Sunday 24 May 2015

159 የትምህርት ርዕስ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ የሚለው መልዕክት የቤተክርስቲያን የሁልጊዜ መልዕክቷ ሊሆን ይገባል ዘጸአት 32 ፥ 25 እና 26 ፤ 1ኛ ሳሙኤል 8 ፥ 19 _ 22 በዚህ ትምህርት ውስጥ ለትምህርቱ ቁልፍ ሃሳቦች ሆነው በዋናነት የቀረቡ ነጥቦች አሉ እነርሱም 1ኛ)መደባለቅ 2ኛ)መዋጥና እንደ ረከሰ ዕቃ መሆን 3ኛ)የእስራኤል ከሞአብ ጋር ማመንዘር እና 4ኛ )ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ መጠመድ የሚሉት ሃሳቦች ናቸው ታድያ ዛሬም የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ የሚለው መልዕክት ለቤተክርስቲያን የሁልጊዜ መልዕክቷ ካልሆነ እነዚህ ከአንድ እስከ አራት በተራ ቁጥር የዘረዘርኳቸው ሃሳቦች በዛሬዋ የክርስቶስ ቤተክርስቲያንም ላይ የግድ መደገማቸው ፣ መሆናቸውና መፈጸማቸውም አይቀርም ደግሞም እየመጡ፣ እየሆኑና እየተፈጸሙም ናቸው ዛሬም ላይ ነገሮችን አስተውለን በእግዚአብሔር ቃልና በመንፈሱ ስንፈትሽ በቤተክርስቲያን መካከል መደባለቅ ፣ መዋጥና እንደረከሰ ዕቃ መሆን ፣ ማመንዘር ፣ ከማያምኑም ጋር በማይመች አካሄድ መጠመድ የሚሉት ነገሮች አሉ ይታያሉ ደግሞም ይስተዋላሉ መረንንነት ስድ መለቀቅ ከቊጥጥርም ውጪ መውጣት ሲሆን የእግዚአብሔር ቃል የሚገለጥበት ራዕይ ሲጠፋ መረንነት በቅዱሳኑ ሕይወት መካከል የአንዳንድ ጊዜ መሆኑ ቀርቶ የሁልጊዜ የሚሆንበት ጊዜ አለ ወንዶችም ደግሞ ከጋለሞቶች ጋር ይጫወታሉና፥ ከጋለሞቶችም ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ በገለሞቱ ጊዜ፥ ሙሽሮቻችሁም ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም የማያስተውልም ሕዝብ ይገለበጣል ይለናል ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 14 ስለዚህም የቤተክርስቲያን መልዕክት አሁንም የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደኔ ይምጣ የሚል ሊሆን ይገባል ከመረንነት እና ስድ ከመለቀቅ የተነሳ ከሌሎች ጋር በመቀላቀል የተነወረችና እየተነወረች ያለች ቤተክርስቲያን እንዳለች ሁሉ ባለመቀላቀል ምክንያት ሳትነውርና መልኳንም ሳትለውጥ ያለች እስካሁን ድረስም የምትኖር ቤተክርስቲያንም መኖርዋን ትምህርቱ ሳይጠቁም አላለፈም በመሆኑም የማትቀላቀል ቤተክርስቲያን ምን ዓይነት እንደሆነች ወደ አራት የሚደርሱ ነጥቦችን በመጠቆም ይህ ትምህርት ያልተቀላቀለችና ልትቀላቀልም የማትፈልግ ቤተክርስቲያንን በትክክል ያሳየናል ከዚህም ሌላ ከሌሎች ጋር ተቀላቅለን ወደ መዋጥና ወደ መርከስ ሕይወት የምንመጣው ለምኞቶቻችን ተላልፈን ከመሰጠታችን የተነሳ እንደሆነ ትምህርቱ አግባብነት ባለው ሁኔታ ይጠቁመናል ታድያ ለዚህ መፍትሔው ከሁሉ በፊት በቅድሚያ በጠራን ጌታ ተደግፈን መጠራታችንና መመረጣችንን ከማጽናት ይልቅ በየግል ፍላጎቶቻችን ተይዘን እንዲህ ቢሆንና እንድያ ቢደረግ ከሚለው መላ ምትና የየግል ከሆኑ የምኞቶች ግልቢያ ወጥተን ለሕይወታችን የእግዚአብሔርን ቃል ብንሰማ እና ብንማር ጌታ እግዚአብሔር በመጀመርያ ምኞቶቻችንን ከበረከቱ ያጠግባል ጐልማሳነታችንንም እንደ ንስር ያድሳል ለዓለምና ለዘላለም በእግዚአብሔር ምሕረት ከመታመን የተነሳም ክሳታችንና ድርቀታችን ተወግዶ በእግዚአብሔር ቤት እንደለመለመ ወይራ ዛፍ እንሆናለን የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ እንግዲህ ተከታታይነት ያለው ስለሆነ በጥቅሉ የሚቃኘው እነዚህን ሁኔታዎች ነው እኔ ግን እነዚህን ሃሳቦች ያሰፈርኩላችሁ ትምህርቱን በቀጣይነት ለመከታተል እንድትችሉ ሃይላይት ለመስጠት ያክል ነው ትምህርቱ በተከታታይነት ቀርቦላችኋል በፌስቡኩና በብሎጎቹ በጎግል አድራሻዬም ውስጥ እየገባችሁ ሳታቋርጡ እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ላሳስብ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment