Sunday 5 July 2015

017 የትምህርት ርዕስ እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ ዓላማ አለው God’s Purpose in Marriage የክፍል ሁለት ቀጣይ ትምህርት ቊጥር ፫ በጋብቻ ውስጥ 1ኛ )ሚስቶችን ለአንድ ነገር ልናደርጋቸው መሞከር የለብንም ይህንን ስናደርግ እንሳሳታለን የጋብቻችን ውጤትም ጥፋት ይሆናል _ አብርሃም በሣራ የተሳሳተበት ጊዜ ነበር _ ሦራም አብራምን ፦ እነሆ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርስዋ ግባ አለችው ዘፍጥረት 16 ፥ 2 _ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባርያዋን አጋርን ወስዳ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው ዘፍጥረት 16 ፥ 3 _ ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን እኔ ባሪያዬን በብብትህ ሰጠሁህ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው ዘፍጥረት 16 ፥ 5 _ ይህም ነገር በአብርሃም ዘንድ ስለ ልጁ እጅግ ችግር ሆነበት ዘፍጥረት 21 ፥ 11 2ኛ ) እንደ እግዚአብሔር ቃል ነገሮችን ማየት እና ማመዛዘን አለብን ( 1ኛ ጴጥሮስ 4 ፥ 11 ) 3ኛ ) ሚስቶቻችን የተፈጥሮ ችሎታቸው በፍላጎቶቻቸው ላይ እንዲሆን ማበረታታት አለብን 4ኛ ) ችሎታ ስላላቸው ደግሞ ያሹትን ሁሉ ለማግኘት እኛ ባሎች መግፋትና ማነሣሣት የለብንም 5ኛ ) የእግዚአብሔር ቃል ተከታዮች ስለሆንን ባል ቦታ አለው ሚስት ቦታ አላት 6ኛ ) ሚስቶችም ሆኑ ባሎች ትክክለኛ ቦታቸውን ሲይዙ የትውልድ ሁሉ ምሣሌ ይሆናሉ ትንቢተ ( ኢሳይያስ 51 ፥ 2 ) 7ኛ ) ትክክለኛ የሚስትነትን ቦታ ይዛ የምትንቀሳቀስ ሚስት ባልዋን አትንቅም ( ኤፌሶን 5 ፥ 33 ) 8ኛ ) ሚስት ለባልዋ ሚስት ሆና ስትመጣ ባለቤት አላት ስለዚህ ለባልዋ ትገዛ ሲል ቃሉ ራስዋን ለባልዋ ትስጥ ማለቱ ነው ኤፌሶን 5 ፥ 22 ፣ 24 ፤ ቆላስያስ 3 ፥ 18 9ኛ ) ሚስቶች በሚፈልጉትና በተገለጠላቸው ነገር ዝንባሌ እንዲያደርጉ እኛ ባሎች ማበረታታት አለብን መጽሐፈ መሣፍንት 5 ፥ 7 ፣ 12 ፣ 24 _ 29 10ኛ) ሚስቶች ከኃላፊነት ብዛትና ጫና ፣ ከሥራም ብዛት የተነሣ ሰውነታቸው ቢጎሳቆልና ቢጠቋቊሩ ራሳቸውን ለትዳራቸው ከመስጠት የተነሳም በቤት ውስጥ ባለ ተግባር ሳይቀር የቤታቸው ፣ የኑሮአቸውና የትዳራቸው ባርያ አድርገው ራሳቸውን በመቁጠር ለዚሁ ሕይወት መሳካት ጐንበስ ቀና እያሉ ቀንና ሌሊት ደፍ ደፍ ቢሉም ለእኛ ለባሎች ግን ዛሬም አስደናቂ ሚስቶች ፣ እናቶች ፣ ልዕልቶችና ንግሥቶች መሆናቸውን ልናውጅላቸው ፣ ልንናገራቸው በተግባርም ልንገልጽላቸው ይገባል ፍቅር ለዘወትር አይወድቅምና 1ኛቆሮንቶስ 13 ፥ 8 የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment