Monday 24 October 2016

የመልዕክት ርዕስ ፦ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ መጽሐፈ መሣፍንት 16 በሙሉ 19 _ 22.የመልዕክት ርዕስ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ መሣፍንት 16 በሙሉ ፥ ፣ 19 _ 22 Topic Then she began to torment him and his strength left him Judges 16 : 19 _ 22 የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ በሚል የቪዲዮ የመልዕክት ርዕስ ወደ እናንተ ብቅ ብያለሁ በዚህ መልዕክትም በብዙ እንደምትጠቀሙ ፣ ይህም መልዕክት ለሕይወታችሁ መልሕቅ የሆነ ቃል እንደሚሆንላችሁ አምናለሁ መጽሐፈ መሣፍንት ምዕራፍ 16 ሙሉ ሃሳቡን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያቶች አንዳንድ ጠቃሚ ሃሳቦችን አንስተን በጽሑፍም ሆነ በቪዲዮ ለእናንተ ለአድማጮች ማስተላለፌን አስታውሳለሁ ዛሬ ግን ከዚህ በተለየ መልኩ ይህ ከላይ በዋና አርዕስት መልክ የሰጠኋችሁ የመልዕክት ሃሳብ ወደ ልቤ ስለመጣ ይህንን የእግዚአብሔር ቃል እውነት ላካፍላችሁ ወድጃለሁ ፣ እንድትከታተሉትም በአክብሮት እጠይቃለሁ ሶምንን ልታዋርድ የጀመረች ደሊላ ጅማሬዋ ማዋረድ አልነበረም ጅማሬዋ ወዳጅነት ነው ነገር ግን ወዳጅነት የጀመረና ወድሃለሁ ያለ ሁሉ ወዳጅ ነው ማለት አይደለምና ደሊላ ወዳጅ ሳትሆን አሸናፊነትን ለጠላቶች ልታቀዳጅ ከጠላቶች ሠፈር የተላከች ሽንጋይ ነበረች አሁንም ነች መሣፍንት 16 ፥ 4 _ 7 አሽናፊዎችና ድል በመንሳትም የምንዞር መሆናችንን አውቀው በሠፈራቸው ፣ ሊያዋርዱንም በሚፈልጉት አደባባዮቻቸው መሽነፋችንንም ሆነ መዋረዳችንን የሚፈልጉ ፣ አብዝተውም የሚናፍቁ አጋንንቶችም ሆኑ አንዳንድ ሥጋውያን ክርስቲያኖች እንዲሁም የዓለም ሰዎች እንዳሉ ልንዘነጋ አይገባም ታድያ እነዚህ ሰዎች ከእኛ የተደበቁ ቢሆኑም ከእግዚአብሔር ግን የተደበቁ አይደሉም የሶምሶንን መዋረድ የሚጠብቁ በሶምሶን ያልታዩ እግዚአብሔር ግን ያያቸው በደሊላ ጓዳ ተደብቀው ደሊላን የሚያማክሩ ሶምሶን የሚታሠርበትንም እርጥብ ጠፍር የሚያቀብሉ በዚያን ዘመን እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም በዘመናችን አሉ መሣፍንት 16 ፥ 7 _ 9 ወዳጅ መሠል ሸንጋይዋ ደሊላ ሁልጊዜ በሶምሶን ሕይወት ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እያለች ጨዋታ በሚመስል የማዘናግያ ቃል ሶምሶንን በመፈታተን የምትኖር ነበረች አሁንም አለች ወደፊትም ትኖራለች በመሆኑም ዕድሉን ከሰጠናት ይህቺ ደሊላ ዛሬ ላይ ላለነው ለእኛም እንዲሁ ናት አሽናፊነታችንን ሳይሆን ተሽናፊነታችንን ፣ ድል ነሺነታችንን ሳይሆን ድል መነሳታችንን ፣ መዋረዳችንንም ጭምር የምትጠብቅ ናት በሶምሶን ሕይወት ውስጥ ደሊላ እንዲህ ነበረች ዛሬም መልኳን ሳትቀይር እንዲሁ አለች ሁልጊዜ የሶምሶንን ሽንፈት እና ውድቀት በታላቅ ጉጉት የምትጠብቅ ወዳጅ መሠል ጠላት ናት ቅዱሳን ወገኖች ዛሬም በሕይወታችን የሚመጡ እንዲህም ዓይነት ሰዎች መኖራቸውን አንዘንጋ ወገኖች ሆይ የዚች የደሊላ ቋንቋዋ ፤ እባክህ ንገረኝ ፣ አታለልከኝና ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም የሚል የመሸንገያ ቋንቋ ነው ታድያ ይሄ ሁሉ ጣዕመ ዜማ ባላቸው ቃላት የተከሸኑ ልመናዋና ተማኅጽኖዋ ወዳጅነትዋን ፣ ለሶምሶንም ያላትን ታማኝነትና ጠቀሜታዋን ጭምር ለማሳየት የመጡ ሳይሆን ሶምሶንን አማለው የሶምሶንን ልብ ለማግኘት የተዘጋጁ የድለላ ቃላት ናቸው በመሆኑም ይሄ ሁሉ ሶምሶንን ለማጥመድ የነበረው የደሊላ ምኞት ከደቂቃዎች በኋላ እውን ሆነ ይሕንንም ስኬትና ታላቅ ድል ያገኘችው ደሊላ ከራስዋ የግል ጥረት ብቻ ሳይሆን ከሶምሶንም ንዝሕላልነት የተነሣ ነበር መሣፍንት 16 ፥ 17 እና 18 የሶምሶንን ግዴለሽነትና ንዝሕላል መሆን በእርግጠኝነት ያወቀችው ደሊላ ያለመታከት ዕለት ዕለት በቃልዋ ስለነዘነዘችው ፣ ስላስቸገረችውም ሶምሶን ነፍሱ እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች እርሱም ከእናቴ ማኅጸን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየሁ ነኝና በራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም የራሴንም ጠጉር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል እደክማለሁም እንደሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ የልቡን ሁሉ ገለጠላት ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የደሊላ የክፋትና የማዋረድ እርምጃዋ የተገለጠው ብቸኛ አፍቃሪና የልብ ወዳጅ የመሠለችው ደሊላ ብቻዋን አለመሆንዋን ከወዳጅነትዋ ይልቅ በተቃራኒ በኩል የቆመች ከጠላትም ወገን የተሰለፈች ኃይለኛና ክፉ ባላንጣም መሆንዋን በሶምሶን ዋነኛ ጠላቶች ፊት አስመሠከረች ይሄ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚል በደሊላ ድምጽ ውስጥ የተቃኘ ሆኖ እያቃጨለ በመደጋገሞ የሚመጣ ፍቅር መሠል የጥሪ ደወል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሶምሶን የሽንፈት ፣ የውርደት እና የማብቂያ ደወል ሆኖ ተደወለ ይህ ደወል ታድያ ሶምሶንን ሳያስበው ከጨዋታ ውጪ ያደረገው ደወል ነበር ታድያ ወገኖች ሆይ ይህ ደወል በሶምሶን ላይ የመጨረሻ ሆኖና ተደወሎ የቀረ አይደለም ዛሬም እኛ ጋር ደርሶ ለእኛም ለአንዳንዶቻችን በጊዜ ካልነቃን መጨረሻችንን ይዞ ሊያዋርደንና ሊያሳፍረን መደወሉ አይቀርም በሬ ከአራጁ ጋር ዋለ እንደሚባለው እኛን ከእንደዚህ ዓይነቱ ለማውጣት ፣ ውሎአችንንም ሆነ አካሄዳችንን ለመለወጥ እንደገናም እኛነታችንንም ጭምር ለመቀስቀስና ለማንቃት ይህ ደወል ከደወልነቱ አልፎ በዘመናችን እንዳለ የቤታችን አላርም ዓይነት ድምጽ ሳይቀር አብዝቶ እየጮኸና እየተጣራ እየተደወለም እንዳለ መዘንጋት የለብንም ለማንኛውም ጌታ እግዚአብሔር ደሊላንና ደሊላን ከመሠሉ ሽንጋዮቻችን ሊያተርፈን በደሊላ ደወል ሳይሆን በራሱ ደወል ቀስቅሶና አንቅቶ ያትርፈን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment