Friday, 22 May 2015

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? ክፍል ሦስት በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ?




ክፍል ሦስት


በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ


አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም
አቤቱ፥ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን  ትንቢተ ኤርምያስ 10 23 _ 24




በትሕትና የእግዚአብሔርን እርማት የምንፈልግበት ምክንያት የሰው መንገድ ከራሱ አይደለም እንደገናም አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም ስለሚለን ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለሁል ጊዜ በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት ለሕይወታችን እንፈልጋለን መጽሐፍቅዱሳችን በሮሜ 8 6 _ 9  ላይ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም ይለናል በሥጋ ስናስብ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ጠበኞች ነን ለእግዚአብሔርም ሕግ አንገዛም እንገዛ ብንልም እንኳ የሚሳነን ሆነን እንገኛለን እግዚአብሔርንም ማስደሰት አንችልም ለዚህ ነው ኤርምያስ በትንቢቱ አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም በማለት ሳያበቃ በሥጋ የተጓዘባቸው መንገዶች አካሄዱንም ለማቅናት የተራመደበት ጐዳናዎች  ቅጣትን እንዳመጡበት የተገነዘበ በመሆኑ አቤቱ፥ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን ሲል አምላኩን የተማጸነው ከዚህ የተነሳ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ዘንድ መኖሩ አስፈላጊነቱ ለዚህ ነው በመንፈስ እንጂ በሥጋ እንድንሆን አያደርገንም እንደገናም የእርሱ የእግዚአብሔር ወገን ለመሆናችን በውስጣችን ያለው የክርስቶስ መንፈስ ያረጋግጥልናል ሌላው በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት የምንፈልግበት ምክንያት እግዚአብሔር ፍጹማን ሊያደርገን ስለሚፈልግ ነው በማቴዎስ ወንጌል 5 48 ላይ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ ይለናል ስለዚህ አባታችን ፍጹም ወደ ሆነበት የፍጽምና ሕይወት ለመምጣት የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በትሕትና መፈለግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ለዚህ ነው በትንቢተ ኢሳይያስ 66 2 ላይ እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ያለን እንደገናም በዚሁ በትንቢተ ኢሳይያስ 66 5 ላይ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ  ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል ነገር ግን ያፍራሉ ይለናል ስለዚህ በመጥላትና በማሳደድ ሕይወት ውስጥ ሆነን እና  እግዚአብሔርም ሲከብር አይተን ከሚያፍሩት ወገኖች ከምንሆን ይልቅ በትሕትና እና በተሰበረ መንፈስ በቃሉ ወደምንንቀጠቀጥበት ሕይወት መጥተን እግዚአብሔር ቢመለከተን ለእኛ እጅግ የተሻለ ነው መዝሙረኛው ዳዊት በቃሉ ወደሚንቀጠቀጥበት ሕይወት ስለመጣ ራሱን እና ማንነቱን በሙሉ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ቃል አሳልፎ በመስጠት አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ  አለ መዝሙር 138 (139) 23 እና 24 ታድያ እኛም እንደ ዳዊት በዘላለም መንገዱ እንድንመራ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ቃል እራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥና ሕይወታችንንም ለእርሱ እንድናስመረምር በእጅጉ ያስፈልገናል እግዚአብሔር ለዚህ ይርዳን ከዚህ በመቀጠል ጥቂት ሃሳቦችን በእንግሊዝኛ ለተጨማሪ ማብራርያነት ይበልጥ እንዲረዳ መስጠት እፈልጋለሁና ተከታተሉ ጌታ ይባርካችሁ

Keep an open mind

Be willing to admit when you are wrong and change even if it means letting go of a long held belief or tradition. If u can successfully apply this one principle you will be for a head in the search for spiritual truth. Act 17 : 11, Isaiah 8 : 20.


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment