Friday 23 October 2015

M2U00032 የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry (የጆሽዋ ብሬክስሩ ) መሠረታዊ ዓላማ እና ግብ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ወደ ጆሽዋብሬክስሩ መንፈሳዊ አገልግሎት በሰላም መጣችሁ ይህ ሚኒስትሪ ዛሬ ላይ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ( ጆሽዋ ብሬክ ስሩ ሪኒዋል ቲቺንግ ኤንድ ፕሪቺንግ ሚኒስትሪ ) የሚለውን ስያሜ አግኝቶ በይፋ ይንቀሳቀስ እንጂ ከዛሬ ሃያ ሦስትና ሃያ አራት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እናት ቤተክርስቲያን ድንገተኛ በሚመስል ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ድንገተኛም ሆነ አጋጣሚ የሚባል ታሪክ የለምና በዘላለም እቅዱ ውስጥ በነበረው አጀንዳ መሠረት በበራውና በተቀጣጠለው የወንጌል ብርሃንና የደኅንነት ቃል የተጀመረ ነው እንቅስቃሴው የጀመረው በቃሉ ላይ ተጽፎ እንደምንመለከተው በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ይብራ ሲል ደግሞ ሊከለክለው የሚችል አንዳች ኃይል ስለሌለ እንደ ኢትዮጵያ የካላንደር አቆጣጠር በ1980ዎቹ ላይ በተለኮሰው ከሰማይ በሆነው የወንጌል ችቦ ይሄ አገልግሎት ተጀመረ በመሆኑም እኔና መሰሎቼን ለአገልግሎት የጠራን ታማኝ አድርጎም የቆጠረን ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ሲጠራን ለራሱ የአገልግሎት ክብር በራዕይና በተልዕኮ ነው የጠራን በሕይወታችንም የደኅንነቱ ብርሃን እንዲበራ ፈቀደና በደሙ ከኃጢአታችን በመታጠብ መንጻት ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎቱም ጭምር ታማኝና ብቁ ሠራተኞች እንድንሆንለት በመንፈሱ አጠመቀን ይህ አገልግሎት በ1980ዎቹ ላይ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ በመከሩ የወንጌል ሥራ ላይ ተሠማርቶ ብዙ ፍሬ አፍርቶአል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጌታ አምጥቷል በጌታም ቃል አስታጥቆ ለአገልግሎትም አብቅቶአል በተለይም የመነኮሳት ኅብረት በሚል ለሁለት ቀን የተካሄደው አገልግሎት ይህንን ራዕይ ውጤታማ ያደረገ ብዙ ያልዳኑ ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ አድርገው የተቀበሉት ሕሙማን የተፈወሱበት አገልግሎት በመሆኑ ለዚሁ ራዕይ ትልቅ ፍንጭ የሰጠ የአገልግሎትንም በሮች በብዙ ያስከፈተ እና ትልቅ ፈር ቀዳጅ የሆነ አገልግሎት ነበር ይህ ኅብረት እንዳይመሠረት ራሱንም ችሎ እንዳይቆም የእግዚአብሔርንም ተልእኮ እንዳያራምድ በብዙ ፈታኝ በሆኑ ማዕበሎች ውስጥ አልፎአል ዛሬም እንዲሁ እያለፈ ይገኛል ዝርዝር ሃሳቡን አንድ ሁለት ብለን ለመግለጽ ባያስፈልገንና ጊዜም የሚወስድብን ቢሆንም ነገር ግን ጌታ ብርታት ሆኖን አሁንም ባለንበት ሁኔታ ሁላችንም አለን ራዕዩ ከእኛ ባሻገር ዛሬም ላይ ብዙ መሪጌቶችንና ቀሳውስቶችን ወልዶ በተለያየ መልኩ የወንጌሉ እውነት በዚያው ቤት ውስጥ እየነደደ ይገኛል በገላትያ 4 ፥ 26 ላይ አንቺ የማትወልጂ መካን ደስ ይበልሽ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ እልል በዪ እና ጩኺ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአልና በ1990 በኤግዚቢሽን ማዕከል ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን አዎን ይወጣል አሮጊቷ ሣራ ወልዳለች የሚል የመልዕክት ቃል የተላለፈ በመሆኑ በዚሁ መሠረት አሮጊቷ ሣራም ከመካንነት ወጥታ ዛሬ ላይ ባለው ሕይወቷ የብዙ ልጆች እናትልትሆን በቅታለች ዛሬም በመብቃት ላይ ትገኛለች የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ ራዕይ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ ወንጌል እውነት እንድትመጣ ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ ቢሆንም ከዚያ መልስ ግን በጌታ አምነው የዳኑትን ቅዱሳን የእግዚአብሔር ቃል እውነትን በማስታጠቅ ደቀመዝሙር የሚያደርግና ለአገልግሎት ጭምር የሚያበቃ ነው ጥንታዊቷ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእምነት መግለጫዋ ላይ ተጽፎ በሚገኘው ጸሎተ ሃይማኖት ወይም የሃይማኖት ጸሎት ተብሎ በሚጠራው የእምነት መግለጫ ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን የሚል ቃል ተጽፎአል ጌታም የሚፈልጋት አንዲቱን ቤተክርስቲያንን ነው ታድያ በዚሁ መሠረት ክርስቶስ ኢየሱስ የፊት መጨማደድና ነውር የሌላትን ቤተክርስቲያን ለራሱ ሊያቀርብ የፈለገ በመሆኑ የበጉ ሠርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጎናጸፍ ተሰጥቶአታል ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ሥራ ነውና ይለናል ራዕይ 19 ፥ 7 እና 8 በመሆኑም አሠራር ልዩ ልዩ ቢሆንም የወንጌልን ሥራ ስንሠራ ግን በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ገብተን የምንሠራው ለአንዲት ቤተክርስቲያን ነውና ከዚህ በመቀጠል በነዚሁ ቃሎች መሠረት እኛም ይህቺኑ አንዱዋንና ነውር የሌላትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ እናዘጋጃለን ቅዱሳን ወገኖች ይህ አገልግሎት በሚኒስትሪ መልክ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ራዕዩ ትልቅ ስለሆነ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ አገልግሎት ነውና ይህንን ራዕይ ሊደግፉ የሚችሉትን አብያተክርስቲያናትንም ሆነ ቅዱሳንን ያሳትፋል እንጂ በሌሎች ሥር ሆኖ የሚንቀሳቀስ አገልግሎት አይደለም ስለዚህ ከዚህ ራዕይ ጋር አብራችሁ መቆም የምትፈልጉ ሁሉ ይህንኑ አውቃችሁ ከዚህ ራዕይ ጋራ በመተባበር እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እንወዳለን ነገር ግን ይህ ራዕይ በአግባብ ቀጥሎ ግቡን እንዲመታ ማበረታታትና መደገፍ ሲገባ ራዕዩ ከግብ እንዳይደርስ ለማኮላሸት መነሳት ትልቅ የሆነ ስሕተትና የሰይጣን ተቃውሞ ስለሆነ ይህን የሚያደርጉ ማናቸውንም ሰዎች ከዚህ ክፉ ተግባራቸው እንዲመለሱ በቅድሚያ ልንመክር እንወዳለን እንቢ አሻፈረኝ በዛው በተቃውሞዬ እቀጥላለሁ የሚሉ ከሆነ ደግሞ እንጸልይላቸዋለን ከጀርባቸው ሆኖ የሚሰራውንም ክፉ መንፈስ በጌታ በኢየሱስ ስም እንገስጻለን፣ እንቃወማለን በተረፈ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ተባረኩ የሁልጊዜ ጸሎታችሁ አይለየን ልንላችሁ እንወዳለን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ የተወደዳችሁ ወገኖች የዚህን ሚኒስትሪ ራዕይ በንባብ መልክ ያቀረብነው ብቻ ሳይሆን በጽሑፍም ጭምር ለእናንተ ለአድማጮች ያደረስነው በመሆኑ በሚገባ አንብባችሁ ከዚህ ራዕይ ጋር እንድትቆሙ በብዙ ልናበረታታችሁ እንወዳለን

No comments:

Post a Comment