Sunday, 3 July 2016
July 2, 2016የመልዕክት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ሲቆጣ የተቆጣው ሳሙኤልና ቀጣዩ እርምጃው ( 1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 10 _ ፍጻሜ ) እግዚአብሔር ሲቆጣ ካልተቆጣን ሲያጽናና ማጽናናት አንችልም እግዚአብሔር ደግሞ ተቆጡ ብቻ ሳይሆን አጽናኑ ሕዝቤን አጽናኑም ነው ያለን ኢሳይያስ 40 ፥ 1 እና 2 ታድያ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያጽናኑ ሰዎች የሁልጊዜ አጽናኞች ብቻ ሳይሆኑ እግዚአብሔር ተቆጥቶም ሲያገኙ ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የሚቆጡ ናቸው እግዚአብሔር ሲቆጣ የማይቆጡ ሰዎች ግን የካህኑ የኤሊን ዘመን መንፈስ የሚከተሉ በመሆናቸው ከእግዚአብሔር ቤት ሳይቀር የሚቆረጡበትና ክንዳቸውም የሚሰበርበት ዘመን መምጣቱ አይቀርም ጌታ እግዚአብሔር ደግሞ በቁጣችሁ ላይ ጸሐይ አይግባ አለን እንጂ አትቆጡ አላለንም ይልቁንም ቃሉን እንድንሰብክ በጊዜውም አለጊዜውም እየጸናን ፈጽመን እየታገስንና እያስተማርንም እንድንዘልፍ እንድንገስጽና እንድንመክርም ነው የሚነግረን ስለዚህ ይህንን የቃሉን እውነት ተከትለን እኛም እግዚአብሔር ያለውን በዘመናችን ያለከልካይ እናደርጋለን 2ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 1 _ 5 ቅዱሳን ወገኖች መልዕክቱ እንግዲህ በነዚህና በመሣሠሉት ሃሳቦች ዙርያ ያጠነጠነ በመሆኑ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ Joshua Breakthrough Apostolic Ministry
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment