Thursday, 11 January 2018

የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Challenges ) ክፍል ስድስት ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ?የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Challenges ) ክፍል ስድስት ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ? ነቢይ ማለት ከእግዚአብሔር የተላከ ማለት ሲሆን መልዕክተኛ እንደመሆኑ መጠን ከዚሁ ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ ለሕዝብ የሚናገር ማለት ነው ( ዘጸአት 7 ፥ 1 እና 2 ፣ ሆሴዕ 12 ፥ 14 ) በነቢይነትም ሆነ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ጥሪ ውስጥ ገብተው ማገልገል ለሚፈልጉ የወንጌላውያን አማኞችም ሆነ ለኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን የተላለፈ ትምህርት ( ቊጥር 1 ) የተወደዳችሁ ወገኖች እንግዲህ በቀጥታ ወደ ትምህርቱ ፍሬ ሃሳብ ስንሄድ በዚሁ ቃል መሠረት ትምህርቱ በነቢያቱ ላይ የሚያጠነጥን ይምሰል እንጂ መላክን በተመለከተ የተላኩም ሆኑ ወደፊትም የሚላኩ ነቢያቱ ብቻ ሳይሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል ወደሰዎች የሚያመጡ የቃሉ አገልጋዮችም ልዑካን ናቸው ( ሮሜ 10 ፥ 14 _ 17 ) ይሁን እንጂ ታድያ አሁን ላይ በነቢያቱም ሆነ በቃሉ አገልጋዮች በኩል እየተሰጠ ያለ አገልግሎት ቃሉን የተከተለና መልኩን የጠበቀ ካለመሆኑ የተነሳ በእግዚአብሔር ስም እየተተነበየ ያለው ትንቢቱም ሆነ ስብከቱ መታነጽያ መሆኑ ቀርቶ የመድረክ ላይ መደባደብያና ማደባደብያ ፣ ትዳርን ሳይቀር መፍቻና ማፋቻ በአጠቃላይ ቤተሰብን መበተኛና ጓደኛንም ከጓደኛ መለያያ ማለያያም እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሮአል ከዚህ የተነሳ ሕዝባችንም ሚዛኑን የጠበቀና መጽሐፍቅዱስን ያማከለ ትንቢትም ሆነ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ካለማግኘቱ የተነሳ የመጡትን ትንቢቶችም ሆነ መልዕክቶች ሰምቶ ተጠቃሚ ከሚሆን ይልቅ ለሌላው የሰማና የሚሰማ ሆኖ በመቅረብ ስማልኝማ ፣ ስሚልኝማ ልክ ልኩን ፣ ልክ ልኳን ነገረልኝ እኮ ሴትም ከሆነች አገልጋይዋ ነገረችልኝ እኮ በማለት አብዛኛው ምዕመናችንም ሆነ የቃሉ አገልጋዮችና ነቢያቱም ጭምር በአገልግሎትና በመልዕክተኝነት ስም መስሎ በታየን ፣ ይሆናል ብለን ባመንበትም ነገር ሁሉ ላይ ቊጭታችንን ልንወጣ የልባችንንም ምኞት ልንፈጽም እየተውተረተርን ያለንና እንቅልፋችንን አጥተን የምናድርም ብዙዎች ነን የእግዚአብሔር አገልግሎት ግን መደባደብያና ሌላውንም ማጥቂያ ፣ የግል ጉዳዮቻችንንም ማስፈጸምያ እና ማሟያ አይደለም ውድ ወገኖቼ ሆይ ለዚሁ ሃሳቤ ድጋፍ የሚሆነኝን በነህምያ 6 ፥ 10 _ 14 ላይ ነህምያን፣ ለነህምያም ትንቢት እንዲያመጣ በሰንባላጥና በጦቢያ ተገዝቶ ትንቢት የተናገረውን የሐሰተኛውን ነቢይ የሸማያን ትንቢትም ሆነ ነህምያ የሰጠውን ምላሽ ፣ የወሰደውንም የሕይወት አቋም ከክፍሉ በሰፊው ተመልክተናል ታድያ ይህንን አስመልክቶ የዛሬዎቹ አገልጋዮቻችን ምን ሊሆኑ እንደሚገባ ፣ ለሕዝባችንም የሚሰጡት ትምህርት ምንና እንዴት መሆን እንዳለበት ትምህርቱ ይጠቁማል ቅዱሳን እንግዲህ ጊዜ ወስዳችሁ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ እኔም እርግጠኛ በመሆን በዚህ ትምህርት ብዙዎቻችን ተጠቃሚዎች እንደምንሆን አምናለሁ ትምህርቱ ይቀጥላል ተባረኩልኝ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

ስለ ሕግ በመጽሐፍቅዱስ ተጠቅሰው ስላሉ በዓላትና ኦርቶዶክሳዊ በዓላት አከባበር የተሰጠ በመረጃ የተደገፈ መጽ... ስለ ሕግ በመጽሐፍቅዱስ ተጠቅሰው ስላሉ በዓላትና ኦርቶዶክሳዊ በዓላት አከባበር የተሰጠ በመረጃ የተደገፈ መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርት ( ክፍል አንድ ) ፈጣን ተሃድሶ ለኦርቶዶክስ ተአምረ ማሪያም ከክርስቶስ ለይቶን የኖረ ወንጀለኛ መጽሐፍ እመቤታችን በዓላቶችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ( 33 ) ናቸው እነዚህን በዓላቶች እንደ እሁድ ሰንበት አድርገው ይቁጠሩዋቸው። ከዓመት እስከ ዓመት እስከዘ ለዓለም ምንም ስራ አይስሩባቸው፤ ( የተአምረ ማርያም መቅድም ቁ፡32_34 ) መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) ስለ ምስጋና የተናገረው ትርጉም ፦ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆንሽ ቅድስት ማርያም ሆይ ጣፋጭ በሆነው በስምሽ መታሰብያ ያማረ በሆነው በደምሽ ፍሬም እንደሰታለን ( ኲሎሙ ዘእግዝእትነ ማርያም ከሚባል ክፍል _ ገጽ 105 ) መጽሐፍቅዱሳችን ስለ ቤዛነት የተናገረው እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም ( የማርቆስ ወንጌል 10 : 45 ) የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም ( ዕብራውያን 9 : 12 ) በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ ( ሮሜ 3 : 24 ) መጽሐፍቅዱሳችን ስለ በዓላት የተናገረው እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2 : 16 ስለዚህ ማንን እንስማ ? ማንን እንቀበል ? የትኛውንስ እንመን ?መጽሐፍ ቅዱስን ? ወይንስ ተአምረ ማርያምንና የሰዓታት መጽሐፍን ?መልሱን ለአድማጮች ብለናል ተባረኩ

Tuesday, 9 January 2018

የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Cchallenges ) ክፍል አምስት በነቢያት አገልግሎት ዙርያ ( ቁጥር 15 )የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Cchallenges ) ክፍል አምስት በነቢያት አገልግሎት ዙርያ ( ቁጥር 15 ) ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ .............የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረበዳ መጣ የማቴዎስ ወንጌል 3 : 4 ፤ የሉቃስ ወንጌል 3 ፥ 1 _ 6 የዮሐንስ መጥምቁ ሕይወቱ ገዳማዊ ሕይወትን ያመለክታልን ? ዮሐንስ መጥምቁስ ገዳማዊ ሕይወትን ያበረታታልን ? ገዳማዊ ሕይወትን የሚያበረታቱ የገድላትና የድርሳናት ጽሑፎች በእግዚአብሔር ቃል ሲፈተሹ የሚል መሪ ሃሳብ የያዘ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ፦—————— ትምህርቱ ከመጽሐፍቅዱስ ሌላ የክርስቶስን ብቸኛ አዳኝነት የሚገልጹ ከመጽሐፍቅዱሳችንም ጋር በተያያዥነት አስረጅ ሆነው የቀረቡ የቤተክርስቲያኒቱ መጻሕፍት በትንታኔና በቤተክርስቲያኒቱ የግዕዝ ቋንቋ ታግዘው የተጠቀሱበት እውነት ይገኝበታል ከዚህም ሌላ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ በገድላቸው ላይ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ኃጢአት አሳይቶኝ በባሕር ውስጥ ለመቶ ዓመት ቁልቁል ተዘቅዝቄ ጸለይኩላት ላሉት ሃሳባቸው ዛሬም በኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በወንጌላውያኑም አብያተክርስቲያናት ያሉ ነቢያትና አገልጋዮች ለታያቸው በደልና ኃጢአት ምላሽ ሊሰጡ ቊልቊል ተዘቅዝቀው ጸለዩ ባንልም ታየኝ ተገለጠልኝ በሚል ሰበብ ብቻ አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል ከአቡዬ ገብረ መንፈስቅዱስ ባልተናነሰ ሁኔታ እየፈጸሙት ስላለው ስሕተት ማስተካከያና እርማት በመስጠት ትምህርቱ ግልጽ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ ትንታኔና መረጃን ያቀርባል ስለዚህ ቅዱሳን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል መማር የምትፈልጉ ወገኖች በሙሉ መልዕክቱን መስማታችሁ ለሕይወታችሁ ወሳኝ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ ተከታተሉ እላለሁኝ ተባረኩ