Aba Yonas Getaneh Asfaw ጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Tuesday, 11 February 2020

ጳውሎስ እስከ ሶስተኛው ሰማይ አረገ ማርያም ተገለጠችለት አብርሃም ይስሃቅና ያዕቆብ ለማርያም ሰገዱ ነገረ ማርያም የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 9  ተፍሲር በነገረ ማርያም ———-7፤ ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ።ከላይ ለተጠቀሰው የመፅሐፉ ክፍል በነገረ ማርያም የተሰጠ ማብራሪያ 7 በመሬት ላይ ወድቄ እየተፍገመገምኩ ሳለሁ እኔን #ጭንጋፍ የሆንኩ ሰው መላዕክት መጠው አፅናኑኝ አንስተው #እስከ #ሶስተኛው #ሰማይ #አሳረጉኝ 8 በዚያ ግዜ የደም ግባቷ እንደ ፀሀይ የሚያበራ ድንግል ከሩቅ ስትመጣ ተመለከትኩ ከሷም ጋር ሁለት መቶ መላዕክት በፊትና በኃላ ሆነው እየዘመሩ መጡ 9 ከኔም ጋር ያለውን መልአክ ይህች ማናት  በዚህ ያህል ክብር ከብራ የምትመጣ አልሁት 10 መልአኩም ይህች አንተ የምታሳድዳቸው የናዝሬቱ እየሱስ ክርስቶስ እናት እናቱ ማርያም ናት አለኝ 11 በዚያ ግዜ ወደኔ መጣችና ሰላም ካለችኝ በኃላ  ሳውል ሳውል ልጄን የናዝሬቱን እየሱስ ለምና ታሳድደዋለህ አለችኝ የሾለውን  ብረት ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል 12 እኔም እየፈራሁና እየተንቀጠቀጥኩ እመቤቴ ሆይ ስለ ሃጢያቴ ምን አደርግ ዘንድ ይገባኛል የሰው ደም እያፈሰስኩ ወንጀለኛ ሆኛለሁ አሁንም እመቤቴ ሆይ #ሀጢያቴን #ይቅር #በይልኝ እነሆ አንች እናቱ እንደሆንሽ ተገልፃልኛልና 19 ይህች ድንግል እንዲህ እያለች በምትነግረኝ ግዜ እነሆ ፊታቸው ብሩህ የሆኑ  ሶስት ሰዎች መጡ 20 ከኔ ጋር የነበሩ መላዕክም እኒህ እነማን ናቸው ብየ ጠየቅኩት 21 እሱም እኒህ አባቶች አብርሃም ይስሃቅ ያዕቆብ ይባላሉ አለኝ 22 እነሱም መጠው ለመቤታች   ሰገዱ እኔንም መጠው ሳ ም አሉኝ እኔም እጅ ነሳኃቸው እናም እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች መልሱልን ጳውሎስ የረሳውን ካቦርት በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ሲፅፍ እንዴት ይህን ታሪክ መፅሐፉ ላይ ሳይፅፈው ቀረ ?ማርያም ሐጢያትን ይቅር ማለት ትችላለች ስግደትስ ለሷ ይገባል?የሐዋሪያት ስራ ላይ ለጳውሎስ ተገለጠለት የተባለው እየሱስ ነው እዚህ ታሪክ ላይ ግን ማርያም ነው የተገለጠችለት እስኪ እናስታርቃቸው?

Date: October 10, 2016Author: Murtaz Ahmed

Share this:


Yonas Asfaw at 16:01
Share

No comments:

Post a Comment

‹
›
Home
View web version

About Me

Yonas Asfaw
View my complete profile
Powered by Blogger.