Monday, 8 July 2019
ርዕስ፦ በሰዎች ካልተወሰንክና ራስህንም ካልወሰንክ እግዚአብሔር ስላንተ የተናገረውን አንተንም የተመለከተበትን እይታ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ መልዕክት እንደሰማችሁት ዳዊትን አባቱ ታናሽ ነው በጎችን ይጠብቃል አለው ፣ የወንድሞቹንም ደህንነት እንዲጠይቅና ወሬንም እንዲያመጣለት ላከው :: የዳዊት ታላቅ ወንድም ኤልያብ ደግሞ በጎችን ለማን ተውካቸው ? የልብህን ኩራት አይቻለው ሲል ተቆጣው ፣ አሳነሰው :: ሳኦል ደግሞ አንተ ብላቴና ነህ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመዋጋት ትሔድ ዘንድ አትችልም አለው :: ጎልያድም ዳዊትን ትኩር ብሎ አየውና ብላቴና መልኩም ያማረ ነበርና ናቀው :: ከዳዊት የድሉ መልስ በኋላ ደግሞ ሳኦል ዮናታንን የሞት ልጅ ነውና ልከህ አስመጣው አለው ፣ ይህም አልበቃ ብሎት ዳዊትን አዋረደው ፣ በዚህ ሁሉ አልሸነፍ ሲል ደግሞ ሳኦል ዳዊትን አጥብቆ ፈራው ፣ ዕድሜውንም ሁሉ ለዳዊት ጠላት ሆነው :: እግዚአብሔር ግን ዳዊትን እንደ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከተው :: የተወደዳችሁ ወገኖቼ እግዚአብሔር እንደ ባለ ማዕረግ ሰው ነውና የሚመለከተን ሰዎች በሚያዩን ዓይን ሳይሆን እግዚአብሔር በሚያየን ዓይን ራሳችንን እንመልከት :: በሐዲሱ ኪዳንም እንደ ባለማዕረግ ሆነን የታየንበት እውነት ወደ ክብር የመጣንበት እውነት ነው :: መጽሐፍቅዱስ እንዲህ ይለናል ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና ስለዚህም ምክንያት፦ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም፦ እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦ እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና ይለናል ዕብራውያን 2 ፥ 10 - 18 ተባረኩ የቃሉ አገልጋይ አባ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment