Wednesday 25 October 2017

የትምህርት ርዕስ :------- መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ የትምህርት ርዕስ መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን 1ኛ )መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ በሚለው ዋና አርዕስት ዙርያ ፦ ሀ ) ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው ? ለ ) ተሃድሶ እንዲመጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንና ምን ናቸው ? ሐ ) በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ ተሃድሶን ካመጡ ሰዎች አንዱ ነህምያ ነውና ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች አንጻር የነህምያን ሕይወት ስንቃኝ ምን እንደሚመስል 2ኛ ) የተሃድሶ ተግዳሮቶች በሚለው ንዑስ አርዕስት ዙርያ ደግሞ ለተሃድሶ ሲንቀሳቀስ ነህምያ የገጠመው ተግዳሮቶች እንደሚከተለው የቀረበ በመሆኑ ምን ምን እንደሆነ ሀ ) የተቃዋሚዎች የንቀት ሳቅ ( ነህምያ 2 ፥ 19 ) ለ ) በብስጭት በመነሳት በአይሁድ ላይ ማላገጥና መቀለድ ( ነህምያ 4 ፥ 6 ) ሐ ) በእስራኤላውያን መካከል የተነሣው የውስጥ ችግር እና ተሃድሶን ሊገቱ የቻሉ በቅዱሳን መካከል የተነሡ አለመግባባቶች ፣ ጸቦች ፣ ሽኩቻዎችና ራስ ተኮር አካሄዶች መ) ቀጣዩ እስትራቴጂ እስራኤልን ለመውጋትና ለማሸበር መማማል ( ነህምያ 4 ፥ 8 ) የሚሉት ናቸው አሁን ያለነው እዚህኛው ሃሳብ ላይ ነው በሚቀጥሉት ክፍለ ጊዜያቶች ነህምያ የገጠሙትን ተግዳሮቶች ማለትም ሽንገላዎችንና ነህምያን ለማሳሳት የተላኩ ሃሰተኛ ነቢያትን እንመለከታቸዋለን ውድ ወገኖቼ ሆይ ትምህርቱ ሰፋ ያሉ ሃሳቦችን የያይዘ ስለሆነ በአጭሩ የምቋጨው አይደለምና በሰፊው የሚቀጥል ነው ስለዚህ ብትችሉ የማስታወሻ ደብተሮቻችሁን እያዘጋጃችሁ ብትመጡና ከትምህርቱ የምታገኙትን ጠቃሚ ነጥቦች ብትጽፉ የበለጠ ትጠቀማላችሁ በማለት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ውድ ወገኖቼ አሁንም በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰግን የማላልፈው ነገር ቢኖር የዛሬውን እንዲህ በፓወር ፖይንት( Power Point ) ተቀናብሮ የተወደደችዋ የዘማሪት ዘርፌ ከበደ መዝሙርም ገብቶበት የተሰራውን የቪዲዮ ማስታወቅያ ከጥሩ ዝግጅት ጋር አቀናብሮ የሠራልኝ የተወደደው ወንድማችን የእግዚአብሔር ባርያ የሆነው አዳነ ግርማ ነው ይህ ወንድማችን በሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በትጋት የሚያገለግል የጌታ ባርያ ሲሆን በዚሁ ኅብረት ውስጥ ያለውን የቴሌ ኮንፍረንሱን በበላይነት የሚመራና ወደ ኅብረቱ የሚመጡትን አገልጋዮች በመጋበዝ ማስታወቅያዎችን ልክ አሁን ለእኔ በሠራልኝ ማስታወቅያ ዓይነት እየሠራና እያዘጋጀ በዓማኑኤል ኅብረት የፌስቡክ ድኅረ ገጽ ላይ በመለጠፍ ኅብረቱን በዚሁ የቴሌ ኮንፍራንስ አገልግሎት የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያወቅርና የሚጠቅም ከዚህም ሌላ የኅብረቱ የቦርድ አባል በመሆን የሚሰራ ታማኝ የጌታ ባርያ ነው በመሆኑም ከዚህ ከእኔ የሚኒስትሪ አገልግሎት ጎን በመሆንም ብዙውን በሥዕልና በቪዲዮ የተደገፉ ማስታወቅያዎችን እስከ አሁን ድረስ በአስገራሚ ሁኔታ የሚሠራልኝ ይኸው ወንድም ነው ስለዚህ ወገኖች ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይህንን ወንድም እንድትባርኩት በአገልግሎቱም ይበልጥ እንዲተጋና ወደፊት እንዲዘረጋ እንድታበረታቱት እንድትጸልዩለትም ለማሳሰብ እወዳለሁ እንደገናም በዚህ አጋጣሚ እኔም ላሳስባችሁ የምፈልገው አንድ ነገር ብትችሉ በዚሁ በሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ በሚኖረው የቴሌ ኮንፍራንስ አገልግሎት ላይ በመስመሩ እየገባችሁ የፕሮግራሙ ተካፋዮች ብትሆኑ የበለጠ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ አገልግሎቱም በተለያዩ እንግዳ ተገባዥ አገልጋዮችና የኅብረቱም አገልጋዮች ጭምር የሚሰጥ ስለሆነ ትልቅ የበረከት ጊዜና በጣምም አስደናቂ ነው እንደገናም ይኸው የሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን የጸሎት አገልጋዮችም ሆኑ የኅብረቱ ዋና መጋቢና የሰሜን አሜሪካ ዓማኑኤል ኅብረት ፕሬዘዳንት የሆነው የተባረከው ወንድማችን መጋቢ ሰሎሞን አደፍርስ ለዚህ ሚኒስትሪ የጀርባ አጥንት ሆነው በመጸለይ እና ከጎኔም በመቆም ይህንኑ አገልግሎት በሚችሉት መጠን እየደገፉ ይገኛሉ እነዚህንም ወገኖች እንድትባርኳቸው እፈለጋለሁ ትምህርቱም እንግዲህ በየሳምንቱ በዚህ መልኩ ይቀጥላል ታማኝ ሆናችሁ በሰዓታችሁ ተገኙ ሰዎችንም መጋበዝ አትርሱ በተረፈ በጌታ ፍቅር በጣም አድርጌ የምወዳችሁና የማከብራችሁ አገልጋያችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Tuesday 24 October 2017

የትምህርት ርዕስ :--- መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ የትምህርት ርዕስ መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን 1ኛ )መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ በሚለው ዋና አርዕስት ዙርያ ፦ ሀ ) ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው ? ለ ) ተሃድሶ እንዲመጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንና ምን ናቸው ? ሐ ) በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ ተሃድሶን ካመጡ ሰዎች አንዱ ነህምያ ነውና ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች አንጻር የነህምያን ሕይወት ስንቃኝ ምን እንደሚመስል 2ኛ ) የተሃድሶ ተግዳሮቶች በሚለው ንዑስ አርዕስት ዙርያ ደግሞ ለተሃድሶ ሲንቀሳቀስ ነህምያ የገጠመው ተግዳሮቶች እንደሚከተለው የቀረበ በመሆኑ ምን ምን እንደሆነ ሀ ) የተቃዋሚዎች የንቀት ሳቅ ( ነህምያ 2 ፥ 19 ) ለ ) በብስጭት በመነሳት በአይሁድ ላይ ማላገጥና መቀለድ ( ነህምያ 4 ፥ 6 ) ሐ ) በእስራኤላውያን መካከል የተነሣው የውስጥ ችግር እና ተሃድሶን ሊገቱ የቻሉ በቅዱሳን መካከል የተነሡ አለመግባባቶች ፣ ጸቦች ፣ ሽኩቻዎችና ራስ ተኮር አካሄዶች መ) ቀጣዩ እስትራቴጂ እስራኤልን ለመውጋትና ለማሸበር መማማል ( ነህምያ 4 ፥ 8 ) የሚሉት ናቸው አሁን ያለነው እዚህኛው ሃሳብ ላይ ነው በሚቀጥሉት ክፍለ ጊዜያቶች ነህምያ የገጠሙትን ተግዳሮቶች ማለትም ሽንገላዎችንና ነህምያን ለማሳሳት የተላኩ ሃሰተኛ ነቢያትን እንመለከታቸዋለን ውድ ወገኖቼ ሆይ ትምህርቱ ሰፋ ያሉ ሃሳቦችን የያይዘ ስለሆነ በአጭሩ የምቋጨው አይደለምና በሰፊው የሚቀጥል ነው ስለዚህ ብትችሉ የማስታወሻ ደብተሮቻችሁን እያዘጋጃችሁ ብትመጡና ከትምህርቱ የምታገኙትን ጠቃሚ ነጥቦች ብትጽፉ የበለጠ ትጠቀማላችሁ በማለት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ውድ ወገኖቼ አሁንም በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰግን የማላልፈው ነገር ቢኖር የዛሬውን እንዲህ በፓወር ፖይንት( Power Point ) ተቀናብሮ የተወደደችዋ የዘማሪት ዘርፌ ከበደ መዝሙርም ገብቶበት የተሰራውን የቪዲዮ ማስታወቅያ ከጥሩ ዝግጅት ጋር አቀናብሮ የሠራልኝ የተወደደው ወንድማችን የእግዚአብሔር ባርያ የሆነው አዳነ ግርማ ነው ይህ ወንድማችን በሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በትጋት የሚያገለግል የጌታ ባርያ ሲሆን በዚሁ ኅብረት ውስጥ ያለውን የቴሌ ኮንፍረንሱን በበላይነት የሚመራና ወደ ኅብረቱ የሚመጡትን አገልጋዮች በመጋበዝ ማስታወቅያዎችን ልክ አሁን ለእኔ በሠራልኝ ማስታወቅያ ዓይነት እየሠራና እያዘጋጀ በዓማኑኤል ኅብረት የፌስቡክ ድኅረ ገጽ ላይ በመለጠፍ ኅብረቱን በዚሁ የቴሌ ኮንፍራንስ አገልግሎት የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያወቅርና የሚጠቅም ከዚህም ሌላ የኅብረቱ የቦርድ አባል በመሆን የሚሰራ ታማኝ የጌታ ባርያ ነው በመሆኑም ከዚህ ከእኔ የሚኒስትሪ አገልግሎት ጎን በመሆንም ብዙውን በሥዕልና በቪዲዮ የተደገፉ ማስታወቅያዎችን እስከ አሁን ድረስ በአስገራሚ ሁኔታ የሚሠራልኝ ይኸው ወንድም ነው ስለዚህ ወገኖች ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይህንን ወንድም እንድትባርኩት በአገልግሎቱም ይበልጥ እንዲተጋና ወደፊት እንዲዘረጋ እንድታበረታቱት እንድትጸልዩለትም ለማሳሰብ እወዳለሁ እንደገናም በዚህ አጋጣሚ እኔም ላሳስባችሁ የምፈልገው አንድ ነገር ብትችሉ በዚሁ በሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ በሚኖረው የቴሌ ኮንፍራንስ አገልግሎት ላይ በመስመሩ እየገባችሁ የፕሮግራሙ ተካፋዮች ብትሆኑ የበለጠ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ አገልግሎቱም በተለያዩ እንግዳ ተገባዥ አገልጋዮችና የኅብረቱም አገልጋዮች ጭምር የሚሰጥ ስለሆነ ትልቅ የበረከት ጊዜና በጣምም አስደናቂ ነው እንደገናም ይኸው የሰሜን አሜሪካ የዓማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን የጸሎት አገልጋዮችም ሆኑ የኅብረቱ ዋና መጋቢና የሰሜን አሜሪካ ዓማኑኤል ኅብረት ፕሬዘዳንት የሆነው የተባረከው ወንድማችን መጋቢ ሰሎሞን አደፍርስ ለዚህ ሚኒስትሪ የጀርባ አጥንት ሆነው በመጸለይ እና ከጎኔም በመቆም ይህንኑ አገልግሎት በሚችሉት መጠን እየደገፉ ይገኛሉ እነዚህንም ወገኖች እንድትባርኳቸው እፈለጋለሁ ትምህርቱም እንግዲህ በየሳምንቱ በዚህ መልኩ ይቀጥላል ታማኝ ሆናችሁ በሰዓታችሁ ተገኙ ሰዎችንም መጋበዝ አትርሱ በተረፈ በጌታ ፍቅር በጣም አድርጌ የምወዳችሁና የማከብራችሁ አገልጋያችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

የትምህርት ርዕስ :--- መንፈሳዊ የሕይወት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ

Sunday 8 October 2017

የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር ፫የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር ፫ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ? የሚለው የክፍል አስራ ስምንት እና የቊጥር 3 ትምህርትን እንደሚከተለው አቀርባለሁ መጽሐፍቅዱሳችን አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም ነው የሚለን ዘፍጥረት 5 ፥ 5 በመሆኑም ከአዳም ሞት በኋላ የሴት ቤተሰብ ከቃየን ቤተሰብ ጋር ፈጥኖ የተለየ መሆኑን የአረብኛ የመጽሐፍቅዱስ መተርጉማን ተናግረዋል እነዚሁ መተርጉማን አያይዘው ሲናገሩ ሴት ልጆቹንና የልጆቹን ሚስቶች ይዞ ከፍ ወዳለው ተራራ ሔርሞን ወደ ተባለው አዳም ወደተቀበረበት ተራራ ሲሄድ ቃየን ደግሞ ልጆቹን ይዞ በሸለቆ ስር መኖር ጀመረ አቤልም ሲመለከት ንጹሕና ቅዱስ ተራራ አገኘ መላዕክት ድምጹን ሊሰሙት ቅርብ የሆኑበት ከመንፈሳዊ መዝሙሩም ጋር ሊገናኙ የሚያስችላቸው ቦታ ነበር ታድያ ልጆቹና የልጆቹ ሚስቶች በእግዚአብሔር ስም ወደሚጠሩበት ቦታ እንዲመጡ ፓትርያርክ ሴት ለምኗቸው ነበር እንደገናም ማንም ሰው ቃየንን ለማግኘት ከዚያ ተራራ የሚወርድ አልነበረም ነገር ግን ያም ቢሆን ጥቂቶች ከተራራው ወረዱ የቃየንን ቆነጃጅት ልጆች የልጅ ልጆቹን ወሰዷቸው እነርሱንም ተከተሏቸው የመረጧቸውንም ለሚስትነት ወሰዷቸው በጉልበት ግን አልነበረም ሕገወጥ በሆነ መንገድም ተጋቡ ማራኪና መልከ መልካም የሆኑትን ለሥጋቸው የሚያስደስታቸውን ያለ ምንም ምግባርና ጠባይ ያለ ምክርና የቤተሰብ ፈቃድ ያለ እግዚአብሔር ምክር ያስደሰቷቸውን ሴቶች ወሰዱ ቃየን ሱሰኛ በሆነበት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ዓይነት ሳይጋቡ ፈጸሙ በመዝፈንና በመደነስ ጊዜአቸውን አጠፉ የሴት ዝርያዎች ወይም የእግዚአብሔር ልጆች ቆሻሻ የሆነው ስሜታቸው ምንድነው ? ስንል ወርደው የቃየንን ልጆች ተገናኟቸው ዝሙትንም ከእነርሱ ፈጸሙ ይለናል እንግዲህ የኤሎሂም ልጆች ዝነኛ የሆኑ የመንግሥተ ሰማያት ሰዎችና የሴት ቤተሰቦች ናቸው ታድያ የሴት ልጆች ጊዜ ወስደው የውሃው ጎርፍ ሊመጣ ባለበት ሰዓት ከቃየን ልጆች ጋር ተጋቡ የመጽሐፍቅዱሱም ጥቅስ ከዚህ የተነሳ የተጠቀሰ ነው የማቴዎስ ወንጌል 24 ፥ 38 ፤ የሉቃስ ወንጌል 17 ፥ 27 እንደገናም ጋብቻን የሚከለክል የሚያግድ ትዕዛዝ እያለ በጋብቻ ተቀላቀሉ ዘጸአት 34 ፥ 16 ፤ ዘፍጥረት 26 ፥ 34 እና 35 ፤ ዘፍጥረት 27 ፥ 46 ፤ ዘፍጥረት 28 ፥ 1 ን እንመልከት በዘጸአት 6 ፥ 2 ላይ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ ይለናል በዘጸአት 6 ፥ 4 ላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በድሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ ይለናል ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሰውን ሴቶች ልጆች ለራሳቸው ወስደው ያገቡት እግዚአብሔር ፈቅዶላቸውና ሴቶቹንም አጥንቶቻችሁና ሥጋዎቻችሁ ናቸው ብሎ ሰጥቷቸው ሳይሆን በዓይኖቻቸው ፊት መልካሞች እንደሆኑ አይተዋቸው መርጠዋቸውም ነው ይህ ዕይታና ምርጫ ደግሞ ቃየላዊ የሆነ ሚስትን የማየትና የመምረጥ ዕይታና ምርጫ ነው በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ቃየል ብቻ ሳይሆን የቃየል ዘሮችም ናቸው በዚሁ መንገድ ሚስቶቻቸውን መርጠው ያገቡት ይህ መንገድ ታድያ በዓይን አምሮት የተፈጸመ የጋብቻ ሥርዓት ስለሆነ እግዚአብሔር በዚህ ነገር የለበትም ይህንንም መንገድ ለጋብቻ አልተጠቀመም ደግሞም ሰዎች ይህንኑ የዓይን አምሮት መንገድ ተከትለው እንዲጋቡ አላመለከተም ወገኖቼ ሆይ ሰዎች በዚህ በዓይን አምሮት መንገድ ተጋብተው ልጅ እስከ መውለድ ድረስ ደርሰው ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ ማለት ልጆችን የወለዱ በመሆናቸው ደርሰው የታወቁ ኃያላን ሆነዋልና ጋብቻው በዓይን አምሮት የተፈጸመ ቢሆንም እንኳ በቃ መጋባታቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንደገናም እግዚአብሔር አዋቂ ስለሆነ ጋብቻውም ትክክል ነው ስንል ድምዳሜ ላይ መድረስ የለብንም አንድ ሰው ያልተፈቀደለትን ሴት አግብቶ ልጆች ስለተወለዱለት የታወቀና ኃያል ሆነ ማለት ትዳሩም ሆነ ልጆቹ ከእግዚአብሔር የተገኙ ናቸው እርሱም የተባረከና በትክክለኛ መንገድ ላይ የለ ሰው ነው ማለት አንችልም የዚህን ሰው ትክክለኛነትና ኃያል መሆን የሚገልጹ የተወለዱለት ልጆች አይደሉም ማንም ሰው እኮ በተሳሳተም መንገድ አግብቶ ይሄ ሊሆንለት ይችላል ስለዚህ መለኪያዎቹ እነዚህ ሊሆኑ ይገባል ማለት የለብንም ይገባልም ስንል ማሰብ የለብንም ይገባል ሲሉ ማሰብም ሆነ ያሰቡትንም ነገር ትክክል ነው ሲሉ ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ደግሞ በዚህ የጋብቻ ሂደት ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሄዱበት መንገድ ምንም ዓይነት ይሁን ንስሐ የማያስፈልገው በመሆኑ ትክክል ናቸውና በዚያው ይቀጥሉበት ማለታችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይህ ብቻ አይደለም ሌሎችም ወደፊት በዚህ መንገድ መጥተው የሚጋቡ ቢኖሩ እንኳ የሚመጣባቸው ችግር የለም እያልን በመሆኑ ትውልድን ወደተሳሳተ መንገድ እየመራን ነውና አሁንም ከተጠያቂነት አንድንም እንዲህ ማድረጋችን ደግሞ ራሳችንንም ሆነ ሌላውን ማታለል የሆንብናልና ሌሎችም ንስሐ እንዲገቡ ተናግረን ራሳችንም ደግሞ በጊዜ ንስሐ ገብተን ትዳራችንን በዚሁ የንስሐ ሕይወት ካላስተካከልን በስተቀር ጋብቻን የሚከለክለውንና የሚያግደውን ትዕዛዝ ተላልፈን ልንጣመር ከማይገቡን ሰዎች ጋር ተጣምረን የተጋባን የተቀላቀልንም በመሆናችን ከዚህም ሌላ ሌሎችም መጥተውና በእኛው መንገድ ተጋብተው እንዲቀላቀሉ በማድረጋችን በፍጻሜው የምንከፍለው ዋጋ የከፋ ይሆናል ሚስትን መውሰድ በጠቅላላው የብሉይኪዳን ሕግ በእግዚአብሔርም የጋብቻ ግንኙነት ምሥረታ ሰዎች ስሜታቸውን በሚቀሰቅስ መንገድ ተነሳስተው በቀላሉ የውጫዊ ግንኙነት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረታቸውን የሚያደርጉበት ነው ይሁን እንጂ አሁንም እግዚአብሔር ይህንን መንገድ ለጋብቻ አልተጠቀመም ለዚህ ጉዳይ እነዚህን ጥቅሶች አሁንም ደግመን እንመልከታቸው ዘፍጥረት 26 ፥ 34 እና 35 ፤ ዘፍጥረት 27 ፥ 46 ፤ ዘፍጥረት 28 ፥ 1 ውድ ወገኖቼ ሆይ ለዚህ ትምህርት ማጠናከርያ እንዲሆን ከእንግሊዘኛው የመጽሐፍቅዱስ ኮመንታሪ የተወሰዱና በዚህም ትምህርት ውስጥ የተካተቱ ሃሳቦች ስላሉ ሃሳቡን በእንግሊዘኛውም አንብባችሁ መረዳት ለምትፈልጉ እንደሚከተለው ጽሑፉን አቅርቤላችኋለሁ አንብባችሁ ተባረኩበት Matthew Henry's Concise Commentary According to the Arabic writers (l), immediately after the death of Adam the family of Seth was separated from the family of Cain; Seth took his sons and their wives to a high mountain (Hermon), on the top of which Adam was buried, and Cain and all his sons lived in the valley beneath, where Abel was slain; and they on the mountain obtained a name for holiness and purity, and were so near the angels that they could hear their voices and join their hymns with them; and they, their wives and their children, went by the common name of the sons of God: and now these were adjured, by Seth and by succeeding patriarchs, by no means to go down from the mountain and join the Cainites; but notwithstanding in the times of Jared some did go down, it seems; See Gill on Genesis 5:20 and after that others, and at this time it became general; and being taken with the beauty of the daughters of Cain and his posterity, they did as follows: and they took them wives of all that they chose; not by force, as Aben Ezra and Ben Gersom interpret, for the Cainites being more numerous and powerful than they, it can hardly be thought that the one would attempt it, or the other suffer it; but they intermarried with them, which the Cainites might not be averse unto; they took to them wives as they fancied, which were pleasing to the flesh, without regard to their moral and civil character, and without the advice and consent of their parents, and without consulting God and his will in the matter; or they took women as they pleased, and were to their liking, and committed fornication, to which the Cainites were addicted; for they spent their time in singing and dancing, and in uncleanness, whereby the posterity of Seth or sons of God were allured to come down and join them, and commit fornication with them, as the Arabic writers (m) relate. Keil and Delitzsch Biblical Commentary on the Old Testament The question whether the "sons of Elohim" were celestial or terrestrial sons of God (angels or pious men of the family of Seth) can only be determined from the context, and from the substance of the passage itself, that is to say, from what is related respecting the conduct of the sons of God and its results. That the connection does not favour the idea of their being angels, is acknowledged even by those who adopt this view. "It cannot be denied," says Delitzsch, "that the connection of Genesis 6:1-8 with Genesis 4 necessitates the assumption, that such intermarriages (of the Sethite and Cainite families) did take place about the time of the flood (cf. Matthew 24:38; Luke 17:27); and the prohibition of mixed marriages under the law (Exodus 34:16; cf. Genesis 27:46; Genesis 28:1.) also favours the same idea." But this "assumption" is placed beyond all doubt, by what is here related of the sons of God. In Genesis 6:2 it is stated that "the sons of God saw the daughters of men, that they were fair; and they took them wives of all which they chose," i.e., of any with whose beauty they were charmed; and these wives bare children to them (Genesis 6:4). Now אשּׁה לקח (to take a wife) is a standing expression throughout the whole of the Old Testament for the marriage relation established by God at the creation, and is never applied to πορνεία, or the simple act of physical connection. ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Friday 6 October 2017

ፈጣን ተሐድሶ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የትምህርት ርዕስ

መንፈሳዊ የሕይወት ተሃዶሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ

ሰኞ ማለዳ 10 ሰዓት ላይ የሚጀምር ለኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችና ለወንጌላውያን አማኞች እንዲሁም አገልጋዮቻቸውም ጭምር   የሚሰጥ ትምህርት ነው ከዚህም ሌላ ይህንን ትምህርት በናፍቆት ሊከታተሉ ለሚወዱ ሁሉ ተዘጋጅቶ የቀረበ በመሆኑ ማንም ሰው ሊከታተለውና ሊሰማው የሚያስፈልገው ለተከታታይ ሳምንታት የሚሰጥ ተከታታይ ትምህርት ነው

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን እስካሁን ድረስ ከዚህ አገልግሎት ጋር ቆማችሁ የዚህ አገልግሎት ተካፋዮች እና ተጠቃሚዎች ስለሆናችሁ እንደገናም ለዚህ አገልግሎት መሳካት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ስላደረጋችሁ ጌታ አምላክ ዘመናችሁን ይባርክ እያልኩ ሰኞ በሚኖረን የፌስቡክ ላይቭ አገልግሎት እንደተነጋገርነው አዲስ ትምህርት የምንጀምርበት ጊዜ ነው መንፈሳዊ የሕይወት ተሃዶሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ምን እንደሚመስል ከመጽሐፍቅዱሳችን አስረጂ በማቅረብ በተለይም መንፈሳዊ ተሃድሶን በሰዎች ሕይወት ላይም ሆነ በቤተክርስቲያን ያመጡ ሰዎችን ከመጽሐፍቅዱሳችን እንመለከታቸዋለን እንደገናም በዚህ ውስጥ ቤተክርስቲያን ምን ትምሰል ? የሚል መጠይቅን ይዘን እንቀርባለን ከዚህም ሌላ ተሃድሶ በኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን መቼ ተጀመረ ?ቤተክርስቲያኒቱም ክርስትናን አንድ ብላ ከተቀበለችበትና ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የነበራት መንፈሳዊ አቋምና መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ምን እንደነበረ እንመለከታለን እንደገናም ከዚህ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል መረዳቷ የቱ ጋር እንደወጣችና እንደለቀቀች ከታሪክም ሆነ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት አጣቅሰን መረጃም ሰብስበን እንመለከታለን የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ ሰፋ ያሉ እውነቶችንና የእግዚአብሔር ቃል መረዳቶችን ይዞ የቀረበ ስለሆነ እናንተም ሰፋ ብላችሁና ማስታወሻ ደብተሮቻችሁንም አዘጋጅታችሁ ተዘጋጅታችሁ ሰዎችንም ወደዚሁ የትምህርት ፕሮግራም በሰዓቱ ተገኝተው እንዲካፈሉ ጋብዟቸው ትምህርቱ እንደሚታወቀውበፌስቡክ ላይቭ የሚጀምረው በእኔ የሰዓት አቆጣጠር 10 AM ማለዳ ላይ ነው ሁልጊዜ ሰኞና ሐሙስ በዚህ ሰዓት ተዘጋጅቶ ይቀርብላችኋል በተረፈ በክርስቶስ ፍቅር በጣም እወዳችኋለሁ አከብራችኋላሁ ዘመናችሁ የተባረከ ይሁን በሰዓታችንና በቀጠሯችንም እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ በማለት የምሰናበታችሁ

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

God bless u all

yonasasfaw8@gmail.com

ፈጣን ተሐድሶ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

 ለዚህ ሥዕላዊ መጠይቅ መጽሐፍቅዱሳዊ መልሳችን

ተሐድሶ ያስፈልገኛል ስትል ወንጌልን አምና የተቀበለች ቤተክርስቲያን በአዲስ ፍጥረት ማንነት ትታደሳለች እንጂ አትጠፋም 

2ኛ ቆሮንቶስ 5፥ 17 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 ፤ የያዕቆብ መልዕክት 1 ፥ 18 እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል ይመልከቱ 

Down arow.png

Image result for መንፈሳዊ ተሐድሶ

Tuesday 3 October 2017

የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር 2የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር 2 ባለፈው ትምህርታችን መላዕክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉበትን ምሥጢር በስፋት አንስተን የምንባባችን መነሻ ሃሳብ ባደረግነው በዘፍጥረት 6 ፥ 1 _ 4 መሠረት የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ ይላልና ምንም እንኳ መላዕክት በአንዳንድ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉ ቢሆኑም በዚህ ቦታ ላይ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት መላዕክት አለመሆናቸውን አየን ለምን ስንል በመላዕክት ዘንድ ማግባትና መጋባት የሌለ በመሆኑ መላዕክት የሰውን ሴቶች ልጆች ሚስቶችን ለራሳቸው ያልወሰዱ መሆናቸውን የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት አድርገን በሰፊው ተመልክተናል ዛሬ ደግሞ ከዚሁ በተያያዘው ሃሳብ ተነስተን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት መላዕክት ካልሆኑ እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ በሰፊው በእግዚአብሔር ቃል ማብራርያነት እንመለከታለን የመጽሐፍቅዱስን ትርጉም ስንመለከት ታድያ ፦ 1ኛ ) እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የመሣፍንት ልጆች ናቸው የመሣፍንት ዘር ልዑል ፣ ልዕልት የሚለውን ትርጉም ይይዛል They were the noble and men of hig rank ኃያልና ጠንካራ ናቸው ዘጸአት 15 ፥ 11 ፤ ዘጸአት 12 ፥ 12 እንደገናም ፈራጆች መሆናቸውን ይነግረናል Where it is translated Judges ዘጸአት 22 ፥ 28 ፤ 1ኛ ሳሙኤል 2 ፥ 25 የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉ የተከበሩ የተደነቁ ልዑላን ወይም ባላባቶች ማለት ሲሆን በንግሥቷ ዙርያ ያሉ በዘላቂነት ጽኑ ኃያል የሆኑ ማለት ነው እንደገናም ኃያልና ጠንካራ የሆኑ የአምላክ ልጆች ማለት ነው ኢዮብ 1 ፥ 6 ፤ ኢዮብ 38 ፥ 7 ታድያ በዘፍጥረት 6 ፥ 1 እና 2 መሠረት ያገቧቸው የአምላክ ልጆች ከአዳም ልጆች ማለትም ከተመረጡት የሰው ሴቶች ልጆች ጋር በእርግጠኝነት ተመሣሣይነት አሏቸው እነዚህ የመሣፍንት ልጆች ዳኞች ፈራጆች ጠቃሚ የተባሉ የተከበሩ ሰዎች የሰውን ሴቶች ልጆች ሚስቶች ማድረጋቸው ይሄ ለእነርሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ወደ እነርሱ መመልከትና እነርሱን ለጋብቻ መውሰድ ወንጀል አይደለም ከእነርሱም ጋር ለዝሙት ውል መግባት ሃይማኖት አልባ ጋብቻ እንኩዋ ቢሆን እስካሁን ድረስ በከፊል ብቻ ነበር ዓለም አቀፍና በየትም ያለ ምግባረ ብልሹነት ወይም ውድቀት አልነበረም ነገር ግን በአቤል ምትክ የመጣው ሴት ይህንን የተረዳ በመሆኑ በሄኖስ ጊዜ አንድ ዓይነት ሰዎችን በእግዚአብሔር ስም ሊጠራ ጀመረ ዘፍጥረት 4 ፥ 25 ይህ ማለት የእግዚአብሔር ልጅና የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው This title manifestly relates to Genesis 4:26, where the same persons are said to be called by the name of the Lord, i.e. to be the sons and servants of God 2ኛ ) እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች በአቤል ፈንታ ከተወለደው ከሴት ጀምሮ የተወለዱ ናቸው እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ታድያ በደንብ የሚታዩ ታዋቂ የሆኑና ትልቅ ልህቀት ያላቸው አማልክት ተብለው ይጠራሉ ኃያል የሆኑ ልጆች ናቸው መዝሙር 82 ፥ 6 እግዚአብሔር ተጸጽቶባቸው አጠፋቸዋለሁ ካላቸውም በተቃራኒው ያሉ ሰዎች ናቸው ዘፍጥረት 6 ፥ 7 ሰዎቹም በአማካኝ በጣም የላቀ ነገር ያላቸው በባሕርያቸው የእግዚአብሔር መለያ ያላቸው እንደገናም ልዑል የተከበረና የተደነቀ ሰው በአጠቃላይ ሚስቶችን ወይም ሴቶችን ሊወስድ የሚችል አይሆንም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ስለሆኑ የሚፈርዱ የሚያለቅሱ ናቸው አለበለዚያም በኃጢአት የሚያለቅሱትን ሰዎች አይጠቅሱአቸውም እግዚአብሔር በሔዋን ልጅ በሴት መወለድ የተሟላ አስተያየት ለመስጠትና ለመሰየም ምክንያታዊ ነው ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በአቤል ፈንታ ለሔዋን ሴትን ሰጣት የእርስዋ ልጅ ሴት በዚህ ምክኛት ትኩረት የተሰጠው የእግዚአብሔር ልጅ ነው በሄኖስ የልደቱ ጊዜም በእግዚአብሔር ስም የመጠራት ልማድ ነበረው ዘፍጥረት 4 ፥ 26 ስለዚህ በአዳም ቤተሰብ ዙርያ ጥርጥር አልነበረም ሴት የተባለው ቀጥሎ እየኖረ ነውና በአዳም መስመር ላይ ሄኖክ ሰባተኛ ነው ደማቅና ምሳሌያዊ የሆነ እውነተኛ አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር እየሄደና እየኖረ ነው በሴት ተወላጅ መሐል እግዚአብሔር ወርቃማ ቃሎችን ተናግሮአል እንደገናም ኖህ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአል ስለዚህም በተፈጥሮ የሽግጝር ወቅት ምክንያት የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ተጠርቷል በአምላካዊ የሥነምግባር ሕግ ስሜትም ከመንፈስ ተወልደዋል ከመንፈስ መወለድ በኋላ በሥጋ ከእግዚአብሔር ጋር አልሄዱም መዝሙር 82 ፥ 6 ፤ ሆሴዕ 2 ፥ 1 ለዚህም ነው ከኖህ ጋራ ዳግመኛ ምድርን እንዳያጠፋ እንዳይረግማትም እግዚአብሔር ቃልኪዳን ያደረገው ኖህ በትውልዱ ጻድቅ ነበረ እንደገናም ኖህ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝቶ ነበረ ከጥፋትም ውሃ እርሱ ቤተሰቦቹን ይዞ ወደ መርከቡ በእምነት ታዞ ስለገባ ድኅነት ለእርሱ እና ለቤተሰቡ ሆነ 3ኛ ) የእግዚአብሔር ልጆች ከእግዚአብሔር ጎን የቆሙ ናቸው በየጊዜው ትርጉም በሚሰጥ ዘዴ በየጊዜው የሚያቀርቡ በእርሱ በተከበረው ስም የሚጠሩ በየቀኑ ባለ ንግጝር እና ጭውውት ከእጝዚአብሔር ጋር የሚሄዱ ናቸው በዘይቤያዊ ወይንም ምሳሌያዊ አነጋገር የልጅ ጥቅሙ በልዩ ልዩ ዓይነት አድራጎት መገናኘትን የሚያመለክት ነው ከእግዚአብሔር ጎን ቆሙ የተባሉትም ሰዎች ሀ ) ኖህ ለ ) አብርሐም ሐ) የሞተችዋ ራሔልና የእርሱ አባት ናቸው ዘፍጥረት 5 ፥ 32 ፣ ዘፍጥረት 15 ፥ 3 ፣ ዘፍጥረት 35 ፥ 18 The sons of God, therefore, are those who are on the Lord's side, who approach him with duly significant offerings, who call upon him by his proper name, and who walk with God in their daily conversation. The figurative use of the word "son" to denote a variety of relations incidental, and moral as well as natural, was not unfamiliar to the early speaker. Thus, Noah is called "the son of five hundred years" Genesis 5:32. Abraham calls Eliezer בן־בותי ben-bēytı̂y, "son of my house" Genesis 15:3. The dying Rachel names her son Ben-oni, "son of my sorrow," while his father called him Benjamin, "son of thy right hand" Genesis 35:18. ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com