በ1980 ዕትም መጽሐፍና በ2000 ዕትም ባሉ የአዋልድ መጻሕፍት መካከል ያሉ ልዩነቶች በ1980 ዕትም መጽሐፍና በ2000 ዕትም ባሉ የአዋልድ መጻሕፍት መካከል ያሉ ልዩነቶች የሁለቱ መጻሕፍት ልዩነት የሚጀምረው ከማውጫው ነው በ1980 ዕትም መጽሐፍ መጽሐፈ አስቴር ሁለት ጊዜ ታተመ በ2000 ዕትም መጽሐፈ አስቴር አንድ ጊዜ ብቻ ታተመ ( አንዱን ብቻ ወስዶአል ) በ1980 ዕትም መጽሐፍ ጸሎተ ምናሴ ፣ መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅና ተረፈ ዳንኤል ታትመው ፣ ተጽፈውና ተካተው ሲገኙ በ2000 ዕትም መጽሐፍ እነዚህ መጻሕፍት የሉም በ2000 ዕትም መጽሐፍ ተረፈ ባሮክ ተጽፎና ታትሞ ይገኛል በ1980 ዕትም መጽሐፍ ግን ተረፈ ባሮክ የለም ከዚህ በመነሳት ወደ ቆጠራው ሲገባ በሁለቱ መጻሕፍት መካከል የቁጥር ልዩነት መኖሩን ለመረዳት እንችላለን የትምህርቱ አቅራቢ: —— አባ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment