Saturday 30 April 2016

የመልዕክት ርዕስ « የፈለገን ኢየሱስ ነው » የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ፥ 1 _ 12 ተነስቶአል ተነስቶአል ተነስቶአል ሞትን ድል ነስቶአል ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሀገር ውስጥና በውጪውም ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ በቅድሚያ እንኩዋን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ በማለት ልባዊ ደስታዬን ስገልጽ በመቀጠልም ይህ በዓል ለሁላችንም የደስታ የበረከት የመጽናናት የዕረፍት በዓል ይሁንልን በማለት ምስጋናዬን ከትልቅ አክብሮት ጋር ለመስጠት እወዳለሁ ከዚህ በመቀጠል ይህንን የትንሣኤ በዓል መታሰብያ ምክንያት በማድረግ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር ተዘጋጅቶ የሚቀርብላችሁ መጽሐፍቅዱሳዊ መልዕክት ይኖረኛል የመልዕክቱ ርዕስ « የፈለገን ኢየሱስ ነው »የሚል ሲሆን የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ፥ 1 _ 12 በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው በዚህ መልዕክትም በብዙ እንደምትባረኩ የሕይወት ለውጥና ክርስቶስንም በመቀበል ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም የመኖር ውሳኔ እንደምታደርጉ አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment