Friday 6 October 2017












ፈጣን ተሐድሶ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን


የትምህርት ርዕስ



መንፈሳዊ የሕይወት ተሃዶሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ




ሰኞ ማለዳ 10 ሰዓት ላይ የሚጀምር ለኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችና ለወንጌላውያን አማኞች እንዲሁም አገልጋዮቻቸውም ጭምር   የሚሰጥ ትምህርት ነው ከዚህም ሌላ ይህንን ትምህርት በናፍቆት ሊከታተሉ ለሚወዱ ሁሉ ተዘጋጅቶ የቀረበ በመሆኑ ማንም ሰው ሊከታተለውና ሊሰማው የሚያስፈልገው ለተከታታይ ሳምንታት የሚሰጥ ተከታታይ ትምህርት ነው



የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን እስካሁን ድረስ ከዚህ አገልግሎት ጋር ቆማችሁ የዚህ አገልግሎት ተካፋዮች እና ተጠቃሚዎች ስለሆናችሁ እንደገናም ለዚህ አገልግሎት መሳካት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ስላደረጋችሁ ጌታ አምላክ ዘመናችሁን ይባርክ እያልኩ ሰኞ በሚኖረን የፌስቡክ ላይቭ አገልግሎት እንደተነጋገርነው አዲስ ትምህርት የምንጀምርበት ጊዜ ነው መንፈሳዊ የሕይወት ተሃዶሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ምን እንደሚመስል ከመጽሐፍቅዱሳችን አስረጂ በማቅረብ በተለይም መንፈሳዊ ተሃድሶን በሰዎች ሕይወት ላይም ሆነ በቤተክርስቲያን ያመጡ ሰዎችን ከመጽሐፍቅዱሳችን እንመለከታቸዋለን እንደገናም በዚህ ውስጥ ቤተክርስቲያን ምን ትምሰል ? የሚል መጠይቅን ይዘን እንቀርባለን ከዚህም ሌላ ተሃድሶ በኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን መቼ ተጀመረ ?ቤተክርስቲያኒቱም ክርስትናን አንድ ብላ ከተቀበለችበትና ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የነበራት መንፈሳዊ አቋምና መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ምን እንደነበረ እንመለከታለን እንደገናም ከዚህ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል መረዳቷ የቱ ጋር እንደወጣችና እንደለቀቀች ከታሪክም ሆነ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት አጣቅሰን መረጃም ሰብስበን እንመለከታለን የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ ሰፋ ያሉ እውነቶችንና የእግዚአብሔር ቃል መረዳቶችን ይዞ የቀረበ ስለሆነ እናንተም ሰፋ ብላችሁና ማስታወሻ ደብተሮቻችሁንም አዘጋጅታችሁ ተዘጋጅታችሁ ሰዎችንም ወደዚሁ የትምህርት ፕሮግራም በሰዓቱ ተገኝተው እንዲካፈሉ ጋብዟቸው ትምህርቱ እንደሚታወቀውበፌስቡክ ላይቭ የሚጀምረው በእኔ የሰዓት አቆጣጠር 10 AM ማለዳ ላይ ነው ሁልጊዜ ሰኞና ሐሙስ በዚህ ሰዓት ተዘጋጅቶ ይቀርብላችኋል በተረፈ በክርስቶስ ፍቅር በጣም እወዳችኋለሁ አከብራችኋላሁ ዘመናችሁ የተባረከ ይሁን በሰዓታችንና በቀጠሯችንም እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ በማለት የምሰናበታችሁ

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

God bless u all



yonasasfaw8@gmail.com

ፈጣን ተሐድሶ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

 ለዚህ ሥዕላዊ መጠይቅ መጽሐፍቅዱሳዊ መልሳችን

ተሐድሶ ያስፈልገኛል ስትል ወንጌልን አምና የተቀበለች ቤተክርስቲያን በአዲስ ፍጥረት ማንነት ትታደሳለች እንጂ አትጠፋም 

2ኛ ቆሮንቶስ 5፥ 17 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 ፤ የያዕቆብ መልዕክት 1 ፥ 18 እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል ይመልከቱ 


Down arow.png






Image result for መንፈሳዊ ተሐድሶ

No comments:

Post a Comment