Saturday, 6 August 2016

ጸሎትና መጽሐፍቅዱስን ማንበብ

ጸሎትና መጽሐፍቅዱስን ማንበብ 







አንዱና ቁልፉ የክርስቲያን ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር በየቀኑ ጊዜ ማጥፋት ነው መጽሐፍቅዱሳዊ ክርስትና ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት ማግኘት ማለት ነው በእርግጠኝነት በጥልቀት ለማደግ ለዚህ ነገር ጊዜ ማጥፋት አለብን በእርግጠኛነት እና በመደበኛነት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ማድረግ አለብን ይህንን ለማድረግ የተመረጠው መንገድ መጸለይና መጽሐፍቅዱስን ማንበብ ነው 


እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው ነው 






በዘፍጥረት 1 27 መሠረት እግዚአብሔር በመልኩ ምን ፈጠረ ?




በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ስንል ምን ማለታችን  ነው ?



በቆላስያስ 1 15  እና 16  የሰውን ዘር ለምን ፈጠረው ?

የውሃ ጥምቀት

የውሃ ጥምቀት 











ሰው ለምን መጠመቅ ያስፈልገዋል ኢየሱስ ትእዛዝ ሰጥቶናል ምሳሌም ሆኖናል ይህ የመታዘዝ እርምጃ እና የአሁንዋ ቤተ ክርስቲያን ልትለማመደው የሚገባ እውነት ነው የውሃ ጥምቀት ሕዝባዊና ውጪያዊ ሥርዓት የሆነ እግዚአብሔር በሕይወታችን የሚያደርገው ውስጣዊ ሥራ ነው 


የማቴዎስ ወንጌል 3 1 _ 17  እንመልከት 


በቊጥር 6 መሠረት በውሃ ጥምቀት ከዚህ ሕዝብ ጋር አብሮ የተጫወተው ምንድነው ?




በቊጥር 8 መሠረት ንስሐን በመከታተል ፍሬ ማፍራት ይቻላል ስንል ምን ማለታችን ነው ?




በቁጥር 11 መሠረት ዮሐንስ በውሃ ሲያጠምቅ ምን አለ ?




ኃጢአትን ሳያደርግ ኢየሱስ የተጠመቀበት ምክንያት ምን ነበር ?




ኢየሱስ ሊጠመቅ በተገኘበት ጊዜ የሥላሴ አባላት ስንት ነበሩ ?




በማቴዎስ ወንጌል 28 19 _ 20 መሠረት ወንጌልን ያመኑ ሰዎች እንዲጠመቁ ማን አዘዘ ?




በሐዋርያት ሥራ 2 37 _ 41 መሠረት የውሃ ጥምቀት የተሠራው ወይም የተደነገገው መቼ ነበር ?





ሮሜ 6 3 _ 4 እናንብብ 




በምን መንገድ የውሃ ጥምቀት ለኢየሱስ ክርስቶስ የሞት የመቃብርና የትንሣኤ ምልክት ሆኖ ተፈቀደ ?





ስንደመድመው ንስሐ የገባው ወይም የሚገባው ማንኛውም ሰው ከኃጢአቱ ተመልሶ ንስሐ ለመግባት ቢጠይቅ እንደገናም በኢየሱስ ቢያምንና በውሃ ቢጠመቅ የውሃ ጥምቀት እግዚአብሔርን ለማስደሰት የመታዘዝ እርምጃ ነው

Sunday, 3 July 2016

የመልዕክት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ሲቆጣ የተቆጣው ሳሙኤልና ቀጣዩ እርምጃው ( 1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 10 _ ፍጻሜ ) የመልዕክት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ሲቆጣ የተቆጣው ሳሙኤልና ቀጣዩ እርምጃው ( 1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 10 _ ፍጻሜ ) እግዚአብሔር ሲቆጣ ካልተቆጣን ሲያጽናና ማጽናናት አንችልም እግዚአብሔር ደግሞ ተቆጡ ብቻ ሳይሆን አጽናኑ ሕዝቤን አጽናኑም ነው ያለን ኢሳይያስ 40 ፥ 1 እና 2 ታድያ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያጽናኑ ሰዎች የሁልጊዜ አጽናኞች ብቻ ሳይሆኑ እግዚአብሔር ተቆጥቶም ሲያገኙ ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የሚቆጡ ናቸው እግዚአብሔር ሲቆጣ የማይቆጡ ሰዎች ግን የካህኑ የኤሊን ዘመን መንፈስ የሚከተሉ በመሆናቸው ከእግዚአብሔር ቤት ሳይቀር የሚቆረጡበትና ክንዳቸውም የሚሰበርበት ዘመን መምጣቱ አይቀርም ጌታ እግዚአብሔር ደግሞ በቁጣችሁ ላይ ጸሐይ አይግባ አለን እንጂ አትቆጡ አላለንም ይልቁንም ቃሉን እንድንሰብክ በጊዜውም አለጊዜውም እየጸናን ፈጽመን እየታገስንና እያስተማርንም እንድንዘልፍ እንድንገስጽና እንድንመክርም ነው የሚነግረን ስለዚህ ይህንን የቃሉን እውነት ተከትለን እኛም እግዚአብሔር ያለውን በዘመናችን ያለከልካይ እናደርጋለን 2ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 1 _ 5 ቅዱሳን ወገኖች መልዕክቱ እንግዲህ በነዚህና በመሣሠሉት ሃሳቦች ዙርያ ያጠነጠነ በመሆኑ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ Joshua Breakthrough Apostolic Ministry

July 2, 2016የመልዕክት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ሲቆጣ የተቆጣው ሳሙኤልና ቀጣዩ እርምጃው ( 1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 10 _ ፍጻሜ ) እግዚአብሔር ሲቆጣ ካልተቆጣን ሲያጽናና ማጽናናት አንችልም እግዚአብሔር ደግሞ ተቆጡ ብቻ ሳይሆን አጽናኑ ሕዝቤን አጽናኑም ነው ያለን ኢሳይያስ 40 ፥ 1 እና 2 ታድያ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያጽናኑ ሰዎች የሁልጊዜ አጽናኞች ብቻ ሳይሆኑ እግዚአብሔር ተቆጥቶም ሲያገኙ ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የሚቆጡ ናቸው እግዚአብሔር ሲቆጣ የማይቆጡ ሰዎች ግን የካህኑ የኤሊን ዘመን መንፈስ የሚከተሉ በመሆናቸው ከእግዚአብሔር ቤት ሳይቀር የሚቆረጡበትና ክንዳቸውም የሚሰበርበት ዘመን መምጣቱ አይቀርም ጌታ እግዚአብሔር ደግሞ በቁጣችሁ ላይ ጸሐይ አይግባ አለን እንጂ አትቆጡ አላለንም ይልቁንም ቃሉን እንድንሰብክ በጊዜውም አለጊዜውም እየጸናን ፈጽመን እየታገስንና እያስተማርንም እንድንዘልፍ እንድንገስጽና እንድንመክርም ነው የሚነግረን ስለዚህ ይህንን የቃሉን እውነት ተከትለን እኛም እግዚአብሔር ያለውን በዘመናችን ያለከልካይ እናደርጋለን 2ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 1 _ 5 ቅዱሳን ወገኖች መልዕክቱ እንግዲህ በነዚህና በመሣሠሉት ሃሳቦች ዙርያ ያጠነጠነ በመሆኑ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ Joshua Breakthrough Apostolic Ministry