Tuesday, 20 September 2016

M2U00296 ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት በሚለው ዋና አርዕስት ሥር ፦ ከድንጋይ አፍልቆ አጠጣቸው እርሱም...ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ምዕራፍ 2 ( ክፍል ሁለት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ በዚህ ምዕራፍ 2 ( ክፍል ሁለት ) ትምህርት እንግዲህ የምናየው ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ መሆንዋን ነው ታድያ አሁንም ይኸው የሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 5 በከመ ይቤ ሙሴ ወባዕዳንሂ ቅዱሳን ነቢያት ከመ ይእቲ እግዚአብሔራዊት ወደ አማርኛው ስተረጉመው ሙሴ ሌሎቹም ቅዱሳን ነቢያት ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ መሆንዋን እንደተናገሩ መጽሐፉ ይናገራል ታድያ ይህ ትምህርት ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ በመሆንዋ ለእስራኤል የተላለፈውን ትዕዛዝ ፣ ሦስቱ ወጣቶች እግዚአብሔርን በማምለክ ላይ የነበራቸውን እምነትና ያሳዩትን አቋም ትምህርቱ ይጠቁማል ፣ ከክርስቲያን የሚጠበቀው ነገር ምን እንደሆነ ያብራራል በእምነት መኖር የክርስቲያን ድርሻ መሆኑንም ይጠቁማል ከዚህም ሌላ በእምነት ስንኖር በጸጋ እንደምንድን ፣ እንደገናም በእምነት መኖር በትዕግስት መጠበቅን ያስተምራል ይለናል እንደገናም አስተዮሙ ማየ እምኮክሕ ዘውእቱ ክርስቶስ እንዲል ከድንጋይ አፍልቆ አጠጣቸው ይኸውም ክርስቶስ ነው በማለት ከብሉ ኪዳን ዘመን ጀምሮ ጌታ ውሃን ከድንጋይ አፍልቆ ለእሥራኤል እንዳጠጣቸው ወደ ሐዲስ ኪዳንም ስንመጣ ይከተላቸው ከነበረው ዓለት ጠጥተዋልና ያም ዓለት ክርስቶስ ነው ስለሚል ክርስቶስ ኢየሱስ ላመንበት ለእኛ ለዘላለም ሕይወት የሚመነጭ መንፈሳዊ ውሃን የሰጠን መሆኑን እንገነዘባለን ሃይማኖት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናት ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱን ይበልጥ በስፋት ለመከታተል ለምትፈልጉ ከዚህ እንደሚከተለው በቪዲዮ ለቅቄዋለሁ እና ተከታተሉ ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ትምህርት ሁላችንንም ይባርከን አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment