Monday 24 October 2016

የመልዕክት ርዕስ ፦ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ መጽሐፈ መሣፍንት 16 በሙሉ 19 _ 22.የመልዕክት ርዕስ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ መሣፍንት 16 በሙሉ ፥ ፣ 19 _ 22 Topic Then she began to torment him and his strength left him Judges 16 : 19 _ 22 የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ በሚል የቪዲዮ የመልዕክት ርዕስ ወደ እናንተ ብቅ ብያለሁ በዚህ መልዕክትም በብዙ እንደምትጠቀሙ ፣ ይህም መልዕክት ለሕይወታችሁ መልሕቅ የሆነ ቃል እንደሚሆንላችሁ አምናለሁ መጽሐፈ መሣፍንት ምዕራፍ 16 ሙሉ ሃሳቡን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያቶች አንዳንድ ጠቃሚ ሃሳቦችን አንስተን በጽሑፍም ሆነ በቪዲዮ ለእናንተ ለአድማጮች ማስተላለፌን አስታውሳለሁ ዛሬ ግን ከዚህ በተለየ መልኩ ይህ ከላይ በዋና አርዕስት መልክ የሰጠኋችሁ የመልዕክት ሃሳብ ወደ ልቤ ስለመጣ ይህንን የእግዚአብሔር ቃል እውነት ላካፍላችሁ ወድጃለሁ ፣ እንድትከታተሉትም በአክብሮት እጠይቃለሁ ሶምንን ልታዋርድ የጀመረች ደሊላ ጅማሬዋ ማዋረድ አልነበረም ጅማሬዋ ወዳጅነት ነው ነገር ግን ወዳጅነት የጀመረና ወድሃለሁ ያለ ሁሉ ወዳጅ ነው ማለት አይደለምና ደሊላ ወዳጅ ሳትሆን አሸናፊነትን ለጠላቶች ልታቀዳጅ ከጠላቶች ሠፈር የተላከች ሽንጋይ ነበረች አሁንም ነች መሣፍንት 16 ፥ 4 _ 7 አሽናፊዎችና ድል በመንሳትም የምንዞር መሆናችንን አውቀው በሠፈራቸው ፣ ሊያዋርዱንም በሚፈልጉት አደባባዮቻቸው መሽነፋችንንም ሆነ መዋረዳችንን የሚፈልጉ ፣ አብዝተውም የሚናፍቁ አጋንንቶችም ሆኑ አንዳንድ ሥጋውያን ክርስቲያኖች እንዲሁም የዓለም ሰዎች እንዳሉ ልንዘነጋ አይገባም ታድያ እነዚህ ሰዎች ከእኛ የተደበቁ ቢሆኑም ከእግዚአብሔር ግን የተደበቁ አይደሉም የሶምሶንን መዋረድ የሚጠብቁ በሶምሶን ያልታዩ እግዚአብሔር ግን ያያቸው በደሊላ ጓዳ ተደብቀው ደሊላን የሚያማክሩ ሶምሶን የሚታሠርበትንም እርጥብ ጠፍር የሚያቀብሉ በዚያን ዘመን እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም በዘመናችን አሉ መሣፍንት 16 ፥ 7 _ 9 ወዳጅ መሠል ሸንጋይዋ ደሊላ ሁልጊዜ በሶምሶን ሕይወት ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እያለች ጨዋታ በሚመስል የማዘናግያ ቃል ሶምሶንን በመፈታተን የምትኖር ነበረች አሁንም አለች ወደፊትም ትኖራለች በመሆኑም ዕድሉን ከሰጠናት ይህቺ ደሊላ ዛሬ ላይ ላለነው ለእኛም እንዲሁ ናት አሽናፊነታችንን ሳይሆን ተሽናፊነታችንን ፣ ድል ነሺነታችንን ሳይሆን ድል መነሳታችንን ፣ መዋረዳችንንም ጭምር የምትጠብቅ ናት በሶምሶን ሕይወት ውስጥ ደሊላ እንዲህ ነበረች ዛሬም መልኳን ሳትቀይር እንዲሁ አለች ሁልጊዜ የሶምሶንን ሽንፈት እና ውድቀት በታላቅ ጉጉት የምትጠብቅ ወዳጅ መሠል ጠላት ናት ቅዱሳን ወገኖች ዛሬም በሕይወታችን የሚመጡ እንዲህም ዓይነት ሰዎች መኖራቸውን አንዘንጋ ወገኖች ሆይ የዚች የደሊላ ቋንቋዋ ፤ እባክህ ንገረኝ ፣ አታለልከኝና ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም የሚል የመሸንገያ ቋንቋ ነው ታድያ ይሄ ሁሉ ጣዕመ ዜማ ባላቸው ቃላት የተከሸኑ ልመናዋና ተማኅጽኖዋ ወዳጅነትዋን ፣ ለሶምሶንም ያላትን ታማኝነትና ጠቀሜታዋን ጭምር ለማሳየት የመጡ ሳይሆን ሶምሶንን አማለው የሶምሶንን ልብ ለማግኘት የተዘጋጁ የድለላ ቃላት ናቸው በመሆኑም ይሄ ሁሉ ሶምሶንን ለማጥመድ የነበረው የደሊላ ምኞት ከደቂቃዎች በኋላ እውን ሆነ ይሕንንም ስኬትና ታላቅ ድል ያገኘችው ደሊላ ከራስዋ የግል ጥረት ብቻ ሳይሆን ከሶምሶንም ንዝሕላልነት የተነሣ ነበር መሣፍንት 16 ፥ 17 እና 18 የሶምሶንን ግዴለሽነትና ንዝሕላል መሆን በእርግጠኝነት ያወቀችው ደሊላ ያለመታከት ዕለት ዕለት በቃልዋ ስለነዘነዘችው ፣ ስላስቸገረችውም ሶምሶን ነፍሱ እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች እርሱም ከእናቴ ማኅጸን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየሁ ነኝና በራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም የራሴንም ጠጉር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል እደክማለሁም እንደሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ የልቡን ሁሉ ገለጠላት ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የደሊላ የክፋትና የማዋረድ እርምጃዋ የተገለጠው ብቸኛ አፍቃሪና የልብ ወዳጅ የመሠለችው ደሊላ ብቻዋን አለመሆንዋን ከወዳጅነትዋ ይልቅ በተቃራኒ በኩል የቆመች ከጠላትም ወገን የተሰለፈች ኃይለኛና ክፉ ባላንጣም መሆንዋን በሶምሶን ዋነኛ ጠላቶች ፊት አስመሠከረች ይሄ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚል በደሊላ ድምጽ ውስጥ የተቃኘ ሆኖ እያቃጨለ በመደጋገሞ የሚመጣ ፍቅር መሠል የጥሪ ደወል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሶምሶን የሽንፈት ፣ የውርደት እና የማብቂያ ደወል ሆኖ ተደወለ ይህ ደወል ታድያ ሶምሶንን ሳያስበው ከጨዋታ ውጪ ያደረገው ደወል ነበር ታድያ ወገኖች ሆይ ይህ ደወል በሶምሶን ላይ የመጨረሻ ሆኖና ተደወሎ የቀረ አይደለም ዛሬም እኛ ጋር ደርሶ ለእኛም ለአንዳንዶቻችን በጊዜ ካልነቃን መጨረሻችንን ይዞ ሊያዋርደንና ሊያሳፍረን መደወሉ አይቀርም በሬ ከአራጁ ጋር ዋለ እንደሚባለው እኛን ከእንደዚህ ዓይነቱ ለማውጣት ፣ ውሎአችንንም ሆነ አካሄዳችንን ለመለወጥ እንደገናም እኛነታችንንም ጭምር ለመቀስቀስና ለማንቃት ይህ ደወል ከደወልነቱ አልፎ በዘመናችን እንዳለ የቤታችን አላርም ዓይነት ድምጽ ሳይቀር አብዝቶ እየጮኸና እየተጣራ እየተደወለም እንዳለ መዘንጋት የለብንም ለማንኛውም ጌታ እግዚአብሔር ደሊላንና ደሊላን ከመሠሉ ሽንጋዮቻችን ሊያተርፈን በደሊላ ደወል ሳይሆን በራሱ ደወል ቀስቅሶና አንቅቶ ያትርፈን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት የይሁዳ መልዕክት ፳ ፍጻሜ ቊጥር ፭ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት ምዕራፍ 3 ( ክፍል ሦስት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምዕመናን በምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብለን ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ብለን ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ ማብራርያዎችን ሰጥተናል በምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት በሚል ቀጣዩንና ሰፊውን ትምህርት እንማማራለን ይህቺ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሠለስቱ ምዕት ዘእለ እስክንድሮስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው ከአባቶች ሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት የቀናች ናት ይለናልና ይህቺ የቀናች የተባለችው ሃይማኖት ማን እንደሆነችና የቀናች መባልዋም ከምን አንጻር እንደሆነ እንደገናም ይህቺ ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣችና የቀናች ሃይማኖት ሰዎችን ለዚሁ እምነት ወይም ሃይማኖት የተገቡ እንዲሆኑና ለሐሰት ትምህርትም የተጋለጡ እንዳይሆኑ በተጨማሪም ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ ባደረጉበት መጠን በጌታ በሆነው ትምህርት ሥር እንዲሰዱና እንዲታነጹ የምታደርግ ከዚም ሌላ ለዚሁ ሃይማኖት የተገቡ ሆነው በባሕርይ ለውጥ ምዕመኖችዋንና አገልጋዮችዋ ባደጉ ጊዜ የሚሆኑትን ነገር ትምህርቱ በሰፊው ያብራራል ወገኖቼ ትምህርቱ እንግዲህ ይህንን የሚመለከት ስለሆነ በቪድዮ ተለቋል ስለዚህ ይህን በሺዲዮ የተለቀቁትን ትምርቶች በመስማት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑና ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Sunday 23 October 2016

ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት የይሁዳ መልዕክት ፳ ፍጻሜ ቊጥር ፬ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት ምዕራፍ 3 ( ክፍል ሦስት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምዕመናን በምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብለን ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ብለን ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ ማብራርያዎችን ሰጥተናል በምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት በሚል ቀጣዩንና ሰፊውን ትምህርት እንማማራለን ይህቺ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሠለስቱ ምዕት ዘእለ እስክንድሮስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው ከአባቶች ሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት የቀናች ናት ይለናልና ይህቺ የቀናች የተባለችው ሃይማኖት ማን እንደሆነችና የቀናች መባልዋም ከምን አንጻር እንደሆነ እንደገናም ይህቺ ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣችና የቀናች ሃይማኖት ሰዎችን ለዚሁ እምነት ወይም ሃይማኖት የተገቡ እንዲሆኑና ለሐሰት ትምህርትም የተጋለጡ እንዳይሆኑ በተጨማሪም ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ ባደረጉበት መጠን በጌታ በሆነው ትምህርት ሥር እንዲሰዱና እንዲታነጹ የምታደርግ ከዚም ሌላ ለዚሁ ሃይማኖት የተገቡ ሆነው በባሕርይ ለውጥ ምዕመኖችዋንና አገልጋዮችዋ ባደጉ ጊዜ የሚሆኑትን ነገር ትምህርቱ በሰፊው ያብራራል ወገኖቼ ትምህርቱ እንግዲህ ይህንን የሚመለከት ስለሆነ በቪድዮ ተለቋል ስለዚህ ይህን በሺዲዮ የተለቀቁትን ትምርቶች በመስማት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑና ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Friday 21 October 2016

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: የመልዕክት ርዕስ በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ1ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1...

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: የመልዕክት ርዕስ 

በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ
1ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1



...
: የመልዕክት ርዕስ  በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ 1ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1 የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ  የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry...


የመልዕክት ርዕስ 


በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ

1ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1
Image result for the lord rejected saul
Image result for the lord rejected saul

Image result for harmful spirit from god to saulImage result for harmful spirit from god to saul
Image result for the anointed david
Image result for David Anointed king





የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ  የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry   ነው ዛሬ ለእናንተ ለወገኖች በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የቀረበ አጭር መልዕክት አለኝ እርሱን እንደሚከተለው በጽሑፍ አቀርብላችኋለሁና ተከታተሉ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ፤ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው ይለናል ይህ ትዕዛዝ ሳሙኤል ለሳኦል እያለቀሰለት ያለ ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? ያለበት ጉዳይ ነው በመሆኑም ይህንን ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር ቢያስፈልግ  ለሳሙኤል እጅግ ከባድ ነው እንደገናም ሳኦል ለእግዚአብሔር ሰገድኩ እያለ ነው ሳሙኤል ደግሞ ምንም እንኳ ሳኦልን አግኝቶ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ በማለት የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ያስተላለፈለት ፣ ሳኦልንም እስከሞተበት ቀን ድረስ  ዳግመኛ ለማየት ያልሄደበት ጉዳይ ቢሆንም የሳኦል ነገር ግን ከሳሙኤል ጨርሶ ያልቆረጠለትና ከልቡም ያልወጣለት ሰው በመሆኑ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተቀብሎና በቀንዱም ዘይቱን ሞልቶ  ቅባልኝ ወደተባለው ሰው መሄድ ለሳሙኤል የሞት ያህል አዳጋች ነበር ለዚሁ ለእግዚአብሔር ትዕዛዝም ይሄው ሳሙኤል ምላሽ በመስጠት ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል ማለቱ አሁንም የሳኦል ነገር በሳሙኤል ሕይወት ውስጥ የሚያስከትለውን  የስጋት ሃይልና የክብደት መጠን በጉልህ የሚያሳይ ነው ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ እያለ በመለማመጥ የልብስን ጫፍ ይዞ የሚቀድን ሰው ፣ አልፎም ሄዶ ለእግዚአብሔር ሰገደ የተባለን ሰውና የተለቀሰለትን ሰው ትቶ  የተዘጋጀውን አዲስ ንጉሥ ለመቀባት በቀንድ ዘይትን ሞልቶ መሄድ ለሳሙኤል አሁንም ፍጹም የማይታሰብና  ድንገተኛም  ዱብዳ ነው ታድያ በዚህ ጉዳይ ላይ ሳሙኤል እንዲህ ከሚጨነቅ ይልቅ ይህንን ሁኔታ እግዚአብሔር ባየበት ዓይን ለማየት  ዓይኑን ቢከፍት እንዲህ ባልተቸገረ ነበር ታድያ ይህንን በሳኦልና በሳሙኤል ዘመን የነበረን አጀንዳ ወደ እኛም ዘመን ስናመጣው ዛሬም በዘመናችን አቅም አግኝተው ንስሐን በሚመስሉ የማግባብያና የለበጣ  ቃሎች ተውጠንጥነውና እና ተቀምመው እንደ ሳኦል ዘመን  የቀጠሉ የሚመስሉ አምልኮዎች ፣ አገልግሎቶች  ፣ የክህነት ሥራዎች እና ክህነቶችም ጭምር በእግዚአብሔር ዘንድ ያበቃላቸው ሆነው የተናቁና የተነወሩ ተቀባይነትም የሌላቸው ናቸው ሳሙኤልንም በመሠሉ የእግዚአብሔር ማላጆችና የእንባ ሰዎች ሊስተካከሉና ማሻሻያም ሊሰጥባቸው የማይፈለጉ ስለሆኑ እግዚአብሔር አሁንም ሳሙኤልን ለመሰሉ ታማኝ ባርያዎች ጊዜን ሳያባክኑ ለቀጣዩ እርምጃ የተዘጋጁ እንዲሆኑ  እስከመቼ ? ………ሂድ ………..አዘጋጅቻለሁ  የሚል ቃል አውጥቶባቸዋል ጌታ እግዚአብሔር እስከመቼ ? ባለበትና ባንገሽገሸው ነገር ሲያለቅሱም ሆነ እንባን ሲያፈሱ  መገኘት ራስን እንደ ማሞኘት በሳኦልና በመሰሎቹም ዘንድ እንደ መሞኘት ያስቆጥራልና አይሆንም  ከዚህም ሌላ ሳኦልንም ሆነ ሳኦልን ለመሰሉ የዘመናችን ሰዎች የሚጠቅም አይደለም እግዚአብሔር በማይቀበለው ነገር እንዲህ ላሉ ሰዎች ሲደክሙ መገኘት መልካም አይደለም ስለዚህ ለዚሁ ለሳሙኤል በመጣው መልዕክት መሠረት በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ ማለት ከተናቀውና ከተነወረው የሳኦል አምልኮና አገልግሎት የንግሥናም ዘመን ጭምር ውጣ እንደማለት ነው ሳሙኤል ከዚህ የሳኦል የንግሥና ፣ የአምልኮና የአገልግሎት ዘመን ካልወጣ በቀንዱ ዘይቱን መሙላት እንደገናም በቀንዱ ዘይቱን ሞልቶ እግዚአብሔር ወዳዘጋጀው ንጉሥ መሄድ አይችልም ነበርና ይህንኑ ለማድረግ ሳሙኤል  ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ ወጣ እግዚአብሔር የተናገረውንም አደረገ ወደ ቤተልሔምም መጣ ይለናል ይህ ነው እርምጃ ማለት እንግዲህ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በአዲስ መንፈስና በአዲስ አሠራር የሚያምን ስለሆነ በዚሁ አሠራራየሚነሱ አዳዲስ ዳዊቶች ዛሬም አሉትና በቀንዱ ዘይቱን ሞልቶ እንደሄደው እንደ ሳሙኤል ለእኛም እንዲሁ ወደነዚህ ሰዎች መሄድ ይሁንልን ሳሙኤል በዚህ ጉዳይ በብዙ ያቅማማና የተቸገረ ቢሆንም ግን ከምንም በላይ እግዚአብሔር ያለውን በመታመን ለእግዚአብሔር ሊታዘዝ ፈቃደኛ በመሆኑ እግዚአብሔር የተናገረውን ማድረግ ቻለ ለእኛም ይሄ ይሁንልን ሌላው ከምታለቅስበት ነገር ወጥተህ በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ የሚለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ለሳሙኤል እጅግ ከባድና ፈታኝ የሆነበት ምክንያት ሳሙኤል ይህንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ታዘዘና አደረገው ማለት የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ራቀ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው ማለት ስለሆነ  ለሳኦል እጅግ ከባድና የከፋ ነገር   ነው ታድያ አሁንም በዚህ ጉዳይ ሳሙኤል ለእግዚአብሔር የታዘዘ በመሆኑ ይህም ስቃይ በሳኦል ሕይወት ሆነ በመሆኑም የሳኦል ሕይወት ያላቸው ሰዎች ዛሬም ከዚህ ሕይወት ያመለጡ አይሆኑም ነገር ግን አሁን ላይ ባለ ሕይወታቸው ሳኦል እንዳላሰበ ይህ ይሆንብናል ይመጣብናልም ብለው አያስቡም ነገር ግን ውሎ አድሮ በሕይወታቸው ይህ ከመሆን አይቀርም የእግዚአብሔር መንፈስ በሐዲስ ኪዳን ከኛ ጋር ሊኖር የተሰጠን ቢሆንም ከተመረረ ግን ምን ሊፈጠር እንደሚችል እኔ መናገር አልችልም ለዚህም ነው ለቤዛ ቀን የታተምንበትን ቅዱሱን መንፈስ እንዳናሳዝንና እንዳናስመርር ጌታ በቃሉ የተናገረን እንደ ሳኦል ዓይነት ሰዎች ዛሬ ላይ ባለ ንስሐን በማይፈልግ ሕይወታቸው ይህንን ቢያደርጉም የነገው የሕይወት ምልልሳቸው ግን የጌታ አብሮነት የሌለበት በመሆኑ በሕይወታቸው የሚሆነው ከዚህ የከፋ ነው ጌታ እግዚአብሔር ከእንዲህ ዓይነቱ የከፋ ነገር ይጠብቀን 







ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ 

Monday 17 October 2016

ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት የይሁዳ መልዕክት ፳ ፍጻሜ ቊጥር ፫ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት ምዕራፍ 3 ( ክፍል ሦስት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምዕመናን በምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብለን ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ብለን ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ ማብራርያዎችን ሰጥተናል በምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት በሚል ቀጣዩንና ሰፊውን ትምህርት እንማማራለን ይህቺ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሠለስቱ ምዕት ዘእለ እስክንድሮስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው ከአባቶች ሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት የቀናች ናት ይለናልና ይህቺ የቀናች የተባለችው ሃይማኖት ማን እንደሆነችና የቀናች መባልዋም ከምን አንጻር እንደሆነ እንደገናም ይህቺ ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣችና የቀናች ሃይማኖት ሰዎችን ለዚሁ እምነት ወይም ሃይማኖት የተገቡ እንዲሆኑና ለሐሰት ትምህርትም የተጋለጡ እንዳይሆኑ በተጨማሪም ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ ባደረጉበት መጠን በጌታ በሆነው ትምህርት ሥር እንዲሰዱና እንዲታነጹ የምታደርግ ከዚም ሌላ ለዚሁ ሃይማኖት የተገቡ ሆነው በባሕርይ ለውጥ ምዕመኖችዋንና አገልጋዮችዋ ባደጉ ጊዜ የሚሆኑትን ነገር ትምህርቱ በሰፊው ያብራራል ወገኖቼ ትምህርቱ እንግዲህ ይህንን የሚመለከት ስለሆነ በቪድዮ ተለቋል ስለዚህ ይህን በሺዲዮ የተለቀቁትን ትምርቶች በመስማት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑና ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 13 October 2016

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: እምነትን ማካፈል

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: እምነትን ማካፈል: እምነትን ማካፈል     እምነትን ለሌሎች ማካፈል የክርስቲያን የሕይወት ክፍል ነው እምነታችንን ለሌሎች ማካፈል በኢየሱስ መታዘዝ የተሠራ እና የተከናወነ ታላቁ ተልእኮ ...

Friday 7 October 2016

ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት የይሁዳ መልዕክት ፳ ፍጻሜ ቊጥር ፪ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት ምዕራፍ 3 ( ክፍል ሦስት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምዕመናን በምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብለን ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ብለን ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ ማብራርያዎችን ሰጥተናል በምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት በሚል ቀጣዩንና ሰፊውን ትምህርት እንማማራለን ይህቺ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሠለስቱ ምዕት ዘእለ እስክንድሮስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው ከአባቶች ሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት የቀናች ናት ይለናልና ይህቺ የቀናች የተባለችው ሃይማኖት ማን እንደሆነችና የቀናች መባልዋም ከምን አንጻር እንደሆነ እንደገናም ይህቺ ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣችና የቀናች ሃይማኖት ሰዎችን ለዚሁ እምነት ወይም ሃይማኖት የተገቡ እንዲሆኑና ለሐሰት ትምህርትም የተጋለጡ እንዳይሆኑ በተጨማሪም ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ ባደረጉበት መጠን በጌታ በሆነው ትምህርት ሥር እንዲሰዱና እንዲታነጹ የምታደርግ ከዚም ሌላ ለዚሁ ሃይማኖት የተገቡ ሆነው በባሕርይ ለውጥ ምዕመኖችዋንና አገልጋዮችዋ ባደጉ ጊዜ የሚሆኑትን ነገር ትምህርቱ በሰፊው ያብራራል ወገኖቼ ትምህርቱ እንግዲህ ይህንን የሚመለከት ስለሆነ በቪድዮ ተለቋል ስለዚህ ይህን በሺዲዮ የተለቀቁትን ትምርቶች በመስማት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑና ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Sunday 2 October 2016

ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት የይሁዳ መልዕክት ቊጥር ፳_ ፍጻሜ ቊጥር ፩ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት ምዕራፍ 3 ( ክፍል ሦስት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምዕመናን በምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብለን ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ብለን ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ ማብራርያዎችን ሰጥተናል በምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት የምታንጽ ናት በሚል ቀጣዩንና ሰፊውን ትምህርት እንማማራለን ይህቺ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ሃይማኖት በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ሠለስቱ ምዕት ዘእለ እስክንድሮስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው ከአባቶች ሐዋርያት ስትያያዝ የመጣች ሃይማኖት የቀናች ናት ይለናልና ይህቺ የቀናች የተባለችው ሃይማኖት ማን እንደሆነችና የቀናች መባልዋም ከምን አንጻር እንደሆነ እንደገናም ይህቺ ከሐዋርያት ስትያያዝ የመጣችና የቀናች ሃይማኖት ሰዎችን ለዚሁ እምነት ወይም ሃይማኖት የተገቡ እንዲሆኑና ለሐሰት ትምህርትም የተጋለጡ እንዳይሆኑ በተጨማሪም ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ ባደረጉበት መጠን በጌታ በሆነው ትምህርት ሥር እንዲሰዱና እንዲታነጹ የምታደርግ ከዚም ሌላ ለዚሁ ሃይማኖት የተገቡ ሆነው በባሕርይ ለውጥ ምዕመኖችዋንና አገልጋዮችዋ ባደጉ ጊዜ የሚሆኑትን ነገር ትምህርቱ በሰፊው ያብራራል ወገኖቼ ትምህርቱ እንግዲህ ይህንን የሚመለከት ስለሆነ በቪድዮ ተለቋል ስለዚህ ይህን በሺዲዮ የተለቀቁትን ትምርቶች በመስማት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑና ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ