የታጨች ድንግል ሆና ሳለ የማርያም የክብርዋ ገናናነት ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን በማለትና የተለየች ፍጡር በማድረግ ማርያም ብሂል መርህ ለመንግሥተ ሰማያት ማርያም ማለት መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው ሊሉን ወደዱ መንግሥተ ሰማያት ሊያስገባን መንገዱን በደሙ የመረቀልን በሩንም የከፈተልን ብቸኛው መንገዳችን እና እውነታችን ግን ኢየሱስ ነው ነገር ግን ይሄ እውነት ለነዚህ ሰዎች የማይዋጥላቸው በመሆኑ አሁንም ከኢየሱስ ይልቅ ማርያምን ወደው በማርያም መሠላልነት ተሸጋግረው ወደ መንግሥቱ ሊገቡ ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሠላላችን ማርያም ሆይ ለምኚልን አሉ እንደገናም ይህቺው ማርያም አርጋለች በማለት የተአምረ ማርያምን መጽሐፍ ጠቅሰው አክብርዋ ለማርያም ከመ ትንሣኤ ወልዳ አሉን ወደ አማርኛው ስተረጉመው የማርያምን ትንሣኤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ አድርጋችሁ አክብሩ ማለታቸው ነው ነገር ግን ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሠላላችን ለማርያምም ሳይቀር የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ብቻ ነው እርሱ በትንሣኤውም ሆነ በእርገቱ ብቸኛ እና በኩር ነው ለምን ስንል ኢየሱስ የሞተው ለኃጢአታችን ነው ከሞት ሲነሳና ወደ ሰማይ ሲያርግ ደግሞ እኛን ስለማጽደቅ የተነሣና ያረገ ነው ስለዚህ ሞቱን ትንሣኤውንም ሆነ እርገቱን ሊመስል የሚችልም ሆነ የሚወዳደር የለም ወደ ዛሬው ትምህርት ስንገባ ደግሞ ማርያምን መካከለኛ ለማድረግ ያላፈሩ ሰዎች ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ፣ ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሠላልና የመሣሠሉትን በማለት ሳያባሩ ማርያም መካከለኛችን ስለሆነች ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ አሉን ወደ አማርኛው ሲተረጐም የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነን የሚል ትርጉም የሚሰጠን ነው ኢየሱስ ግን ሊቆጣንና ሊያጠፋን የመጣ ጌታ ሆኖ የማርያም ምልጃና ልመና የሚያስፈልገው አይደለም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን 1ኛ ) ኢየሱስ በዘብዴዎስ ልጆች ቁጣና በሰማርያ ሕዝቦች ላይ ባቀረቡት የእሳት ይውረድ ጥያቄ ባለመስማማት የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ የመጣ አለመሆኑን በመናገር የዘብዴዎስን ልጆች ገሠጸ የሉቃስ ወንጌል 9 ፥ 51 _ 57 2ኛ ) በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ላይ ለተጻፈላት ሴት በተወሰደ እርምጃ ባለመስማማት ኢየሱስ ከእናንተ ኃጢአት የሌለባት ይውገራት ማለቱና ሴቲቱንም ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ እኔም አልፈርድብሽም በማለት ሴቲቱን በሰላም አሰናበተ ዮሐንስ ወንጌል 8 ፥ 1 _ 11 3ኛ ) ኢየሱስ በእኛ ላይ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቊጣ ተቀበለ እንጂ የውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነን ሲል እንደተናገረው የተቆጣና ከቁጣውም ለመመለስ ሲል የማርያምን ምልጃና ጸሎትዋንም የጠየቀ አልነበረም ( ትንቢተ ኢሳይያስ 53 በሙሉ ፣ 1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 22 _ 25 ፣ ሮሜ 9 ፥ 22 _ 23 ) 4ኛ ) ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርስ ወዶ ይታገሳል 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 9 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 12 _ 16 ፤ ሮሜ 2 ፥ 14 5ኛ ) ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔርም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት እንጂ ለቁጣ አልመረጠንም ( 1ኛ ተሰሎንቄ 5 ፥ 9 ) 6ኛ ) ነገር ግን እኛ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን በሥጋ ምኞት በፊት እንኖር ነበር እንደ ሌሎችም ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን ( ኤፌሶን 2 ፥ 3 ) 7ኛ ) በልጁ ስናምን ግን የዘላለም ሕይወት ይኖረናል በልጁ የማናምን ከሆነ ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በእኛ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አናይም ( ዮሐንስ ወንጌል 3 ፥ 36 ) 8ኛ ) ለሕያውና እውነተኛውን አምላክ ለማገልገል ከሙታን ያስነሣውን ልጁን እርሱን ኢየሱስን ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነንን ለመጠበቅ ከልዩ ልዩ ነገር ዘወር ማለት እንደሚገባን ቃሉ ይነግረናል ( የማቴዎስ ወንጌል 3 ፥ 7 ፤ የሉቃስ ወንጌል 3 ፥ 7 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 1 ፥ 9 እና 10 ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ ነው ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ለተጨማሪ መረጃ በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት አዳምጡ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com


No comments:

Post a Comment