Friday 16 September 2016

ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት የይሁዳ መልዕክት 3 ፣ 20 _23 no.1 ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ( የይሁዳ መልዕክት 3 ፣ 20 _ 23 ) ምዕራፍ ፩ ( ክፍል አንድ ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ይህ ሚኒስትሪ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙትን ሃሳቦች ከመጻሕፍቶችዋ ውስጥ በማውጣት ሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ ወደ ቃሉ እውነት እንዲመጣ የሚረዳ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ይህ አገልግሎት አማኞችን በእግዚአብሔር ቃል ማስታጠቅና ደቀመዝሙር ማድረግን ከዚያም መልስ እውነተኛዋንና የፊት መጨማደድ የሌለባትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ በማዘጋጀት የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በዚሁ ሃሳብ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንደሚከተለው ይዤ ቀርቤያለሁና እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ከላይ በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረት ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት ብያለሁ ይህንንም ያልኩበት ምክንያት በይሁዳ መልዕክት ቊጥር 3 ላይ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ይለናል ስለዚህ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠ እንጂ አንድ ዓይነት ወይም የተስማሙ ሰዎች ያቀነባበሩትና ያዘጋጁት በተዋረድም ወደ እኛ የመጣ አይደለም ሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 5 ላይም በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ወከመ ትንስእዋ ለእንታክቲ እንተ ይቤ ከመ የኃብክሙ ኪያሃ ወደ አማርኛው ስተረጉመው እርስዋን ይሰጣችሁ ዘንድ የተናገራት ሃይማኖትን ገንዘብ ታድርጓት ዘንድ ይለናል በመሆኑም በዚህ ትምህርት ውስጥ ከእግዚአብሔር የተሰጠችዋ ሃይማኖት ምን እንደሆነች በቪዲዮ በተከታታይ በተለቀቀው ትምህርት በሰፊው ተብራርቶ ቀርቦልናል ስለዚህ ይህ በቪዲዮ የቀረበው ትምህርት እንዳያመልጣችሁ ተከታትላችሁም እንድትጠቀሙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment