Tuesday 7 May 2019

የምንባቡ ኃይለ ቃል ፦ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ 1ኛ ሳሙኤል 7 በሙሉ ፣ ቁጥር 7የምንባቡ ኃይለ ቃል ፦ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ ( 1ኛ ሳሙኤል 7 በሙሉ ፣ ቁጥር 7 ) የተወደዳችሁ ወገኖች ከምንባቡ እንደምንመለከተው ሃያ ዓመት ሙሉ አዝነው እግዚአብሔርን የተከተሉ እስራኤላውያን በአሊምንና አስታሮትን አርቀዋል :: እግዚአብሔርንም ብቻ አምልከዋል :: :: ከዚህም ባሻገር ወደ ምጽጳም ተሰብስበው ፣ውሃ ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት በማፍሰስ እውነተኛና ትክክለኛ ንስሐ ገብተው በዚያን ቀን ጾመዋል:: ከዚህ የተነሳ ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በምጽጳ ፈርዶአል :: ይህ ሁሉ ከሆነ ታድያ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ፍልስጥኤማውያንን ስለምን ፈሩ ? ስለምንስ አሁንም የእስራኤል ልጆች ሳሙኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ትጸልይልን ዘንድ አትታክት ሊሉት ቻሉ ? ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው :: እስራኤልም ከፍልስጥኤማውያን ሊዋጉ በቀረቡ ጊዜ ጌታ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ታላቅ ነጐድጓድ አንጐዳጎደ አስደነገጣቸውም :: በእስራኤላውያንም ፊት ድል ተመቱ እያለ ምንባቡ ይቀጥላል ::ነገር ግን ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው :: ስሙንም እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል ሲል አቤንኤዜር ብሎ ጠራው ይለናል ::ይሁን እንጂ ታድያ ለእስራኤል ሳይታክት የጸለየው ሳሙኤል ሆኖ ሳለ ደግሞም የጸለየ ብቻ ሳይሆን በዚሁ በእግዚአብሔር ፊት የተሰማ ፣ ለውጤትም የበቃ እና እስራኤልንም ያበቃ እርሱ ሆኖ ሳለ እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዜር የማለቱ ጉዳይ አሁን ላይ በአገልግሎት ተሰይመን ጌታን በማገልገል ለምንገኘው ለእኛ የሚሰጠን ትርጉም ምን ምንድነው የሚሉትንና የመሣሠሉትን ጥያቄዎች ይሄ መልዕክት ይመልሳል ብዬ አምናለሁ ወደ መልዕክቱ በማለፍ የቪዲዮውን መልዕክት በማስተዋል ሆነን እንስማ ተባረኩልኝ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment