Saturday 30 April 2016

የመልዕክት ርዕስ « የፈለገን ኢየሱስ ነው » የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ፥ 1 _ 12 ተነስቶአል ተነስቶአል ተነስቶአል ሞትን ድል ነስቶአል ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሀገር ውስጥና በውጪውም ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ በቅድሚያ እንኩዋን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ በማለት ልባዊ ደስታዬን ስገልጽ በመቀጠልም ይህ በዓል ለሁላችንም የደስታ የበረከት የመጽናናት የዕረፍት በዓል ይሁንልን በማለት ምስጋናዬን ከትልቅ አክብሮት ጋር ለመስጠት እወዳለሁ ከዚህ በመቀጠል ይህንን የትንሣኤ በዓል መታሰብያ ምክንያት በማድረግ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር ተዘጋጅቶ የሚቀርብላችሁ መጽሐፍቅዱሳዊ መልዕክት ይኖረኛል የመልዕክቱ ርዕስ « የፈለገን ኢየሱስ ነው »የሚል ሲሆን የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ፥ 1 _ 12 በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው በዚህ መልዕክትም በብዙ እንደምትባረኩ የሕይወት ለውጥና ክርስቶስንም በመቀበል ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም የመኖር ውሳኔ እንደምታደርጉ አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Friday 29 April 2016

Lesson one የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 Part 3 የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ኃይልን ማበርታት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በብዙ አስፈላጊ ነገር ነው ኃይልን ማበርታት በዚህ ምድር በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ገብቶ ለመኖር ፣ ኃይልን ማበርታት ለተልዕኮና ለእግዚአብሔር ሥራ በእርግጠኝነት ይጠቅማል ኃይላቸውን ያላበረቱ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር በአግባቡ መኖር አይችሉም ወሳኝ በሆነ የሕይወት አቁዋም ላይ ሲቀለበሱ ፣ ሲንሸራተቱና ሲያስመስሉ አልፈው ሄደውም በግብዝነት ያልሆኑትን ሲሆኑ ሌሎችንም ሊመስሉ ሲሳቡና በደቦም ሲጉዋዙ ይስተዋላሉ ገላትያ 2 ፥ 11 _ 14 ኃይላቸውን ያበረቱ ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ሊፈጽሙ ዳር የሚያደርሱና ሥራውንም ሳያዝረከርኩ በትክክል የሚወጡ ናቸው ለዚህም ነው ሚክያስ በትንቢቱ እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ ያለን ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 ለምን ስንል አሁንም ሚክያስ በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው፦ ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል ይለናል ትንቢተ ሚክያስ 2 ፥ 1 ታድያ አሁንም ኃጢአትን ኃጢአት በደሉንም ሳያሽሞነሙኑ በደል ነው ብለው ሊናገሩ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልተው የሚገለጡ ሰዎች ሲመጡ በመኝታቸው ላይ በደልን አስበው እና ሊፈጽሙም ተቀስቅሰው የሚመጡ ሰዎች ይከለከላሉ 1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 20 እና 2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 1ን በሙሉ ይመልከቱ ወደ ሐዲስ ኪዳንም ሄደን ስንመለከት ዮሐንስ መጥምቁ በሄሮድስና በቤተመንግሥቱ የበደል ሥራ ውስጥ ተገልጦ ያደረገው ነገር ይህንን ነው ዮሐንስ ሄሮድስን፦ የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና ይለናል የማርቆስ ወንጌል 6 ፥ 18 ከዚያም አልፎ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል በማለት ይነግረናል የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 17 ይሁን እንጂ ታድያ መንፈስንና ኃይልን ካለማበርታት የተነሳ ዛሬ ላይ የቤተክርስቲያን መልዕክት ተንቆ ፣ ቀዝቅዞና ተለሳልሶ በምትኩ በደልና መተላለፍ ከፍ ብሎ ነግሦ በዓለማችንም ሆነ በቅዱሳን መካከል ይታያል ፣ በጉልህም ይንጸባረቃል ይህንንም በደል ለመቀነስ ሲባል አሁንም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል የሚሄድ እንደ ዮሐንስ ያለ ነገሥታት የሚሰሙት ፣ ለመልዕክቱም ታዘው ምን እናድርግ የሚሉት ፣ አንዳንዶችም ሰምተው የጌታን መንገድ ለመከተል ሲሉ በመልዕክቱ ኃይል ተነክተው ለመወሰን በልባቸው የሚያመነቱበት ሰው አልተገኘም ከዚህም ሌላ በዚሁ መንገድ ጻድቅና ቅዱስ እንደሆነ ተቆጥሮ የሚፈራና የሚጠበቅም እንደ ዮሐንስ ያለ ሰው ሊገኝ በፍጹም አልቻለም ይልቁንም አሁን ላይ ያለው መንፈስ የኤልያስ መንፈስ ሳይሆን የኢየሱስን የኪዳኑን ሕጎች የሚያጸና በማከናወንም የሚገልጣቸው መንፈስ ነው ያለው ነገር ግን ክንውኑን ሊገልጹ በእግዚአብሔር ቃል እውነት ፣ በተወለደ ማንነትና ባደገ ስብእና ከመንፈሱ ጋር የሚፈሱ ሰዎች በዚያን ዘመን ቢኖሩም በዘመናችን ግን ለዚህ መንፈስ የተገቡ ከጥቂት ሰዎች በቀር በአብዛኛው ለዚህ የተዘጋጀን ባለመሆናችን ዛሬ በጋብቻ ዙርያ ፣ በዘመን መካከል ባለ የትውልድ የግንኙነትና የልብ መቀባበል ዙርያ ፣ የጻድቃን ጥበብ በሚሆን ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ዙርያ ሰዎችን አልደረስናቸውም ፣ አላገኘናቸውምም ስለዚህ አሁን ላይ ባለ ዘመን ሁሉም ነገር ምስቅልቅሉ ወጥቶ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው በነዚህ በዘረዘርኩዋቸው ጉዳዮችና ሌሎችም ባልጠቀስኩዋቸው ነገሮች ውስጥ የሰፋ ክፍተት አለ መረንነት ፣ ሕግ አልበኝነት ፣ ማናለብኝነት ፣ አለሌነትና ዋልጌነት ገዝፎ ከፍቶና ሰልጥኖ ዓለማችንን ወርሮአል ትምህርቱ እነዚህን ይዘቶች በተገቢ መልኩ የሚጠቃቅስና መፍትሔዎቻቸውንም የሚጠቁም በመሆኑ በቪዲዮ ተዘጋጅቶ ተከታታይነትና ቀጣይነት ባለው መልእክት ይደመጥ ዘንድ ቀርቦአል በዚህ ትምህርት ሁላችሁም እንደምትባረኩበት አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 28 April 2016

Lesson One የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 Part 2 የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ኃይልን ማበርታት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በብዙ አስፈላጊ ነገር ነው ኃይልን ማበርታት በዚህ ምድር በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ገብቶ ለመኖር ፣ ኃይልን ማበርታት ለተልዕኮና ለእግዚአብሔር ሥራ በእርግጠኝነት ይጠቅማል ኃይላቸውን ያላበረቱ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር በአግባቡ መኖር አይችሉም ወሳኝ በሆነ የሕይወት አቁዋም ላይ ሲቀለበሱ ፣ ሲንሸራተቱና ሲያስመስሉ አልፈው ሄደውም በግብዝነት ያልሆኑትን ሲሆኑ ሌሎችንም ሊመስሉ ሲሳቡና በደቦም ሲጉዋዙ ይስተዋላሉ ገላትያ 2 ፥ 11 _ 14 ኃይላቸውን ያበረቱ ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ሊፈጽሙ ዳር የሚያደርሱና ሥራውንም ሳያዝረከርኩ በትክክል የሚወጡ ናቸው ለዚህም ነው ሚክያስ በትንቢቱ እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ ያለን ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 ለምን ስንል አሁንም ሚክያስ በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው፦ ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል ይለናል ትንቢተ ሚክያስ 2 ፥ 1 ታድያ አሁንም ኃጢአትን ኃጢአት በደሉንም ሳያሽሞነሙኑ በደል ነው ብለው ሊናገሩ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልተው የሚገለጡ ሰዎች ሲመጡ በመኝታቸው ላይ በደልን አስበው እና ሊፈጽሙም ተቀስቅሰው የሚመጡ ሰዎች ይከለከላሉ 1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 20 እና 2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 1ን በሙሉ ይመልከቱ ወደ ሐዲስ ኪዳንም ሄደን ስንመለከት ዮሐንስ መጥምቁ በሄሮድስና በቤተመንግሥቱ የበደል ሥራ ውስጥ ተገልጦ ያደረገው ነገር ይህንን ነው ዮሐንስ ሄሮድስን፦ የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና ይለናል የማርቆስ ወንጌል 6 ፥ 18 ከዚያም አልፎ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል በማለት ይነግረናል የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 17 ይሁን እንጂ ታድያ መንፈስንና ኃይልን ካለማበርታት የተነሳ ዛሬ ላይ የቤተክርስቲያን መልዕክት ተንቆ ፣ ቀዝቅዞና ተለሳልሶ በምትኩ በደልና መተላለፍ ከፍ ብሎ ነግሦ በዓለማችንም ሆነ በቅዱሳን መካከል ይታያል ፣ በጉልህም ይንጸባረቃል ይህንንም በደል ለመቀነስ ሲባል አሁንም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል የሚሄድ እንደ ዮሐንስ ያለ ነገሥታት የሚሰሙት ፣ ለመልዕክቱም ታዘው ምን እናድርግ የሚሉት ፣ አንዳንዶችም ሰምተው የጌታን መንገድ ለመከተል ሲሉ በመልዕክቱ ኃይል ተነክተው ለመወሰን በልባቸው የሚያመነቱበት ሰው አልተገኘም ከዚህም ሌላ በዚሁ መንገድ ጻድቅና ቅዱስ እንደሆነ ተቆጥሮ የሚፈራና የሚጠበቅም እንደ ዮሐንስ ያለ ሰው ሊገኝ በፍጹም አልቻለም ይልቁንም አሁን ላይ ያለው መንፈስ የኤልያስ መንፈስ ሳይሆን የኢየሱስን የኪዳኑን ሕጎች የሚያጸና በማከናወንም የሚገልጣቸው መንፈስ ነው ያለው ነገር ግን ክንውኑን ሊገልጹ በእግዚአብሔር ቃል እውነት ፣ በተወለደ ማንነትና ባደገ ስብእና ከመንፈሱ ጋር የሚፈሱ ሰዎች በዚያን ዘመን ቢኖሩም በዘመናችን ግን ለዚህ መንፈስ የተገቡ ከጥቂት ሰዎች በቀር በአብዛኛው ለዚህ የተዘጋጀን ባለመሆናችን ዛሬ በጋብቻ ዙርያ ፣ በዘመን መካከል ባለ የትውልድ የግንኙነትና የልብ መቀባበል ዙርያ ፣ የጻድቃን ጥበብ በሚሆን ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ዙርያ ሰዎችን አልደረስናቸውም ፣ አላገኘናቸውምም ስለዚህ አሁን ላይ ባለ ዘመን ሁሉም ነገር ምስቅልቅሉ ወጥቶ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው በነዚህ በዘረዘርኩዋቸው ጉዳዮችና ሌሎችም ባልጠቀስኩዋቸው ነገሮች ውስጥ የሰፋ ክፍተት አለ መረንነት ፣ ሕግ አልበኝነት ፣ ማናለብኝነት ፣ አለሌነትና ዋልጌነት ገዝፎ ከፍቶና ሰልጥኖ ዓለማችንን ወርሮአል ትምህርቱ እነዚህን ይዘቶች በተገቢ መልኩ የሚጠቃቅስና መፍትሔዎቻቸውንም የሚጠቁም በመሆኑ በቪዲዮ ተዘጋጅቶ ተከታታይነትና ቀጣይነት ባለው መልእክት ይደመጥ ዘንድ ቀርቦአል በዚህ ትምህርት ሁላችሁም እንደምትባረኩበት አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Lesson One የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 Part 2

Wednesday 27 April 2016

Lesson One የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 Part 1የትምህርት ርዕስ ኃይልን የማበርታት ጥቅሙ ኃይልን ማበርታት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በብዙ አስፈላጊ ነገር ነው ኃይልን ማበርታት በዚህ ምድር በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ገብቶ ለመኖር ፣ ኃይልን ማበርታት ለተልዕኮና ለእግዚአብሔር ሥራ በእርግጠኝነት ይጠቅማል ኃይላቸውን ያላበረቱ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር በአግባቡ መኖር አይችሉም ወሳኝ በሆነ የሕይወት አቁዋም ላይ ሲቀለበሱ ፣ ሲንሸራተቱና ሲያስመስሉ አልፈው ሄደውም በግብዝነት ያልሆኑትን ሲሆኑ ሌሎችንም ሊመስሉ ሲሳቡና በደቦም ሲጉዋዙ ይስተዋላሉ ገላትያ 2 ፥ 11 _ 14 ኃይላቸውን ያበረቱ ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ሊፈጽሙ ዳር የሚያደርሱና ሥራውንም ሳያዝረከርኩ በትክክል የሚወጡ ናቸው ለዚህም ነው ሚክያስ በትንቢቱ እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ ያለን ትንቢተ ሚክያስ 3 ፥ 8 ለምን ስንል አሁንም ሚክያስ በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው፦ ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል ይለናል ትንቢተ ሚክያስ 2 ፥ 1 ታድያ አሁንም ኃጢአትን ኃጢአት በደሉንም ሳያሽሞነሙኑ በደል ነው ብለው ሊናገሩ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልተው የሚገለጡ ሰዎች ሲመጡ በመኝታቸው ላይ በደልን አስበው እና ሊፈጽሙም ተቀስቅሰው የሚመጡ ሰዎች ይከለከላሉ 1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 20 እና 2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 1ን በሙሉ ይመልከቱ ወደ ሐዲስ ኪዳንም ሄደን ስንመለከት ዮሐንስ መጥምቁ በሄሮድስና በቤተመንግሥቱ የበደል ሥራ ውስጥ ተገልጦ ያደረገው ነገር ይህንን ነው ዮሐንስ ሄሮድስን፦ የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና ይለናል የማርቆስ ወንጌል 6 ፥ 18 ከዚያም አልፎ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል በማለት ይነግረናል የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 17 ይሁን እንጂ ታድያ መንፈስንና ኃይልን ካለማበርታት የተነሳ ዛሬ ላይ የቤተክርስቲያን መልዕክት ተንቆ ፣ ቀዝቅዞና ተለሳልሶ በምትኩ በደልና መተላለፍ ከፍ ብሎ ነግሦ በዓለማችንም ሆነ በቅዱሳን መካከል ይታያል ፣ በጉልህም ይንጸባረቃል ይህንንም በደል ለመቀነስ ሲባል አሁንም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል የሚሄድ እንደ ዮሐንስ ያለ ነገሥታት የሚሰሙት ፣ ለመልዕክቱም ታዘው ምን እናድርግ የሚሉት ፣ አንዳንዶችም ሰምተው የጌታን መንገድ ለመከተል ሲሉ በመልዕክቱ ኃይል ተነክተው ለመወሰን በልባቸው የሚያመነቱበት ሰው አልተገኘም ከዚህም ሌላ በዚሁ መንገድ ጻድቅና ቅዱስ እንደሆነ ተቆጥሮ የሚፈራና የሚጠበቅም እንደ ዮሐንስ ያለ ሰው ሊገኝ በፍጹም አልቻለም ይልቁንም አሁን ላይ ያለው መንፈስ የኤልያስ መንፈስ ሳይሆን የኢየሱስን የኪዳኑን ሕጎች የሚያጸና በማከናወንም የሚገልጣቸው መንፈስ ነው ያለው ነገር ግን ክንውኑን ሊገልጹ በእግዚአብሔር ቃል እውነት ፣ በተወለደ ማንነትና ባደገ ስብእና ከመንፈሱ ጋር የሚፈሱ ሰዎች በዚያን ዘመን ቢኖሩም በዘመናችን ግን ለዚህ መንፈስ የተገቡ ከጥቂት ሰዎች በቀር በአብዛኛው ለዚህ የተዘጋጀን ባለመሆናችን ዛሬ በጋብቻ ዙርያ ፣ በዘመን መካከል ባለ የትውልድ የግንኙነትና የልብ መቀባበል ዙርያ ፣ የጻድቃን ጥበብ በሚሆን ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ዙርያ ሰዎችን አልደረስናቸውም ፣ አላገኘናቸውምም ስለዚህ አሁን ላይ ባለ ዘመን ሁሉም ነገር ምስቅልቅሉ ወጥቶ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው በነዚህ በዘረዘርኩዋቸው ጉዳዮችና ሌሎችም ባልጠቀስኩዋቸው ነገሮች ውስጥ የሰፋ ክፍተት አለ መረንነት ፣ ሕግ አልበኝነት ፣ ማናለብኝነት ፣ አለሌነትና ዋልጌነት ገዝፎ ከፍቶና ሰልጥኖ ዓለማችንን ወርሮአል ትምህርቱ እነዚህን ይዘቶች በተገቢ መልኩ የሚጠቃቅስና መፍትሔዎቻቸውንም የሚጠቁም በመሆኑ በቪዲዮ ተዘጋጅቶ ተከታታይነትና ቀጣይነት ባለው መልእክት ይደመጥ ዘንድ ቀርቦአል በዚህ ትምህርት ሁላችሁም እንደምትባረኩበት አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Monday 25 April 2016

( ትምህርት ሰባት ) የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር..Part 3 የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ 1ኛ )ትምህርቱ ሲጀምር የመከራን ዓይነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማጣቀስ ክርስቲያን ከመከራ ጋር የተያያዘ ሕይወት ያለው መሆኑን በሰፊው ይተነትንና ጌታ እግዚአብሔር በዚህ በከባድ ሕመምና በከባድ የመከራ ጊዜ የሚሰጠው ተስፋ አለ በማለት ይቀጥላል ከባዱ ሕመምና ከባዱ መከራ ደግሞ የአንድ ጊዜ መከራ ወይንም የአንድ ሌሊት ችግር ሳይሆን ሊገፋ የማይችል ዓመታትን ያስቆጠረ የረጅም ጊዜ ስቃይና የጨለማ ሕይወት መሆኑን ያበስራል ኢዮብ 5 ፥ 6 እና 7 ፤ ኢዮብ 14 ፥ 1 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 3 ፥ 3 ፤ ፊልጵስዩስ 1 ፥ 29 እና 30 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 8 _ 11 ፣ 15 _ 18 ፤ መዝሙር 45 ( 46 ) ፥ 1 እና 2 ታድያ ሰዎች በቀላሉ ሊወጡትና ሊገላገሉት የማይችሉትን ይህንን የረጅም ጊዜ የጨለማና የሰቆቃ ሕይወት ያለ እግዚአብሔር ተስፋ በራሳቸው ወይም በማንነታቸው ፍጹም ሊዘልቁትም ሆነ ሊወጡት አለመቻላቸውን ይጠቁማል ስለዚህ ይህ የእግዚአብሔር ተስፋ የቃሉ አማኞች ለሆኑ ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር በእጅጉ አስፈላጊ የሆነ ተስፋ በመሆኑ ይህንን በቃሉ ውስጥ ያለን የእግዚአብሔር ተስፋ አማኝ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር የሆነ በሙሉ ሊያምነው ሊቀበለው ሊያጣጥመውና ሊወደው ተስፋም ሊያደርገው የሚገባ እውነት መሆኑን ከትምህርቱና ከቃሉ እውነት አንጻር አበክሬ ለማስገንዘብ እወዳለሁ 2ኛ )ተስፋ ማጣትን በተመለከተ ፦ መጽሐፍቅዱሳችን በኤፌሶን 2 ፥ 11 _ 19 ላይ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ይለናል ወገኖቼ እንግዲህ ይህ ቃል ከእስራኤል መንግስት ርቀው ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች ሆነው በዚህ ዓለም ተስፋን አጥተው ከእግዚአብሔር ተለይተው ያለ ክርስቶስ ለነበሩ አሕዛብ የተነገረ ቢሆንም ይሄ ጉዳይ ያለክርስቶስ የሆነና ከእግዚአብሔር የተለየ የሰውን ዘር ሁሉ የሚመለከት በመሆኑ ክርስቶስ የሌለው ማለትም ክርስቶስን የሕይወቱ ጌታና አዳኝ አድርጎ ያልተቀበለ የሰው ዘር ሁሉ ክርስቶስ እስከሌለውና ከእግዚአብሔር እስከተለየ ድረስ ተስፋ ያጣ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ያስተምረናል ተስፋ ማጣት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በብዙ ርቀት ውስጥ ያለ የአሮጌው ሰው ማንነትን የሚያመለክት ነው ይህ የአሮጌው ሰው የማንነት ሕይወት የሰላም መታጣት ያለበት የቅናት የጥል የክርክር የነፍሰ ገዳይነት እና የመሣሠሉት የአመጽ ሥራዎች የሚገለጹበት ሕይወት ነው ታድያ ተስፋ ማጣት ሲኖር የሰላም መታጣት አለና እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች ሁሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ በጉልህ ይንጸባረቃሉ በመሆኑም ይህ ክፉ ባሕርይ የሚገለጥበት አዳማዊ ሕይወት የሰውን ልጅ በኑሮው እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለ ዘላለማዊ ሕይወቱም ጭምር ተስፋ ያሳጣና ሰላምንም የከለከለ ነው ከዚህም ሌላ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም ሰው ከሰው ጋር ማለትም ወንድም ከወንድሙ ጋር ተጣልቶና ተጠላልቶ ተፈራርቶና ተራርቆም እንዲኖር ያደረገ ክፉኛ ባሕርይ ነው ይህንን ነው እንግዲህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለሰው ዘር ሁሉ በመሞትና ደሙንም በማፍሰስ የሰው ልጅ በሙሉ ያጣውንና ከቶውንም ቢሆን ሊያገኘው የማይችለውን ተስፋና ሰላም የመለሰለት ስለዚህ ይህንን ጌታ ኢየሱስን ያመነ ማንኛውም የሰው ዘር ሁሉ ከተስፋ ማጣት ወጥቶ በአሁኑ ሰዓት ተስፋውንና ሙሉ የሆነ ሰላሙን ያገኘ ነው ከዚህም ባሻገር ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው በራቀ ሕይወት የሚመላለሰው ማንነቱ በክርስቶስ ደም ምክንያት ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው ጋር የመቅረብ ዕድሉን አምጥቶለታል ለዚህ ነው ኢሳይያስ በትንቢቱ ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ያለን ትንቢተ ኢሳይያስ 9 ፥ 1 እና 2 ጭንቀት ራሱን የቻለ ተስፋ ማጣትና የሰላም መደፍረስ ያለበት ሕይወት በመሆኑ ክርስቶስ ለሌለው እና ከእግዚአብሔር ለራቀ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ከባድ የመከራ፣ የጨለማ፣ የሰቆቃና የሞት ጥላ ያለበት ሕይወት ነው በመሆኑም እርሱን በማመናችን ምክንያት ለዘላለም እስከወዲያኛው የሚያሳርፈን ጌታ በመጣልን ጊዜ ግን ኢሳይያስ በትንቢቱ እንደነገረን ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም የሚል ቃል ታወጀልን ወገኖቼ ይህንን ታላቅ የምሕረት አዋጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ብቻ ሳይሆን ዛሬም እኔም የእግዚአብሔር ባርያ የሆንኩት በተራዬ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም ስል ይህን እውነት ላልሰሙ ሁሉ ይሰሙና ከችግሮቻቸውም ነጻ ይወጡ ዘንድ አውጃለሁ 3ኛ )ሦስተኛው ተስፋ ደግሞ ጌታ እግዚአብሔር ረጅሙን የአራት መቶ ሰላሳ ዓመት የግብጽ ባርነትና የሰባውን የባቢሎን የምርኮ ዓመት እስራኤል ባርያ ሆነው በገፈገፉበት ጊዜ አስቀድሞ ለእምነት አባታቸው ለአብርሃምና ለራሳቸው ለእስራኤል የሰጠው ተስፋ ነበር በመሆኑም እንግዲህ ይሄ የእግዚአብሔር ተስፋ ነው እስራኤልን እነዚህን ሁለቱን ረጃጅም የምርኮ ዓመታት በተስፋ እንዲከርሙ ያደረገው እስራኤል በግብጽ ሳሉ በዚህ ተስፋ ውስጥ ስለነበሩ ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነስቶ ገባሮች ቢያደርጋቸውና ቢጠበብባቸውም እነርሱ ግን እንዳስጨነቋቸው መጠን እንዲሁ በዙ እጅግም ጸኑ ይለናል በባቢሎንም እንዲሁ ምርኮ ሆነው በሄዱ ጊዜ የተነገራቸው የተስፋው ቃል የሚፈጸም ነውና እንዲሁ ያጸናቸው ነበር ዘፍጥረት 15 ፥ 13 እና 14 ፤ ዘጸአት ምዕራፍ 1 በሙሉ ፤ ኤርምያስ 29 ፥ 10 4ኛ ) በትንቢተ ኤርምያስ 46 ፥ 28 በተነገረው ቃል መሠረት ጌታ እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም ማለቱ የሰው ልጆችን ከልቡ አለማስጨነቁ እና ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት የሚራራ መሆኑን አይተንበታል ከዚሁ ጋራም ንጉሥ ዳዊትን ሰይጣን አንቀሳቅሶት ሕዝብ ቆጠራ ውስጥ በገባ ጊዜ ጌታ እንዴት እንደራራለትና እንደማረው በሰፊው ተመልክተናል 1ኛ ዜና 21 ፥ 1 _ 30 ፤ ሰቆ ኤርምያስ 3 ፥ 22 እና 23 ፣ 31 _ 33 ወገኖቼ ሆይ የትምህርቱ ይዘት ይህን የሚመስል ሲሆን ይህንኑ አስመልክቶ ግን ቀጣይነት ያላቸው በቪዲዮ የተለቀቁ ትምህርቶች ስላሉ እነዚህኑ ትምህርቶች ከዚሁ ጽሑፍ ጋር በማገናዘብ በማስተዋል እንድትከታተሉአቸውና ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉት በትሕትና እና በአክብሮት እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ.

Friday 22 April 2016

( ትምህርት ሰባት ) የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ Part 2Part 2 የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ 1ኛ )ትምህርቱ ሲጀምር የመከራን ዓይነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማጣቀስ ክርስቲያን ከመከራ ጋር የተያያዘ ሕይወት ያለው መሆኑን በሰፊው ይተነትንና ጌታ እግዚአብሔር በዚህ በከባድ ሕመምና በከባድ የመከራ ጊዜ የሚሰጠው ተስፋ አለ በማለት ይቀጥላል ከባዱ ሕመምና ከባዱ መከራ ደግሞ የአንድ ጊዜ መከራ ወይንም የአንድ ሌሊት ችግር ሳይሆን ሊገፋ የማይችል ዓመታትን ያስቆጠረ የረጅም ጊዜ ስቃይና የጨለማ ሕይወት መሆኑን ያበስራል ኢዮብ 5 ፥ 6 እና 7 ፤ ኢዮብ 14 ፥ 1 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 3 ፥ 3 ፤ ፊልጵስዩስ 1 ፥ 29 እና 30 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 8 _ 11 ፣ 15 _ 18 ፤ መዝሙር 45 ( 46 ) ፥ 1 እና 2 ታድያ ሰዎች በቀላሉ ሊወጡትና ሊገላገሉት የማይችሉትን ይህንን የረጅም ጊዜ የጨለማና የሰቆቃ ሕይወት ያለ እግዚአብሔር ተስፋ በራሳቸው ወይም በማንነታቸው ፍጹም ሊዘልቁትም ሆነ ሊወጡት አለመቻላቸውን ይጠቁማል ስለዚህ ይህ የእግዚአብሔር ተስፋ የቃሉ አማኞች ለሆኑ ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር በእጅጉ አስፈላጊ የሆነ ተስፋ በመሆኑ ይህንን በቃሉ ውስጥ ያለን የእግዚአብሔር ተስፋ አማኝ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር የሆነ በሙሉ ሊያምነው ሊቀበለው ሊያጣጥመውና ሊወደው ተስፋም ሊያደርገው የሚገባ እውነት መሆኑን ከትምህርቱና ከቃሉ እውነት አንጻር አበክሬ ለማስገንዘብ እወዳለሁ 2ኛ )ተስፋ ማጣትን በተመለከተ ፦ መጽሐፍቅዱሳችን በኤፌሶን 2 ፥ 11 _ 19 ላይ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ይለናል ወገኖቼ እንግዲህ ይህ ቃል ከእስራኤል መንግስት ርቀው ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች ሆነው በዚህ ዓለም ተስፋን አጥተው ከእግዚአብሔር ተለይተው ያለ ክርስቶስ ለነበሩ አሕዛብ የተነገረ ቢሆንም ይሄ ጉዳይ ያለክርስቶስ የሆነና ከእግዚአብሔር የተለየ የሰውን ዘር ሁሉ የሚመለከት በመሆኑ ክርስቶስ የሌለው ማለትም ክርስቶስን የሕይወቱ ጌታና አዳኝ አድርጎ ያልተቀበለ የሰው ዘር ሁሉ ክርስቶስ እስከሌለውና ከእግዚአብሔር እስከተለየ ድረስ ተስፋ ያጣ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ያስተምረናል ተስፋ ማጣት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በብዙ ርቀት ውስጥ ያለ የአሮጌው ሰው ማንነትን የሚያመለክት ነው ይህ የአሮጌው ሰው የማንነት ሕይወት የሰላም መታጣት ያለበት የቅናት የጥል የክርክር የነፍሰ ገዳይነት እና የመሣሠሉት የአመጽ ሥራዎች የሚገለጹበት ሕይወት ነው ታድያ ተስፋ ማጣት ሲኖር የሰላም መታጣት አለና እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች ሁሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ በጉልህ ይንጸባረቃሉ በመሆኑም ይህ ክፉ ባሕርይ የሚገለጥበት አዳማዊ ሕይወት የሰውን ልጅ በኑሮው እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለ ዘላለማዊ ሕይወቱም ጭምር ተስፋ ያሳጣና ሰላምንም የከለከለ ነው ከዚህም ሌላ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም ሰው ከሰው ጋር ማለትም ወንድም ከወንድሙ ጋር ተጣልቶና ተጠላልቶ ተፈራርቶና ተራርቆም እንዲኖር ያደረገ ክፉኛ ባሕርይ ነው ይህንን ነው እንግዲህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለሰው ዘር ሁሉ በመሞትና ደሙንም በማፍሰስ የሰው ልጅ በሙሉ ያጣውንና ከቶውንም ቢሆን ሊያገኘው የማይችለውን ተስፋና ሰላም የመለሰለት ስለዚህ ይህንን ጌታ ኢየሱስን ያመነ ማንኛውም የሰው ዘር ሁሉ ከተስፋ ማጣት ወጥቶ በአሁኑ ሰዓት ተስፋውንና ሙሉ የሆነ ሰላሙን ያገኘ ነው ከዚህም ባሻገር ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው በራቀ ሕይወት የሚመላለሰው ማንነቱ በክርስቶስ ደም ምክንያት ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው ጋር የመቅረብ ዕድሉን አምጥቶለታል ለዚህ ነው ኢሳይያስ በትንቢቱ ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ያለን ትንቢተ ኢሳይያስ 9 ፥ 1 እና 2 ጭንቀት ራሱን የቻለ ተስፋ ማጣትና የሰላም መደፍረስ ያለበት ሕይወት በመሆኑ ክርስቶስ ለሌለው እና ከእግዚአብሔር ለራቀ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ከባድ የመከራ፣ የጨለማ፣ የሰቆቃና የሞት ጥላ ያለበት ሕይወት ነው በመሆኑም እርሱን በማመናችን ምክንያት ለዘላለም እስከወዲያኛው የሚያሳርፈን ጌታ በመጣልን ጊዜ ግን ኢሳይያስ በትንቢቱ እንደነገረን ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም የሚል ቃል ታወጀልን ወገኖቼ ይህንን ታላቅ የምሕረት አዋጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ብቻ ሳይሆን ዛሬም እኔም የእግዚአብሔር ባርያ የሆንኩት በተራዬ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም ስል ይህን እውነት ላልሰሙ ሁሉ ይሰሙና ከችግሮቻቸውም ነጻ ይወጡ ዘንድ አውጃለሁ 3ኛ )ሦስተኛው ተስፋ ደግሞ ጌታ እግዚአብሔር ረጅሙን የአራት መቶ ሰላሳ ዓመት የግብጽ ባርነትና የሰባውን የባቢሎን የምርኮ ዓመት እስራኤል ባርያ ሆነው በገፈገፉበት ጊዜ አስቀድሞ ለእምነት አባታቸው ለአብርሃምና ለራሳቸው ለእስራኤል የሰጠው ተስፋ ነበር በመሆኑም እንግዲህ ይሄ የእግዚአብሔር ተስፋ ነው እስራኤልን እነዚህን ሁለቱን ረጃጅም የምርኮ ዓመታት በተስፋ እንዲከርሙ ያደረገው እስራኤል በግብጽ ሳሉ በዚህ ተስፋ ውስጥ ስለነበሩ ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነስቶ ገባሮች ቢያደርጋቸውና ቢጠበብባቸውም እነርሱ ግን እንዳስጨነቋቸው መጠን እንዲሁ በዙ እጅግም ጸኑ ይለናል በባቢሎንም እንዲሁ ምርኮ ሆነው በሄዱ ጊዜ የተነገራቸው የተስፋው ቃል የሚፈጸም ነውና እንዲሁ ያጸናቸው ነበር ዘፍጥረት 15 ፥ 13 እና 14 ፤ ዘጸአት ምዕራፍ 1 በሙሉ ፤ ኤርምያስ 29 ፥ 10 4ኛ ) በትንቢተ ኤርምያስ 46 ፥ 28 በተነገረው ቃል መሠረት ጌታ እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም ማለቱ የሰው ልጆችን ከልቡ አለማስጨነቁ እና ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት የሚራራ መሆኑን አይተንበታል ከዚሁ ጋራም ንጉሥ ዳዊትን ሰይጣን አንቀሳቅሶት ሕዝብ ቆጠራ ውስጥ በገባ ጊዜ ጌታ እንዴት እንደራራለትና እንደማረው በሰፊው ተመልክተናል 1ኛ ዜና 21 ፥ 1 _ 30 ፤ ሰቆ ኤርምያስ 3 ፥ 22 እና 23 ፣ 31 _ 33 ወገኖቼ ሆይ የትምህርቱ ይዘት ይህን የሚመስል ሲሆን ይህንኑ አስመልክቶ ግን ቀጣይነት ያላቸው በቪዲዮ የተለቀቁ ትምህርቶች ስላሉ እነዚህኑ ትምህርቶች ከዚሁ ጽሑፍ ጋር በማገናዘብ በማስተዋል እንድትከታተሉአቸውና ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉት በትሕትና እና በአክብሮት እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday 20 April 2016

( ትምህርት ሰባት ) የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ Part 1Part 1 የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ 1ኛ )ትምህርቱ ሲጀምር የመከራን ዓይነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማጣቀስ ክርስቲያን ከመከራ ጋር የተያያዘ ሕይወት ያለው መሆኑን በሰፊው ይተነትንና ጌታ እግዚአብሔር በዚህ በከባድ ሕመምና በከባድ የመከራ ጊዜ የሚሰጠው ተስፋ አለ በማለት ይቀጥላል ከባዱ ሕመምና ከባዱ መከራ ደግሞ የአንድ ጊዜ መከራ ወይንም የአንድ ሌሊት ችግር ሳይሆን ሊገፋ የማይችል ዓመታትን ያስቆጠረ የረጅም ጊዜ ስቃይና የጨለማ ሕይወት መሆኑን ያበስራል ኢዮብ 5 ፥ 6 እና 7 ፤ ኢዮብ 14 ፥ 1 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 3 ፥ 3 ፤ ፊልጵስዩስ 1 ፥ 29 እና 30 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 8 _ 11 ፣ 15 _ 18 ፤ መዝሙር 45 ( 46 ) ፥ 1 እና 2 ታድያ ሰዎች በቀላሉ ሊወጡትና ሊገላገሉት የማይችሉትን ይህንን የረጅም ጊዜ የጨለማና የሰቆቃ ሕይወት ያለ እግዚአብሔር ተስፋ በራሳቸው ወይም በማንነታቸው ፍጹም ሊዘልቁትም ሆነ ሊወጡት አለመቻላቸውን ይጠቁማል ስለዚህ ይህ የእግዚአብሔር ተስፋ የቃሉ አማኞች ለሆኑ ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር በእጅጉ አስፈላጊ የሆነ ተስፋ በመሆኑ ይህንን በቃሉ ውስጥ ያለን የእግዚአብሔር ተስፋ አማኝ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር የሆነ በሙሉ ሊያምነው ሊቀበለው ሊያጣጥመውና ሊወደው ተስፋም ሊያደርገው የሚገባ እውነት መሆኑን ከትምህርቱና ከቃሉ እውነት አንጻር አበክሬ ለማስገንዘብ እወዳለሁ 2ኛ )ተስፋ ማጣትን በተመለከተ ፦ መጽሐፍቅዱሳችን በኤፌሶን 2 ፥ 11 _ 19 ላይ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ይለናል ወገኖቼ እንግዲህ ይህ ቃል ከእስራኤል መንግስት ርቀው ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች ሆነው በዚህ ዓለም ተስፋን አጥተው ከእግዚአብሔር ተለይተው ያለ ክርስቶስ ለነበሩ አሕዛብ የተነገረ ቢሆንም ይሄ ጉዳይ ያለክርስቶስ የሆነና ከእግዚአብሔር የተለየ የሰውን ዘር ሁሉ የሚመለከት በመሆኑ ክርስቶስ የሌለው ማለትም ክርስቶስን የሕይወቱ ጌታና አዳኝ አድርጎ ያልተቀበለ የሰው ዘር ሁሉ ክርስቶስ እስከሌለውና ከእግዚአብሔር እስከተለየ ድረስ ተስፋ ያጣ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ያስተምረናል ተስፋ ማጣት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በብዙ ርቀት ውስጥ ያለ የአሮጌው ሰው ማንነትን የሚያመለክት ነው ይህ የአሮጌው ሰው የማንነት ሕይወት የሰላም መታጣት ያለበት የቅናት የጥል የክርክር የነፍሰ ገዳይነት እና የመሣሠሉት የአመጽ ሥራዎች የሚገለጹበት ሕይወት ነው ታድያ ተስፋ ማጣት ሲኖር የሰላም መታጣት አለና እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች ሁሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ በጉልህ ይንጸባረቃሉ በመሆኑም ይህ ክፉ ባሕርይ የሚገለጥበት አዳማዊ ሕይወት የሰውን ልጅ በኑሮው እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለ ዘላለማዊ ሕይወቱም ጭምር ተስፋ ያሳጣና ሰላምንም የከለከለ ነው ከዚህም ሌላ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም ሰው ከሰው ጋር ማለትም ወንድም ከወንድሙ ጋር ተጣልቶና ተጠላልቶ ተፈራርቶና ተራርቆም እንዲኖር ያደረገ ክፉኛ ባሕርይ ነው ይህንን ነው እንግዲህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለሰው ዘር ሁሉ በመሞትና ደሙንም በማፍሰስ የሰው ልጅ በሙሉ ያጣውንና ከቶውንም ቢሆን ሊያገኘው የማይችለውን ተስፋና ሰላም የመለሰለት ስለዚህ ይህንን ጌታ ኢየሱስን ያመነ ማንኛውም የሰው ዘር ሁሉ ከተስፋ ማጣት ወጥቶ በአሁኑ ሰዓት ተስፋውንና ሙሉ የሆነ ሰላሙን ያገኘ ነው ከዚህም ባሻገር ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው በራቀ ሕይወት የሚመላለሰው ማንነቱ በክርስቶስ ደም ምክንያት ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው ጋር የመቅረብ ዕድሉን አምጥቶለታል ለዚህ ነው ኢሳይያስ በትንቢቱ ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ያለን ትንቢተ ኢሳይያስ 9 ፥ 1 እና 2 ጭንቀት ራሱን የቻለ ተስፋ ማጣትና የሰላም መደፍረስ ያለበት ሕይወት በመሆኑ ክርስቶስ ለሌለው እና ከእግዚአብሔር ለራቀ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ከባድ የመከራ፣ የጨለማ፣ የሰቆቃና የሞት ጥላ ያለበት ሕይወት ነው በመሆኑም እርሱን በማመናችን ምክንያት ለዘላለም እስከወዲያኛው የሚያሳርፈን ጌታ በመጣልን ጊዜ ግን ኢሳይያስ በትንቢቱ እንደነገረን ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም የሚል ቃል ታወጀልን ወገኖቼ ይህንን ታላቅ የምሕረት አዋጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ብቻ ሳይሆን ዛሬም እኔም የእግዚአብሔር ባርያ የሆንኩት በተራዬ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም ስል ይህን እውነት ላልሰሙ ሁሉ ይሰሙና ከችግሮቻቸውም ነጻ ይወጡ ዘንድ አውጃለሁ 3ኛ )ሦስተኛው ተስፋ ደግሞ ጌታ እግዚአብሔር ረጅሙን የአራት መቶ ሰላሳ ዓመት የግብጽ ባርነትና የሰባውን የባቢሎን የምርኮ ዓመት እስራኤል ባርያ ሆነው በገፈገፉበት ጊዜ አስቀድሞ ለእምነት አባታቸው ለአብርሃምና ለራሳቸው ለእስራኤል የሰጠው ተስፋ ነበር በመሆኑም እንግዲህ ይሄ የእግዚአብሔር ተስፋ ነው እስራኤልን እነዚህን ሁለቱን ረጃጅም የምርኮ ዓመታት በተስፋ እንዲከርሙ ያደረገው እስራኤል በግብጽ ሳሉ በዚህ ተስፋ ውስጥ ስለነበሩ ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነስቶ ገባሮች ቢያደርጋቸውና ቢጠበብባቸውም እነርሱ ግን እንዳስጨነቋቸው መጠን እንዲሁ በዙ እጅግም ጸኑ ይለናል በባቢሎንም እንዲሁ ምርኮ ሆነው በሄዱ ጊዜ የተነገራቸው የተስፋው ቃል የሚፈጸም ነውና እንዲሁ ያጸናቸው ነበር ዘፍጥረት 15 ፥ 13 እና 14 ፤ ዘጸአት ምዕራፍ 1 በሙሉ ፤ ኤርምያስ 29 ፥ 10 4ኛ ) በትንቢተ ኤርምያስ 46 ፥ 28 በተነገረው ቃል መሠረት ጌታ እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም ማለቱ የሰው ልጆችን ከልቡ አለማስጨነቁ እና ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት የሚራራ መሆኑን አይተንበታል ከዚሁ ጋራም ንጉሥ ዳዊትን ሰይጣን አንቀሳቅሶት ሕዝብ ቆጠራ ውስጥ በገባ ጊዜ ጌታ እንዴት እንደራራለትና እንደማረው በሰፊው ተመልክተናል 1ኛ ዜና 21 ፥ 1 _ 30 ፤ ሰቆ ኤርምያስ 3 ፥ 22 እና 23 ፣ 31 _ 33 ወገኖቼ ሆይ የትምህርቱ ይዘት ይህን የሚመስል ሲሆን ይህንኑ አስመልክቶ ግን ቀጣይነት ያላቸው በቪዲዮ የተለቀቁ ትምህርቶች ስላሉ እነዚህኑ ትምህርቶች ከዚሁ ጽሑፍ ጋር በማገናዘብ በማስተዋል እንድትከታተሉአቸውና ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉት በትሕትና እና በአክብሮት እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Monday 18 April 2016

( ትምህርት ሰባት ) የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ (መግቢያ )የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች የትምህርት ርዕስ ፦ በከባድ ሕመም ፣ በከባድ መከራ ጊዜ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ተስፋ 1ኛ )ትምህርቱ ሲጀምር የመከራን ዓይነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማጣቀስ ክርስቲያን ከመከራ ጋር የተያያዘ ሕይወት ያለው መሆኑን በሰፊው ይተነትንና ጌታ እግዚአብሔር በዚህ በከባድ ሕመምና በከባድ የመከራ ጊዜ የሚሰጠው ተስፋ አለ በማለት ይቀጥላል ከባዱ ሕመምና ከባዱ መከራ ደግሞ የአንድ ጊዜ መከራ ወይንም የአንድ ሌሊት ችግር ሳይሆን ሊገፋ የማይችል ዓመታትን ያስቆጠረ የረጅም ጊዜ ስቃይና የጨለማ ሕይወት መሆኑን ያበስራል ኢዮብ 5 ፥ 6 እና 7 ፤ ኢዮብ 14 ፥ 1 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 3 ፥ 3 ፤ ፊልጵስዩስ 1 ፥ 29 እና 30 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 8 _ 11 ፣ 15 _ 18 ፤ መዝሙር 45 ( 46 ) ፥ 1 እና 2 ታድያ ሰዎች በቀላሉ ሊወጡትና ሊገላገሉት የማይችሉትን ይህንን የረጅም ጊዜ የጨለማና የሰቆቃ ሕይወት ያለ እግዚአብሔር ተስፋ በራሳቸው ወይም በማንነታቸው ፍጹም ሊዘልቁትም ሆነ ሊወጡት አለመቻላቸውን ይጠቁማል ስለዚህ ይህ የእግዚአብሔር ተስፋ የቃሉ አማኞች ለሆኑ ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር በእጅጉ አስፈላጊ የሆነ ተስፋ በመሆኑ ይህንን በቃሉ ውስጥ ያለን የእግዚአብሔር ተስፋ አማኝ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር የሆነ በሙሉ ሊያምነው ሊቀበለው ሊያጣጥመውና ሊወደው ተስፋም ሊያደርገው የሚገባ እውነት መሆኑን ከትምህርቱና ከቃሉ እውነት አንጻር አበክሬ ለማስገንዘብ እወዳለሁ 2ኛ )ተስፋ ማጣትን በተመለከተ ፦ መጽሐፍቅዱሳችን በኤፌሶን 2 ፥ 11 _ 19 ላይ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ይለናል ወገኖቼ እንግዲህ ይህ ቃል ከእስራኤል መንግስት ርቀው ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች ሆነው በዚህ ዓለም ተስፋን አጥተው ከእግዚአብሔር ተለይተው ያለ ክርስቶስ ለነበሩ አሕዛብ የተነገረ ቢሆንም ይሄ ጉዳይ ያለክርስቶስ የሆነና ከእግዚአብሔር የተለየ የሰውን ዘር ሁሉ የሚመለከት በመሆኑ ክርስቶስ የሌለው ማለትም ክርስቶስን የሕይወቱ ጌታና አዳኝ አድርጎ ያልተቀበለ የሰው ዘር ሁሉ ክርስቶስ እስከሌለውና ከእግዚአብሔር እስከተለየ ድረስ ተስፋ ያጣ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ያስተምረናል ተስፋ ማጣት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በብዙ ርቀት ውስጥ ያለ የአሮጌው ሰው ማንነትን የሚያመለክት ነው ይህ የአሮጌው ሰው የማንነት ሕይወት የሰላም መታጣት ያለበት የቅናት የጥል የክርክር የነፍሰ ገዳይነት እና የመሣሠሉት የአመጽ ሥራዎች የሚገለጹበት ሕይወት ነው ታድያ ተስፋ ማጣት ሲኖር የሰላም መታጣት አለና እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች ሁሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ በጉልህ ይንጸባረቃሉ በመሆኑም ይህ ክፉ ባሕርይ የሚገለጥበት አዳማዊ ሕይወት የሰውን ልጅ በኑሮው እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለ ዘላለማዊ ሕይወቱም ጭምር ተስፋ ያሳጣና ሰላምንም የከለከለ ነው ከዚህም ሌላ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም ሰው ከሰው ጋር ማለትም ወንድም ከወንድሙ ጋር ተጣልቶና ተጠላልቶ ተፈራርቶና ተራርቆም እንዲኖር ያደረገ ክፉኛ ባሕርይ ነው ይህንን ነው እንግዲህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለሰው ዘር ሁሉ በመሞትና ደሙንም በማፍሰስ የሰው ልጅ በሙሉ ያጣውንና ከቶውንም ቢሆን ሊያገኘው የማይችለውን ተስፋና ሰላም የመለሰለት ስለዚህ ይህንን ጌታ ኢየሱስን ያመነ ማንኛውም የሰው ዘር ሁሉ ከተስፋ ማጣት ወጥቶ በአሁኑ ሰዓት ተስፋውንና ሙሉ የሆነ ሰላሙን ያገኘ ነው ከዚህም ባሻገር ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው በራቀ ሕይወት የሚመላለሰው ማንነቱ በክርስቶስ ደም ምክንያት ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው ጋር የመቅረብ ዕድሉን አምጥቶለታል ለዚህ ነው ኢሳይያስ በትንቢቱ ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ያለን ትንቢተ ኢሳይያስ 9 ፥ 1 እና 2 ጭንቀት ራሱን የቻለ ተስፋ ማጣትና የሰላም መደፍረስ ያለበት ሕይወት በመሆኑ ክርስቶስ ለሌለው እና ከእግዚአብሔር ለራቀ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ከባድ የመከራ፣ የጨለማ፣ የሰቆቃና የሞት ጥላ ያለበት ሕይወት ነው በመሆኑም እርሱን በማመናችን ምክንያት ለዘላለም እስከወዲያኛው የሚያሳርፈን ጌታ በመጣልን ጊዜ ግን ኢሳይያስ በትንቢቱ እንደነገረን ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም የሚል ቃል ታወጀልን ወገኖቼ ይህንን ታላቅ የምሕረት አዋጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ብቻ ሳይሆን ዛሬም እኔም የእግዚአብሔር ባርያ የሆንኩት በተራዬ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም ስል ይህን እውነት ላልሰሙ ሁሉ ይሰሙና ከችግሮቻቸውም ነጻ ይወጡ ዘንድ አውጃለሁ 3ኛ )ሦስተኛው ተስፋ ደግሞ ጌታ እግዚአብሔር ረጅሙን የአራት መቶ ሰላሳ ዓመት የግብጽ ባርነትና የሰባውን የባቢሎን የምርኮ ዓመት እስራኤል ባርያ ሆነው በገፈገፉበት ጊዜ አስቀድሞ ለእምነት አባታቸው ለአብርሃምና ለራሳቸው ለእስራኤል የሰጠው ተስፋ ነበር በመሆኑም እንግዲህ ይሄ የእግዚአብሔር ተስፋ ነው እስራኤልን እነዚህን ሁለቱን ረጃጅም የምርኮ ዓመታት በተስፋ እንዲከርሙ ያደረገው እስራኤል በግብጽ ሳሉ በዚህ ተስፋ ውስጥ ስለነበሩ ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነስቶ ገባሮች ቢያደርጋቸውና ቢጠበብባቸውም እነርሱ ግን እንዳስጨነቋቸው መጠን እንዲሁ በዙ እጅግም ጸኑ ይለናል በባቢሎንም እንዲሁ ምርኮ ሆነው በሄዱ ጊዜ የተነገራቸው የተስፋው ቃል የሚፈጸም ነውና እንዲሁ ያጸናቸው ነበር ዘፍጥረት 15 ፥ 13 እና 14 ፤ ዘጸአት ምዕራፍ 1 በሙሉ ፤ ኤርምያስ 29 ፥ 10 4ኛ ) በትንቢተ ኤርምያስ 46 ፥ 28 በተነገረው ቃል መሠረት ጌታ እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም ማለቱ የሰው ልጆችን ከልቡ አለማስጨነቁ እና ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት የሚራራ መሆኑን አይተንበታል ከዚሁ ጋራም ንጉሥ ዳዊትን ሰይጣን አንቀሳቅሶት ሕዝብ ቆጠራ ውስጥ በገባ ጊዜ ጌታ እንዴት እንደራራለትና እንደማረው በሰፊው ተመልክተናል 1ኛ ዜና 21 ፥ 1 _ 30 ፤ ሰቆ ኤርምያስ 3 ፥ 22 እና 23 ፣ 31 _ 33 ወገኖቼ ሆይ የትምህርቱ ይዘት ይህን የሚመስል ሲሆን ይህንኑ አስመልክቶ ግን ቀጣይነት ያላቸው በቪዲዮ የተለቀቁ ትምህርቶች ስላሉ እነዚህኑ ትምህርቶች ከዚሁ ጽሑፍ ጋር በማገናዘብ በማስተዋል እንድትከታተሉአቸውና ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉት በትሕትና እና በአክብሮት እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 14 April 2016

(ትምህርት ሁለት) የትምህርቱ ርዕስ :- ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም ( ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ትን...ትምህርት ሁለት ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ ወቅታዊ እና ትምህርት አዘል መልዕክት ነው የትምህርቱ ርዕስ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም የሚል ሲሆን :---------------- የምንባቡ መነሻ ሃሳብ ደግሞ የኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት ውስጥ ኃይልን ስለመታጠቅ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ትምህርቶች መካከል የተወሰደና ጥቂቱን ሃሳብ የያዘ ነው ሙሉውን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት የማቀርበው ይሆናል በዚህ አጋጣሚ ግን የፓልቶክን አገልግሎት ለማታውቁ በየሳምንቱ ማክሰኞ በእኔ የሰዓት አቆጣጠር ከ 10 ፥ 30 ማለዳ ላይ ጀምሮ በዚሁ ሩም በእኔ በባርያው የሚተላለፍ ትምህርት ስላለ እርሱን እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናሁን ማሳሰብ እወዳለሁ ሩሙ ማለትም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ስለዚህ ጊዜ ያላችሁ ወገኖች በእነዚህ ሰዓታቶች ሁሉ እየገባችሁ መካፈል የምትችሉ መሆናችሁን ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ በመቀጠልም ወዳዘጋጀሁት የትምህርት ሃሳብ ስመጣ ይህንን ጸሎት ኤርምያስ እንዲህ ሲል የጸለየው ጸሎት ቢሆንም በትላንትናው ዘመን በኤርምያስ ብቻ ሳይሆን አሁንም ላይ ባለ ዘመንና እስከ ለዘላለሙም ከእግዚአብሔር ያለፈ ፣ ከእግዚአብሔርም የሚያቅት ምንም ነገር የሌለ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ይጠቁማል ለዚህም ነው እንግዲህ ኤርምያስ አሁንም በትንቢቱ አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ሲል የነገረን ትንቢተ ኤርምያስ 10 ፥ 6 የእግዚአብሔር ታላቅነት በየት በየት ቦታ እና ለምን ለምን ጉዳይ ተገለጠ ስንል ደግሞ በቪዲዮ የሚለቀቀው ትምህርት ስላለ እርሱ ሰፊውን ሃሳብ ይዞ ይመልስልናል ከዚህም ባሸገር የዚህ ትምህርታዊ መልዕክት ዋናውና አንኳሩ ሃሳብ እነዚህ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር እንደሌለ የተረዱ እና የተባሉትን ነገር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚቃኝ ሲሆን ከተባሉት ነገር ውጪ ያደረጉ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ትምህርቱ በሰፊው አብራርቶ ይዘረዝራል ይህ ትምህርት ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ መካከል ባለ የሥራ ዘርፍ ፣ በቤተክርስቲያንና በመሣሠሉት የሃላፊነት ቦታዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተግባርና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጭምር በምን መንገድ ሊወጡት እንደሚገባ በሰፊው የሚያብራራ ፣ የሚያትትና የሚያስተምርም ነው ታድያ ይህንን ትምህርት አስተውለን እንደሚገባ ከተከታተልነው በተገቢው መንገድ እንደምንጠቀም ሕይወታችንም በዚሁ ቃል በብዙ እንደሚለወጥ እምነቴ ነው ውድ የቃሉ አድማጮች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እንግዲህ ይህን በቪዲዮ የሚለቀቀውን ትምህርት ከሰማችሁ በኋላ ለሌሎች ሊሰሙ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ሼር በማድረግ ትምህርቱን እንድታሰሙ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday 13 April 2016

(ትምህርት ሁለት) የትምህርቱ ርዕስ :- ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም ( ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ትን..ትምህርት ሁለት ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ ወቅታዊ እና ትምህርት አዘል መልዕክት ነው የትምህርቱ ርዕስ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም የሚል ሲሆን :---------------- የምንባቡ መነሻ ሃሳብ ደግሞ የኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት ውስጥ ኃይልን ስለመታጠቅ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ትምህርቶች መካከል የተወሰደና ጥቂቱን ሃሳብ የያዘ ነው ሙሉውን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት የማቀርበው ይሆናል በዚህ አጋጣሚ ግን የፓልቶክን አገልግሎት ለማታውቁ በየሳምንቱ ማክሰኞ በእኔ የሰዓት አቆጣጠር ከ 10 ፥ 30 ማለዳ ላይ ጀምሮ በዚሁ ሩም በእኔ በባርያው የሚተላለፍ ትምህርት ስላለ እርሱን እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናሁን ማሳሰብ እወዳለሁ ሩሙ ማለትም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ስለዚህ ጊዜ ያላችሁ ወገኖች በእነዚህ ሰዓታቶች ሁሉ እየገባችሁ መካፈል የምትችሉ መሆናችሁን ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ በመቀጠልም ወዳዘጋጀሁት የትምህርት ሃሳብ ስመጣ ይህንን ጸሎት ኤርምያስ እንዲህ ሲል የጸለየው ጸሎት ቢሆንም በትላንትናው ዘመን በኤርምያስ ብቻ ሳይሆን አሁንም ላይ ባለ ዘመንና እስከ ለዘላለሙም ከእግዚአብሔር ያለፈ ፣ ከእግዚአብሔርም የሚያቅት ምንም ነገር የሌለ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ይጠቁማል ለዚህም ነው እንግዲህ ኤርምያስ አሁንም በትንቢቱ አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ሲል የነገረን ትንቢተ ኤርምያስ 10 ፥ 6 የእግዚአብሔር ታላቅነት በየት በየት ቦታ እና ለምን ለምን ጉዳይ ተገለጠ ስንል ደግሞ በቪዲዮ የሚለቀቀው ትምህርት ስላለ እርሱ ሰፊውን ሃሳብ ይዞ ይመልስልናል ከዚህም ባሸገር የዚህ ትምህርታዊ መልዕክት ዋናውና አንኳሩ ሃሳብ እነዚህ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር እንደሌለ የተረዱ እና የተባሉትን ነገር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚቃኝ ሲሆን ከተባሉት ነገር ውጪ ያደረጉ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ትምህርቱ በሰፊው አብራርቶ ይዘረዝራል ይህ ትምህርት ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ መካከል ባለ የሥራ ዘርፍ ፣ በቤተክርስቲያንና በመሣሠሉት የሃላፊነት ቦታዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተግባርና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጭምር በምን መንገድ ሊወጡት እንደሚገባ በሰፊው የሚያብራራ ፣ የሚያትትና የሚያስተምርም ነው ታድያ ይህንን ትምህርት አስተውለን እንደሚገባ ከተከታተልነው በተገቢው መንገድ እንደምንጠቀም ሕይወታችንም በዚሁ ቃል በብዙ እንደሚለወጥ እምነቴ ነው ውድ የቃሉ አድማጮች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እንግዲህ ይህን በቪዲዮ የሚለቀቀውን ትምህርት ከሰማችሁ በኋላ ለሌሎች ሊሰሙ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ሼር በማድረግ ትምህርቱን እንድታሰሙ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ .

Monday 11 April 2016

(ትምህርት ሁለት)የትምህርቱ ርዕስ :- ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም ( ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ትንቢ..ትምህርት ሁለት ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ ወቅታዊ እና ትምህርት አዘል መልዕክት ነው የትምህርቱ ርዕስ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም የሚል ሲሆን :---------------- የምንባቡ መነሻ ሃሳብ ደግሞ የኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት ውስጥ ኃይልን ስለመታጠቅ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ትምህርቶች መካከል የተወሰደና ጥቂቱን ሃሳብ የያዘ ነው ሙሉውን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት የማቀርበው ይሆናል በዚህ አጋጣሚ ግን የፓልቶክን አገልግሎት ለማታውቁ በየሳምንቱ ማክሰኞ በእኔ የሰዓት አቆጣጠር ከ 10 ፥ 30 ማለዳ ላይ ጀምሮ በዚሁ ሩም በእኔ በባርያው የሚተላለፍ ትምህርት ስላለ እርሱን እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናሁን ማሳሰብ እወዳለሁ ሩሙ ማለትም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ስለዚህ ጊዜ ያላችሁ ወገኖች በእነዚህ ሰዓታቶች ሁሉ እየገባችሁ መካፈል የምትችሉ መሆናችሁን ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ በመቀጠልም ወዳዘጋጀሁት የትምህርት ሃሳብ ስመጣ ይህንን ጸሎት ኤርምያስ እንዲህ ሲል የጸለየው ጸሎት ቢሆንም በትላንትናው ዘመን በኤርምያስ ብቻ ሳይሆን አሁንም ላይ ባለ ዘመንና እስከ ለዘላለሙም ከእግዚአብሔር ያለፈ ፣ ከእግዚአብሔርም የሚያቅት ምንም ነገር የሌለ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ይጠቁማል ለዚህም ነው እንግዲህ ኤርምያስ አሁንም በትንቢቱ አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ሲል የነገረን ትንቢተ ኤርምያስ 10 ፥ 6 የእግዚአብሔር ታላቅነት በየት በየት ቦታ እና ለምን ለምን ጉዳይ ተገለጠ ስንል ደግሞ በቪዲዮ የሚለቀቀው ትምህርት ስላለ እርሱ ሰፊውን ሃሳብ ይዞ ይመልስልናል ከዚህም ባሸገር የዚህ ትምህርታዊ መልዕክት ዋናውና አንኳሩ ሃሳብ እነዚህ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር እንደሌለ የተረዱ እና የተባሉትን ነገር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚቃኝ ሲሆን ከተባሉት ነገር ውጪ ያደረጉ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ትምህርቱ በሰፊው አብራርቶ ይዘረዝራል ይህ ትምህርት ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ መካከል ባለ የሥራ ዘርፍ ፣ በቤተክርስቲያንና በመሣሠሉት የሃላፊነት ቦታዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተግባርና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጭምር በምን መንገድ ሊወጡት እንደሚገባ በሰፊው የሚያብራራ ፣ የሚያትትና የሚያስተምርም ነው ታድያ ይህንን ትምህርት አስተውለን እንደሚገባ ከተከታተልነው በተገቢው መንገድ እንደምንጠቀም ሕይወታችንም በዚሁ ቃል በብዙ እንደሚለወጥ እምነቴ ነው ውድ የቃሉ አድማጮች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እንግዲህ ይህን በቪዲዮ የሚለቀቀውን ትምህርት ከሰማችሁ በኋላ ለሌሎች ሊሰሙ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ሼር በማድረግ ትምህርቱን እንድታሰሙ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ አባዮናስ ጌታነህ .

Thursday 7 April 2016

የትምህርቱ ርዕስ :- ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም ( ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ትንቢተ ኤርምያስ 10 ...ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ ወቅታዊ እና ትምህርት አዘል መልዕክት ነው የትምህርቱ ርዕስ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም የሚል ሲሆን :---------------- የምንባቡ መነሻ ሃሳብ ደግሞ የኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት ውስጥ ኃይልን ስለመታጠቅ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ትምህርቶች መካከል የተወሰደና ጥቂቱን ሃሳብ የያዘ ነው ሙሉውን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት የማቀርበው ይሆናል በዚህ አጋጣሚ ግን የፓልቶክን አገልግሎት ለማታውቁ በየሳምንቱ ማክሰኞ በእኔ የሰዓት አቆጣጠር ከ 10 ፥ 30 ማለዳ ላይ ጀምሮ በዚሁ ሩም በእኔ በባርያው የሚተላለፍ ትምህርት ስላለ እርሱን እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናሁን ማሳሰብ እወዳለሁ ሩሙ ማለትም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ስለዚህ ጊዜ ያላችሁ ወገኖች በእነዚህ ሰዓታቶች ሁሉ እየገባችሁ መካፈል የምትችሉ መሆናችሁን ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ በመቀጠልም ወዳዘጋጀሁት የትምህርት ሃሳብ ስመጣ ይህንን ጸሎት ኤርምያስ እንዲህ ሲል የጸለየው ጸሎት ቢሆንም በትላንትናው ዘመን በኤርምያስ ብቻ ሳይሆን አሁንም ላይ ባለ ዘመንና እስከ ለዘላለሙም ከእግዚአብሔር ያለፈ ፣ ከእግዚአብሔርም የሚያቅት ምንም ነገር የሌለ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ይጠቁማል ለዚህም ነው እንግዲህ ኤርምያስ አሁንም በትንቢቱ አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ሲል የነገረን ትንቢተ ኤርምያስ 10 ፥ 6 የእግዚአብሔር ታላቅነት በየት በየት ቦታ እና ለምን ለምን ጉዳይ ተገለጠ ስንል ደግሞ በቪዲዮ የሚለቀቀው ትምህርት ስላለ እርሱ ሰፊውን ሃሳብ ይዞ ይመልስልናል ከዚህም ባሸገር የዚህ ትምህርታዊ መልዕክት ዋናውና አንኳሩ ሃሳብ እነዚህ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር እንደሌለ የተረዱ እና የተባሉትን ነገር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚቃኝ ሲሆን ከተባሉት ነገር ውጪ ያደረጉ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ትምህርቱ በሰፊው አብራርቶ ይዘረዝራል ይህ ትምህርት ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ መካከል ባለ የሥራ ዘርፍ ፣ በቤተክርስቲያንና በመሣሠሉት የሃላፊነት ቦታዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተግባርና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጭምር በምን መንገድ ሊወጡት እንደሚገባ በሰፊው የሚያብራራ ፣ የሚያትትና የሚያስተምርም ነው ታድያ ይህንን ትምህርት አስተውለን እንደሚገባ ከተከታተልነው በተገቢው መንገድ እንደምንጠቀም ሕይወታችንም በዚሁ ቃል በብዙ እንደሚለወጥ እምነቴ ነው ውድ የቃሉ አድማጮች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እንግዲህ ይህን በቪዲዮ የሚለቀቀውን ትምህርት ከሰማችሁ በኋላ ለሌሎች ሊሰሙ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ሼር በማድረግ ትምህርቱን እንድታሰሙ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ አባዮናስ ጌታነህ

Wednesday 6 April 2016

የትምህርቱ ርዕስ :- ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም ( ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ትንቢተ ኤርምያስ 10 ..ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ ወቅታዊ እና ትምህርት አዘል መልዕክት ነው የትምህርቱ ርዕስ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር የለም የሚል ሲሆን :---------------- የምንባቡ መነሻ ሃሳብ ደግሞ የኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ትንቢተ ኤርምያስ 32 ፥ 17 ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት ውስጥ ኃይልን ስለመታጠቅ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ትምህርቶች መካከል የተወሰደና ጥቂቱን ሃሳብ የያዘ ነው ሙሉውን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት የማቀርበው ይሆናል በዚህ አጋጣሚ ግን የፓልቶክን አገልግሎት ለማታውቁ በየሳምንቱ ማክሰኞ በእኔ የሰዓት አቆጣጠር ከ 10 ፥ 30 ማለዳ ላይ ጀምሮ በዚሁ ሩም በእኔ በባርያው የሚተላለፍ ትምህርት ስላለ እርሱን እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናሁን ማሳሰብ እወዳለሁ ሩሙ ማለትም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብሮድ ካስት የፓልቶክ አገልግሎት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ስለዚህ ጊዜ ያላችሁ ወገኖች በእነዚህ ሰዓታቶች ሁሉ እየገባችሁ መካፈል የምትችሉ መሆናችሁን ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ በመቀጠልም ወዳዘጋጀሁት የትምህርት ሃሳብ ስመጣ ይህንን ጸሎት ኤርምያስ እንዲህ ሲል የጸለየው ጸሎት ቢሆንም በትላንትናው ዘመን በኤርምያስ ብቻ ሳይሆን አሁንም ላይ ባለ ዘመንና እስከ ለዘላለሙም ከእግዚአብሔር ያለፈ ፣ ከእግዚአብሔርም የሚያቅት ምንም ነገር የሌለ መሆኑን የክፍሉ ሃሳብ ይጠቁማል ለዚህም ነው እንግዲህ ኤርምያስ አሁንም በትንቢቱ አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ሲል የነገረን ትንቢተ ኤርምያስ 10 ፥ 6 የእግዚአብሔር ታላቅነት በየት በየት ቦታ እና ለምን ለምን ጉዳይ ተገለጠ ስንል ደግሞ በቪዲዮ የሚለቀቀው ትምህርት ስላለ እርሱ ሰፊውን ሃሳብ ይዞ ይመልስልናል ከዚህም ባሸገር የዚህ ትምህርታዊ መልዕክት ዋናውና አንኳሩ ሃሳብ እነዚህ ከእግዚአብሔር የሚያቅት ነገር እንደሌለ የተረዱ እና የተባሉትን ነገር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚቃኝ ሲሆን ከተባሉት ነገር ውጪ ያደረጉ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ትምህርቱ በሰፊው አብራርቶ ይዘረዝራል ይህ ትምህርት ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ መካከል ባለ የሥራ ዘርፍ ፣ በቤተክርስቲያንና በመሣሠሉት የሃላፊነት ቦታዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተግባርና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጭምር በምን መንገድ ሊወጡት እንደሚገባ በሰፊው የሚያብራራ ፣ የሚያትትና የሚያስተምርም ነው ታድያ ይህንን ትምህርት አስተውለን እንደሚገባ ከተከታተልነው በተገቢው መንገድ እንደምንጠቀም ሕይወታችንም በዚሁ ቃል በብዙ እንደሚለወጥ እምነቴ ነው ውድ የቃሉ አድማጮች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እንግዲህ ይህን በቪዲዮ የሚለቀቀውን ትምህርት ከሰማችሁ በኋላ ለሌሎች ሊሰሙ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ሼር በማድረግ ትምህርቱን እንድታሰሙ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ .

Tuesday 5 April 2016

ትምህርት ስድስት ፦ በተስፋ ቃል መፈተን ዕብራውያን 11 ፥ 17 _ 19 ፤ መዝሙር ( 105 )፥ 16 _ 19 Pa...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ በተስፋ ቃል መፈተን በተስፋ ቃል ከተፈተኑት መካከል ፦ 1ኛ) አብርሃም ነው አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው ይለናል ዕብራውያን 11 ፥ 17 እና 18 ታድያ የአብርሃም ፈተና እንዲሁ ይስሐቅን በእምነት የማቅረብ ፈተና አይደለም በውስጡ ብዙ የመስዋዕትነት ሕይወት አለው ይህንንም በዘፍጥረት 22 ፥ 10 ጀምሮ እስከ 19 ቊጥር ድረስ የተጻፈልን በመሆኑ ይህንን ሁኔታ በዚሁ ክፍል በዝርዝር እናገኘዋለን እንዲሁም በዘፍጥረት 12 ፥ 10 _ 20 ላይ በምድር ራብ በሆነ ጊዜ አብራም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ መውረዱን የክፍሉ ሃሳብ ይነግረናል ይህ ራብ ደግሞ የጸና ነበርና ወደ ግብጽም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እህቴ ነሽ በማለትና እህቱም ነኝ እንድትል ሦራን በማሳመን ከግብጽ ሰዎች አስደንጋጭ ሞት ሚስቱ በሆነችው ነገር ግን እህቱ ነኝ በዪ ባላት በሦራ ምክንያት የማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ሦራ ለግብጹ ንጉሥ ለፈርኦን ሚስት ልት ሆን የተወሰደች በመሆንዋ እውነተኛውን ጉዳይ የሚያውቀው እግዚአብሔር በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የአብራምን ሚስት ሦራን ለዚሁ ለአብራም አተረፈለት ስለዚህም ንጉሥ ፈርኦን አብራምን ጠርቶ ይህ ያደረግህብኝ ምንድር ነው ? እርስዋ ሚስት እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም ? ለምንስ፦ እኅቴ ናት አልህ ? እኔ ሚስት ላደርጋት ወስጄአት ነበር አሁንም ሚስትህ እነኋት ይዘሃት ሂድ ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው ይለናል 2ኛ) ዮሴፍ ነው በመዝሙር 104 (105)፥ 16 _ 19 በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ በፊታቸው ሰውን ላከ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ እያለ ይናገራል እስር ቤት እግረ ሙቅም ሆነ ሰንሰለት መራርነት ያለበት የጨለማ ሕይወት ነው ይሁን እንጂ ታድያ እግዚአብሔር በዚያ ስፍራ ለዮሴፍ ምሕረትን ያበዛለት ቢሆንም ዮሴፍ ግን ይህንኑ የተስፋ ቃል በመጠበቅ ምክንያት በሕይወቱ የተፈተነ ነበር ዘፍጥረት 39 ፥ 21 ፤ ዘፍጥረት 40 ፥ 15 ፤ ዘፍጥረት 40 ፥ 1 _ 23 3ኛ ) አብርሃምና ከአብርሃም በኋላ የመ ጡ የእምነት አባቶች ፈተና መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ስለ አብርሃም ሲናገር አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና ይለናል ዘፍጥረት 11 ፥ 8 _ 10 ከአብርሃም በኋላ ስላሉ የእምነት አባቶች ሲናገር ደግሞ እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና ይለናል ዕብራውያን 11 ፥ 13 _ 16 ይመልከቱ ታድያ እነዚህ አባቶች በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ፍጹማን የሆኑት በእኛ ነው ይህም እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና ዕብራውያን 11 ፥ 39 እና 40 ን በድጋሜ ይመልከቱ 4ኛ ) የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ እግዚአብሔር ፈቃዱ አይለወጥም ስለዚህም ይህን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ጌታ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ በመካከል በመሃላ ገብቶአል ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ በማለት የዕብራውያን ጸሐፊ ዘግቦልናል ዕብራውያን 6 ፥ 17 _ 20 በተስፋ ቃል ስንፈተን ፦ ሀ) በመጠበቅያችን ወይንም በማማችን ላይ መቆም ያስፈልገናል ዕንባቆም 2 ፥ 1 _ 3 ፤ ዕብራውያን 10 ፥ 37 _ 39 ለ) መጽናት ያስፈልገናል ዕብራውያን 10 ፥ 36 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 11 ፥ 2 እና 3 ፤ ራዕይ 22 ፥ 12 እና 13 ፣ 20 ሐ ) መትጋት ያስፈልገናል ዕብራውያን 6 ፥ 9 _ 12 ፤ የሉቃስ ወንጌል 12 ፥ 35 _ 48 መ) ለአንዳንዶች የተስፋውን ቃል አምኖና ከሩቅ ተሳልሞ መሞት ቢሆንም ለሌሎች ግን የተስፋውን ቃል ማግኘት ነበር ዕብራውያን 11 ፥ 13 ፣ 33 ቅዱሳን ወገኖች ከዚህ ጽሑፍ ባሻገር ይህንኑ ትምህርት በብዙ ሊያብራራ በቪዲዮ የተለቀቀ ትምህርት ስላለን ይህንኑ ትምህርት እየገባችሁ በመከታተል ለሌሎችም እንድታሰሙ ሼር እንድታደርጉ ከታላቅ አክብሮት ጋር በትሕትና እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ፣ ኑሮአችሁንና ሕይወታችሁን ሁሉ ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ