Tuesday 28 June 2016

የትምህርት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ራሱን እንዴት ገለጠ ? Part 1 How is God Revealed him self ?የትምህርት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ራሱን እንዴት ገለጠ ? Part 1 እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በቃሉ ነው እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥለት ነበር የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤል ሁሉ ደረሰ ይለናል 1ኛ ሳሙኤል 3 ፥ 21 እንደገናም ጳውሎስ ስለዚህም ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ይስጣች የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ በማለት ተናገረን ኤፌሶን 3 ፥ 15 _ 20 የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ የምንችለው ደግሞ እግዚአብሔር ቃሉንለሳሙኤል እንደገለጠለት ሁሉ ለእኛም ሲገልጥልን ነው ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ የእግዚአብሔር መገለጥ የግድ አስፈላጊያችን ነው ታድያ ሐዋርያው ለነዚህ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች የሚጸልይላቸው የቃሉን መገለጥ አግኝተው በውስጥ ሰውነታቸው በኃይል እንዲጠነክሩ ክርስቶስም በልባቸው በእምነት እንዲኖር ከመታወቅ የሚያልፈውንም የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ እንዲበረቱና እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ድረስ ደርሰው እንዲሞሉ ለማድረግ ነው ትምህርቱ በእነዚህ ጥቅሶች ዙርያ ብቻ ያጠነጠነ ሳይሆን በሌሎችም ሃሳቦችና የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ዙርያ ሰፊ የሆነ ማብራርያም የሚሰጠን ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን እነዚህ የሚለቀቁትን ቪዲዮዎች እንግዲህ ይበልጥ ተመልክታችሁ እንድትጠቀሙ ለማሳሰብ እወዳለሁ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry Servant of Lord Yonas Asfaw

Wednesday 22 June 2016

የመልዕክት ርዕስ ፦ ዳዊትም የተናገረው ቃል ተሰማ ( 1ኛ ሳሙኤል 17 ፥ 31 )የመልዕክት ርዕስ ፦ ዳዊትም የተናገረው ቃል ተሰማ ( 1ኛ ሳሙኤል 17 ፥ 31 ) መሰማት ዛሬ የብዙ ሰዎች ፍላጎትና ጥያቄ እየሆነ የመጣበት ጊዜ ነው ብዙ ሰዎች ባሉበት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከሌላው ይልቅ በብዙ እንዲሰሙ ሌላው ቀርቶ አጠገባቸው ካለው ከወንድማቸው ወይም ከእህቶቻቸው ይልቅ አብልጠው እና በልጠው ተሽለውም እንዲሰሙ የሚፈልጉበት ጊዜ ላይ ያለን በመሆኑ የውዽድሩ መጠን ከመቼውም በላይ እየናረና ከፍም እያለ የመጣበት ሰዓት ላይ ደርሰናል በመሆኑም ይህ ሁኔታ በጊዜው እልባት ሊያገኝ ሲገባው መፍትሔ ሰጪ ጠፍቶ አንዱ ሌላውን ከሚሰማው ይልቅ በዚያው ልክ አንዱ አንዱን እንዳይሰማው የሆነበት እንሰማማ ሲሉ በአንድ ጠረጴዛ የተቀመጡ ቢሆኑም እንኩዋ የሚቀመጡት ተደማምጠው መፍትሔ ላይ ለመድረስ ሳይሆን ለክርክርና ለፍጭት ለድብድብ አልፎም ለመለያየት ነው የዳዊት መሰማት ግን ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በብዙ የተለየ ነው ዳዊት የተናገረው ቃል የተሰማው ልሰማ ወይንም የእኔ ቃል ብቻ ይሰማ በሚል መንፈስ ውስጥ ሆኖ ሳይሆን ጌታ እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲሰማ ስለፈቀደለት ነው ታድያ ዛሬም በዘመናችን እንዲሰሙ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተፈቀደላቸው ሁሉ የቱንም ያህል ተቃውሞ ቢደርስባቸው ፣ ድምጻቸውም እንዳይወጣና እንዳይሰሙ ቢደረጉም እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ይሰማሉ ቃላቸው እስከ ምድር ዳርቻ የወጣ ሰዎች መሰማት ስላለባቸውና ሰዎችም ስለፈቀዱላቸው የተሰሙ ሳይሆኑ እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው የተሰሙ ነበሩ ( መዝሙር 19 ፥ 4 )እግዚአብሔር ሲፈቅድ የማይሰማ ማንም የለም ታድያ ይሄ ትምህርት የሚያስታውሰን የዳዊትን የተናገረውን ቃል መሰማት ብቻ ሳይሆን ቃሉ በንጉሥ ሳኦል ሳይቀር የተሰማው ዳዊት ወደዚህ መሰማት የመጣበትን መንገድና ዝርዝር ሁኔታ ትምህርቱ ይጠቁማል ስለዚህ የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ ረዘም ብሎ ሰፋ ያለ ቢሆንም ታግሳችሁና ጊዜ ወስዳችሁ እንደሚገባ ብትሰሙት በብዙ ትጠቀማላችሁ ብዬ አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry Servant of Lord Yonas Asfaw

Thursday 2 June 2016

የመልዕክት ርእስ ፡- ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ ( መጽሐፈ መሣፍንት ምዕራፍ 16 በሙሉ )የመልእክት ርእስ ፡- ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ (መጽሐፈ መሣፍንት 16 ምእራፍ በሙሉ) ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ቃል ለሶምሶን የማንቂያ ደወል ሊሆን ይገባ ነበር ነገር ግን አልሆነም ደሊላ የተባለችው ሴትም ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ድምጽ እና የመምጣታቸውም ጉዳይ በሶምሶን ሕይወት ላይ በተለያየ ጊዜ እውን እስኪሆን ድረስ የምትጠብቅ ሴት ነበረች ነገር ግን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ድምጽ ለሶምሶን ከደሊላ ጋር ኩኩሉ አልነጋም ሲል የሚጫወተው የወዳጅነት ድምጽ ሆነበት በዚህም የማንቂያ ደወል ሊነቃ ስላልቻለ ይህንኑ ጨዋታ በተደጋጋሚ መጫወት ጀመረ መጽሐፍቅዱስ በጨዋታ ሜዳ የሚታገል ማንም ቢሆን እንደሚገባ ባይታገል የድሉን አክሊል አያገኝም ይለናል ስለዚህ በፋንታው ሶምሶን ውርደትና ሽንፈት ደረሰበት እንጂ የድሉን አክሊል በወቅቱ በዚያን ሰዓት አላገኘም ድሉ የደሊላና የፍልስጥኤማውያን ሆነ ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እየተባለ በየጊዜው በደሊላ ሲነገረው የነበረው ነገር እውን ሆነ ታድያ አንዳንድ በጨዋታ መልክ ተለሳልሰው እና እንደ ቀልድ መስለው የሚነገሩን ነገሮች እውነት እላ ችሁአለሁ ወገኖቼ እውን ይሆናሉ እውን ሲሆኑም ደግሞ ይሆናሉ ስንል በማንጠብቅበት መንገድ ነው እንደገናም በሕይወታችን እውን ሲሆኑ አስከፊ ሁኔታን ይዘው ነው ይሄ ሊገባን ይገባል ታድያ እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ልብ ልንል የሚገባው ሶምሶን በእርግጠኝነት ጠላት እንዳለበት ካወቀ ማድረግ የነበረበት ከደሊላ ጋር የነበረውን የኩኩሉ አልነጋም ጨዋታ ወዲያው በቅጽበት ማቆም ነበረበት ግን አላቆመም ወገኖቼ የኛም ችግር ከዚሁ የዘለለ አይደለም ማቆም የነበረብንን የኩኩሉ ጨዋታ ዛሬ ላይ ካላቆምነው በሁዋላ ላይ ከኩኩሉ ይልቅ መልኩን ቀይሮና እውን ሆኖ በሕይወታችን ሲመጣ ጊዜው የእኛ አይሆንምና በፍጹም ልናቆመው አንችልም ማቆም ካለብን ሁሉንም ነገር ማቆም ያለብን አሁን ነው ይህ ብቻ አይደለም ሶምሶን ጠላት እንዳለበት ካወቀ አሁንም ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እስኪባል መጠበቅ የለበትም እንደውም መጡብህ ሳይሆን ማጣባቸው መባል ነው ያለበት ለእርሱ ግን ነገር የተገላቢጦሽ ሆኖ ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ ተባለ ይሁን እንጂ ከሶምሶን ይልቅ ለዚህ እና በዚህ ጉዳይ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ኢያሱ ነው ኢያሱ ያደረገው ነገር እንዲህ ነው ኢያሱም ከጌልጌላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው እግዚአብሔርም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው እያለ ከተናገረ በሁዋላ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ የለም ይለናል ኢያሱ ምእራፍ 10 በሙሉ አንብቡት እኛም ታድያ ለሶምሶን ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እንደተባለ ለእኛም በየስማችን እገሌ ሆይ ጠላቶችህ መጡብህ የምንባል መሆን የለብንም ይልቁንም በጠላቶቻችን ላይ ሌሊቱን ሙሉ ፈጥነን በመገስገስ የምንመጣባቸው የምናስደነግጣቸው የምንመታቸው እግዚአብሔርም የሚዋጋልን ሊሆን ነው የሚገባው ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ በጨዋታ ሜዳ እንደሚገባ ስንታገልና በትዳር ንግድ እራሳችንን ሳናጠላልፍ ስንቀር ማስተዋልም ሲኖረን ነው የተወደዳችሁ ወገኖች መልእክቱ እነዚህንና የመሳሰሉትን ሃሳቦች የጠቀለለ ነው በመልእክቱ እንግዲህ ተገልገሉ ተባረኩበት ተጠቀሙ ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ