ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and
Preaching Ministry ሥር
በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች እየተዘጋጀ የሚቀርብ ተከታታታይ ትምህርት ነው
Topic Teaching
የትምህርት ርዕስ
Different responses of those who understand
ከተረዱ ሰዎች የሚመጡ ልዩ ልዩ መልሶች
ክፍል ሰባት
እግዚአብሔር ሦስት ዓይነት ምላሽ የሚሰጡ ሰዎችን እንደቃሉ አስቀምጦልናል ከእነዚህ ማነው ትክክለኛ መረዳት ያለው ? ስንል እግዚአብሔር አዕምሮን ከፍቷል ትርጉሙን ይዘዋል ጨብጠውማል ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል
በማቴዎስ ወንጌል 13 ፥ 21 ላይ በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም በቃሉም ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል ይለናል
ይህ ሰው በመጀመርያ የተቀበለውን ደስታ መለሰ ነገር ግን በፍጥነት ወደኋላ አለ ለምን ወደኋላ አለ ? ስንል ከሌሎች ሰዎች የመከራ ጫና እና ክብደት የተነሳ ማለትም ካልተረዱ ሰዎች በሚነሳ መከራ ነው እርሱ የሚጨነቀው እግዚአብሔር ከሚያስበው በላይ ይበልጥ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ነው በጀልባ ውስጥ ያለውን ቋጥኝ ይፈራል በዙርያው ያሉ ሰዎች ለእርሱ ማረጋገጫዎችና ጠቃሚዎች ናቸው ረብሻና ማሳደድ ለእግዚአብሔር በመኖር ባለ ልምምድ እርሱን የሚያደናቅፉት ናቸው ከዚህ የተነሳም ከእግዚአብሔር የተጠራበትን መጠራት ሊቀበል ይቸገራል መቀበልም ያቅተዋል አይቀበልምም
በማቴዎስ ወንጌል 13 ፥ 22 ላይ ደግሞ በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው የዚህም ዓለም ሃሳብና የባለጠግነት ማታለል ቃሉን ያንቃል የማያፈራም ይሆናል ይለናል
በዚህ ሰው ሕይወት ውስጥ የምንመለከተው አንድ እውነት ይህ ሰው ቀረብ ብሎ ያየው የራሱ አስተያየት ወይም ግምት አያሳስበውም ነገር ግን እርሱ ሌላ ችግር አለው እርሱም ስስት ነው የራሱን ምቾት በብዙ ይጠብቃል የተሻለ ማዕረግም ለማግኘት ራሱን ይንከባከባል የራሱን ጊዜና ኃይል ፍላጐት ፍጆታው ያደርጋል ለእግዚአብሔር ጊዜ የለውም ራሱን በማገልገል በጣም ቢዚና ጊዜም የሌለው ነው ከመንፈሳዊ ነገሮች ይልቅ ቁሳዊ ነገሮች ለእርሱ ይበልጥ ጠቃሚ ናቸው የእግዚአብሔርን ጥሪ በፍጹም አይቀበልም
በማቴዎስ ወንጌል 13 ፥ 23 መሠረትም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል ይላል
ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል የተረዳ ነው እንደገናም ቃሉን በቁምነገር የወሰደ ነው ይህ ሰው ለደኅንነት የተመረጠ ነው እግዚአብሔርንም የሕይወቱ መጀመርያ ያደረገ ነው በፊልጵስዩስ 2 ፥ 13 መሠረት ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና ይለናል ብዙ ሰው ተጠርቷል ነገር ግን ጥቂቱ መልስ ይሰጣል ጥቂቶቹም በእውነት ንስሐ የሚገቡና ሕይወታቸውንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በማስገዛት ለእግዚአብሔር የትዕዛዛቱ ቃል ለመታዘዝ ቃል የገቡ ናቸው እነዚያም ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ የሚሰጡ በእግዚአብሔርም የተመረጡ ናቸው ለእርሱ ለመታዘዝና እርሱን ለማገልገል መመረጥ በእግዚአብሔር መመረጥ ነው እርሱንም
መጀመርያ ማድረግ ነው ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ይጥቀመን ከዚህ በመቀጠል የዘማሪ ፓስተር እንዳለ ወልደ ጊዮርጊስ ይፈውስ ይዳሰኝ እጅህ የሚለውን የቪዲዮ መዝሙር እጋብዛችኋለሁ
የትምህርቱ አዘጋጅ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ
ተባረኩልኝ
No comments:
Post a Comment