Sunday 23 October 2016

ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት የይሁዳ መልዕክት ፳ ፍጻሜ ቊጥር ፬ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት ምዕራፍ 3 ( ክፍል ሦስት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምዕመናን በምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብለን ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ብለን ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ ማብራርያዎችን ሰጥተናል በምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት በሚል ቀጣዩንና ሰፊውን ትምህርት እንማማራለን ይህቺ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሠለስቱ ምዕት ዘእለ እስክንድሮስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው ከአባቶች ሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት የቀናች ናት ይለናልና ይህቺ የቀናች የተባለችው ሃይማኖት ማን እንደሆነችና የቀናች መባልዋም ከምን አንጻር እንደሆነ እንደገናም ይህቺ ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣችና የቀናች ሃይማኖት ሰዎችን ለዚሁ እምነት ወይም ሃይማኖት የተገቡ እንዲሆኑና ለሐሰት ትምህርትም የተጋለጡ እንዳይሆኑ በተጨማሪም ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ ባደረጉበት መጠን በጌታ በሆነው ትምህርት ሥር እንዲሰዱና እንዲታነጹ የምታደርግ ከዚም ሌላ ለዚሁ ሃይማኖት የተገቡ ሆነው በባሕርይ ለውጥ ምዕመኖችዋንና አገልጋዮችዋ ባደጉ ጊዜ የሚሆኑትን ነገር ትምህርቱ በሰፊው ያብራራል ወገኖቼ ትምህርቱ እንግዲህ ይህንን የሚመለከት ስለሆነ በቪድዮ ተለቋል ስለዚህ ይህን በሺዲዮ የተለቀቁትን ትምርቶች በመስማት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑና ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment