Tuesday 24 October 2017

የትምህርት ርዕስ :--- መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ የትምህርት ርዕስ መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን 1ኛ )መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ በሚለው ዋና አርዕስት ዙርያ ፦ ሀ ) ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው ? ለ ) ተሃድሶ እንዲመጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንና ምን ናቸው ? ሐ ) በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ ተሃድሶን ካመጡ ሰዎች አንዱ ነህምያ ነውና ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች አንጻር የነህምያን ሕይወት ስንቃኝ ምን እንደሚመስል 2ኛ ) የተሃድሶ ተግዳሮቶች በሚለው ንዑስ አርዕስት ዙርያ ደግሞ ለተሃድሶ ሲንቀሳቀስ ነህምያ የገጠመው ተግዳሮቶች እንደሚከተለው የቀረበ በመሆኑ ምን ምን እንደሆነ ሀ ) የተቃዋሚዎች የንቀት ሳቅ ( ነህምያ 2 ፥ 19 ) ለ ) በብስጭት በመነሳት በአይሁድ ላይ ማላገጥና መቀለድ ( ነህምያ 4 ፥ 6 ) ሐ ) በእስራኤላውያን መካከል የተነሣው የውስጥ ችግር እና ተሃድሶን ሊገቱ የቻሉ በቅዱሳን መካከል የተነሡ አለመግባባቶች ፣ ጸቦች ፣ ሽኩቻዎችና ራስ ተኮር አካሄዶች መ) ቀጣዩ እስትራቴጂ እስራኤልን ለመውጋትና ለማሸበር መማማል ( ነህምያ 4 ፥ 8 ) የሚሉት ናቸው አሁን ያለነው እዚህኛው ሃሳብ ላይ ነው በሚቀጥሉት ክፍለ ጊዜያቶች ነህምያ የገጠሙትን ተግዳሮቶች ማለትም ሽንገላዎችንና ነህምያን ለማሳሳት የተላኩ ሃሰተኛ ነቢያትን እንመለከታቸዋለን ውድ ወገኖቼ ሆይ ትምህርቱ ሰፋ ያሉ ሃሳቦችን የያይዘ ስለሆነ በአጭሩ የምቋጨው አይደለምና በሰፊው የሚቀጥል ነው ስለዚህ ብትችሉ የማስታወሻ ደብተሮቻችሁን እያዘጋጃችሁ ብትመጡና ከትምህርቱ የምታገኙትን ጠቃሚ ነጥቦች ብትጽፉ የበለጠ ትጠቀማላችሁ በማለት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ውድ ወገኖቼ አሁንም በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰግን የማላልፈው ነገር ቢኖር የዛሬውን እንዲህ በፓወር ፖይንት( Power Point ) ተቀናብሮ የተወደደችዋ የዘማሪት ዘርፌ ከበደ መዝሙርም ገብቶበት የተሰራውን የቪዲዮ ማስታወቅያ ከጥሩ ዝግጅት ጋር አቀናብሮ የሠራልኝ የተወደደው ወንድማችን የእግዚአብሔር ባርያ የሆነው አዳነ ግርማ ነው ይህ ወንድማችን በሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በትጋት የሚያገለግል የጌታ ባርያ ሲሆን በዚሁ ኅብረት ውስጥ ያለውን የቴሌ ኮንፍረንሱን በበላይነት የሚመራና ወደ ኅብረቱ የሚመጡትን አገልጋዮች በመጋበዝ ማስታወቅያዎችን ልክ አሁን ለእኔ በሠራልኝ ማስታወቅያ ዓይነት እየሠራና እያዘጋጀ በዓማኑኤል ኅብረት የፌስቡክ ድኅረ ገጽ ላይ በመለጠፍ ኅብረቱን በዚሁ የቴሌ ኮንፍራንስ አገልግሎት የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያወቅርና የሚጠቅም ከዚህም ሌላ የኅብረቱ የቦርድ አባል በመሆን የሚሰራ ታማኝ የጌታ ባርያ ነው በመሆኑም ከዚህ ከእኔ የሚኒስትሪ አገልግሎት ጎን በመሆንም ብዙውን በሥዕልና በቪዲዮ የተደገፉ ማስታወቅያዎችን እስከ አሁን ድረስ በአስገራሚ ሁኔታ የሚሠራልኝ ይኸው ወንድም ነው ስለዚህ ወገኖች ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይህንን ወንድም እንድትባርኩት በአገልግሎቱም ይበልጥ እንዲተጋና ወደፊት እንዲዘረጋ እንድታበረታቱት እንድትጸልዩለትም ለማሳሰብ እወዳለሁ እንደገናም በዚህ አጋጣሚ እኔም ላሳስባችሁ የምፈልገው አንድ ነገር ብትችሉ በዚሁ በሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ በሚኖረው የቴሌ ኮንፍራንስ አገልግሎት ላይ በመስመሩ እየገባችሁ የፕሮግራሙ ተካፋዮች ብትሆኑ የበለጠ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ አገልግሎቱም በተለያዩ እንግዳ ተገባዥ አገልጋዮችና የኅብረቱም አገልጋዮች ጭምር የሚሰጥ ስለሆነ ትልቅ የበረከት ጊዜና በጣምም አስደናቂ ነው እንደገናም ይኸው የሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን የጸሎት አገልጋዮችም ሆኑ የኅብረቱ ዋና መጋቢና የሰሜን አሜሪካ ዓማኑኤል ኅብረት ፕሬዘዳንት የሆነው የተባረከው ወንድማችን መጋቢ ሰሎሞን አደፍርስ ለዚህ ሚኒስትሪ የጀርባ አጥንት ሆነው በመጸለይ እና ከጎኔም በመቆም ይህንኑ አገልግሎት በሚችሉት መጠን እየደገፉ ይገኛሉ እነዚህንም ወገኖች እንድትባርኳቸው እፈለጋለሁ ትምህርቱም እንግዲህ በየሳምንቱ በዚህ መልኩ ይቀጥላል ታማኝ ሆናችሁ በሰዓታችሁ ተገኙ ሰዎችንም መጋበዝ አትርሱ በተረፈ በጌታ ፍቅር በጣም አድርጌ የምወዳችሁና የማከብራችሁ አገልጋያችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment