Wednesday, 28 October 2015

Topic Teaching የትምህርት ርዕስ Different responses of those who understand ከተረዱ ሰዎች የሚመጡ ልዩ ልዩ መልሶች ክፍል ሰባት

ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር                                                                      በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች እየተዘጋጀ የሚቀርብ  ተከታታታይ ትምህርት ነው


Topic Teaching

የትምህርት ርዕስ

Different responses of those who understand

ከተረዱ ሰዎች የሚመጡ ልዩ ልዩ መልሶች


ክፍል ሰባት


እግዚአብሔር ሦስት ዓይነት ምላሽ የሚሰጡ ሰዎችን እንደቃሉ አስቀምጦልናል ከእነዚህ ማነው ትክክለኛ መረዳት ያለው ? ስንል እግዚአብሔር አዕምሮን ከፍቷል ትርጉሙን ይዘዋል ጨብጠውማል ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል

  በማቴዎስ ወንጌል 13 ፥ 21 ላይ በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም በቃሉም ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል ይለናል
       
    ይህ ሰው በመጀመርያ የተቀበለውን ደስታ መለሰ ነገር ግን በፍጥነት ወደኋላ አለ ለምን ወደኋላ አለ ?  ስንል ከሌሎች ሰዎች የመከራ ጫና እና ክብደት የተነሳ ማለትም ካልተረዱ ሰዎች በሚነሳ መከራ ነው እርሱ የሚጨነቀው እግዚአብሔር ከሚያስበው በላይ ይበልጥ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ነው በጀልባ ውስጥ ያለውን ቋጥኝ ይፈራል በዙርያው ያሉ ሰዎች ለእርሱ ማረጋገጫዎችና ጠቃሚዎች ናቸው ረብሻና ማሳደድ ለእግዚአብሔር በመኖር ባለ ልምምድ እርሱን የሚያደናቅፉት ናቸው ከዚህ የተነሳም ከእግዚአብሔር የተጠራበትን መጠራት ሊቀበል ይቸገራል መቀበልም ያቅተዋል አይቀበልምም

  በማቴዎስ ወንጌል 13 ፥ 22 ላይ ደግሞ በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው የዚህም ዓለም ሃሳብና የባለጠግነት ማታለል ቃሉን ያንቃል የማያፈራም ይሆናል ይለናል
   
    በዚህ ሰው ሕይወት ውስጥ የምንመለከተው አንድ እውነት ይህ ሰው ቀረብ ብሎ ያየው የራሱ አስተያየት ወይም ግምት አያሳስበውም ነገር ግን እርሱ ሌላ ችግር አለው እርሱም ስስት ነው የራሱን ምቾት በብዙ ይጠብቃል የተሻለ ማዕረግም ለማግኘት ራሱን ይንከባከባል የራሱን ጊዜና ኃይል ፍላጐት ፍጆታው ያደርጋል ለእግዚአብሔር ጊዜ የለውም ራሱን በማገልገል በጣም ቢዚና ጊዜም የሌለው ነው ከመንፈሳዊ ነገሮች ይልቅ ቁሳዊ ነገሮች ለእርሱ ይበልጥ ጠቃሚ ናቸው የእግዚአብሔርን ጥሪ በፍጹም አይቀበልም

 
  በማቴዎስ ወንጌል 13 ፥ 23 መሠረትም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል ይላል
     
   ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል የተረዳ ነው እንደገናም ቃሉን በቁምነገር የወሰደ ነው ይህ ሰው ለደኅንነት የተመረጠ ነው እግዚአብሔርንም የሕይወቱ መጀመርያ ያደረገ ነው በፊልጵስዩስ 2 ፥ 13 መሠረት ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና ይለናል ብዙ ሰው ተጠርቷል ነገር ግን ጥቂቱ መልስ ይሰጣል ጥቂቶቹም በእውነት ንስሐ የሚገቡና ሕይወታቸውንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በማስገዛት ለእግዚአብሔር የትዕዛዛቱ ቃል ለመታዘዝ ቃል የገቡ ናቸው እነዚያም ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ የሚሰጡ በእግዚአብሔርም የተመረጡ ናቸው ለእርሱ ለመታዘዝና እርሱን ለማገልገል መመረጥ በእግዚአብሔር መመረጥ ነው እርሱንም  መጀመርያ ማድረግ ነው ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ይጥቀመን ከዚህ በመቀጠል  የዘማሪ ፓስተር እንዳለ ወልደ ጊዮርጊስ ይፈውስ ይዳሰኝ እጅህ  የሚለውን የቪዲዮ መዝሙር እጋብዛችኋለሁ
  

የትምህርቱ አዘጋጅ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ


            ተባረኩልኝ

Tuesday, 27 October 2015

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Only those drown by God will understand እነዚህ...

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Only those drown by God will understand እነዚህ...: Only those drown by God will understand እነዚህ ብቻ በእግዚአብሔር የፈቃድ መረዳት የተሳሉ ናቸው ክፍል ስድስት ለእግዚአብሔር የመጠራትና የመመረጥ ...

Only those drown by God will understand እነዚህ ብቻ በእግዚአብሔር የፈቃድ መረዳት የተሳሉ ናቸው ክፍል ስድስት

Only those drown by God will understand



እነዚህ ብቻ በእግዚአብሔር የፈቃድ መረዳት የተሳሉ ናቸው


ክፍል ስድስት


ለእግዚአብሔር የመጠራትና የመመረጥ ሂደት ከእግዚአብሔር " በተአምር" መለየት የሚጀምር ነው መጽሐፉም  የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ ይለናል ዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 44  ከዚህም ሌላ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ፥ 65 ላይም ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለን ጌታ እግዚአብሔር አስደናቂ የሆነና ያልተለመደ የኃይል ምስክርነት አለው እርሱ ለእኛ ደርሶ እኛን ከሰይጣን እስራት ተጽዕኖ ፣ ከምንኖርበትም ከዓለም ክፋት ፈትቶናል ወደፊትም ገና ብዙዎችን ይፈታል እግዚአብሔር የሚጋብዘን ከእነዚህ ነገሮች ሊያወጣን ነው ልባችንንም የሚለውጠው ወደ ራሱ አቅጣጫ ነው እርሱ አጥብቆ የሚፈልገው ፣ ማረጋገጫ እና እውቅናም የሰጠን ፣ የሚሰጠንም መንገዱን እንድንማር ፣ ፈቃዳችንንም ለእርሱ እንድናስገዛ ነው ነገር ግን ዝንባሌያችን ለእግዚአብሔር ሕግ ሊገዛ አይፈቅድም ሕጉንም መቃወም ይጀምራል በሮሜ 8 ፥ 7 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና መገዛትም ተስኖታል ይለናል ለእግዚአብሔር ፈቃድ መሸነፍ መማረክ በእውነትም ተአምር ነው መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ስለበጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና ይለናል ፊልጵስዩስ 2 ፥ 13 ስለ አራቱ የመሬት ዓይነቶች ፣ ትርጉማቸው ፣ ለእግዚአብሔር ቃል ዘር ሰዎች ያላቸው ኃላፊነት ፣ የእግዚአብሔር ቃል እውነት በእነዚህ ነገሮች ውስጥ መሰበኩ ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የጠራቸው ብቻ እውነትን መረዳታቸውና መያዛቸው ፣ ለዚህ መልዕክት ሰዎች ልዩ ልዩ ምላሽ መስጠታቸው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ላይ በግልጽ ተጽፎ እናገኘዋለን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ቊጥር 19 ላይ ደግሞ የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ክፉ ይመጣል በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው ይለናል ታድያ እንደነዚህ ዓይነት ሕዝቦች የመልዕክቱን አስፈላጊነት አያስተውሉም  በመሆኑም ይህን መልዕክትና ትምህርት ያነበብን የደረሰንም ሰዎች ያነበብነው ቃል ተራ የሆኑና ሰዎችን ለማሳመንም ሆነ የራስ ለማድረግ ሲባል ተኰልኩለው የተጻፉ ልብ ወለድ የሰዎች የፈጠራ ድርሰቶች  ሳይሆኑ የእግዚአብሔር የመንግሥቱ ቃል ስለሆነ የመልዕክቱን አስፈላጊነት አስተውለን እኛም ለየራሳችን  አወንታዊ ምላሽ ልንሰጥበት ይገባል  ስል ወንድማዊ ምክሬን ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ዓይኖቻችንን ይክፈትልን አሜን
የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry  


አገልጋይና ባለራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Friday, 23 October 2015

M2U00032 የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry (የጆሽዋ ብሬክስሩ ) መሠረታዊ ዓላማ እና ግብ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ወደ ጆሽዋብሬክስሩ መንፈሳዊ አገልግሎት በሰላም መጣችሁ ይህ ሚኒስትሪ ዛሬ ላይ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ( ጆሽዋ ብሬክ ስሩ ሪኒዋል ቲቺንግ ኤንድ ፕሪቺንግ ሚኒስትሪ ) የሚለውን ስያሜ አግኝቶ በይፋ ይንቀሳቀስ እንጂ ከዛሬ ሃያ ሦስትና ሃያ አራት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እናት ቤተክርስቲያን ድንገተኛ በሚመስል ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ድንገተኛም ሆነ አጋጣሚ የሚባል ታሪክ የለምና በዘላለም እቅዱ ውስጥ በነበረው አጀንዳ መሠረት በበራውና በተቀጣጠለው የወንጌል ብርሃንና የደኅንነት ቃል የተጀመረ ነው እንቅስቃሴው የጀመረው በቃሉ ላይ ተጽፎ እንደምንመለከተው በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ይብራ ሲል ደግሞ ሊከለክለው የሚችል አንዳች ኃይል ስለሌለ እንደ ኢትዮጵያ የካላንደር አቆጣጠር በ1980ዎቹ ላይ በተለኮሰው ከሰማይ በሆነው የወንጌል ችቦ ይሄ አገልግሎት ተጀመረ በመሆኑም እኔና መሰሎቼን ለአገልግሎት የጠራን ታማኝ አድርጎም የቆጠረን ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ሲጠራን ለራሱ የአገልግሎት ክብር በራዕይና በተልዕኮ ነው የጠራን በሕይወታችንም የደኅንነቱ ብርሃን እንዲበራ ፈቀደና በደሙ ከኃጢአታችን በመታጠብ መንጻት ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎቱም ጭምር ታማኝና ብቁ ሠራተኞች እንድንሆንለት በመንፈሱ አጠመቀን ይህ አገልግሎት በ1980ዎቹ ላይ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ በመከሩ የወንጌል ሥራ ላይ ተሠማርቶ ብዙ ፍሬ አፍርቶአል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጌታ አምጥቷል በጌታም ቃል አስታጥቆ ለአገልግሎትም አብቅቶአል በተለይም የመነኮሳት ኅብረት በሚል ለሁለት ቀን የተካሄደው አገልግሎት ይህንን ራዕይ ውጤታማ ያደረገ ብዙ ያልዳኑ ሰዎች ጌታን የሕይወታቸው ጌታ አድርገው የተቀበሉት ሕሙማን የተፈወሱበት አገልግሎት በመሆኑ ለዚሁ ራዕይ ትልቅ ፍንጭ የሰጠ የአገልግሎትንም በሮች በብዙ ያስከፈተ እና ትልቅ ፈር ቀዳጅ የሆነ አገልግሎት ነበር ይህ ኅብረት እንዳይመሠረት ራሱንም ችሎ እንዳይቆም የእግዚአብሔርንም ተልእኮ እንዳያራምድ በብዙ ፈታኝ በሆኑ ማዕበሎች ውስጥ አልፎአል ዛሬም እንዲሁ እያለፈ ይገኛል ዝርዝር ሃሳቡን አንድ ሁለት ብለን ለመግለጽ ባያስፈልገንና ጊዜም የሚወስድብን ቢሆንም ነገር ግን ጌታ ብርታት ሆኖን አሁንም ባለንበት ሁኔታ ሁላችንም አለን ራዕዩ ከእኛ ባሻገር ዛሬም ላይ ብዙ መሪጌቶችንና ቀሳውስቶችን ወልዶ በተለያየ መልኩ የወንጌሉ እውነት በዚያው ቤት ውስጥ እየነደደ ይገኛል በገላትያ 4 ፥ 26 ላይ አንቺ የማትወልጂ መካን ደስ ይበልሽ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ እልል በዪ እና ጩኺ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአልና በ1990 በኤግዚቢሽን ማዕከል ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን አዎን ይወጣል አሮጊቷ ሣራ ወልዳለች የሚል የመልዕክት ቃል የተላለፈ በመሆኑ በዚሁ መሠረት አሮጊቷ ሣራም ከመካንነት ወጥታ ዛሬ ላይ ባለው ሕይወቷ የብዙ ልጆች እናትልትሆን በቅታለች ዛሬም በመብቃት ላይ ትገኛለች የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ ራዕይ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ ወንጌል እውነት እንድትመጣ ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ ቢሆንም ከዚያ መልስ ግን በጌታ አምነው የዳኑትን ቅዱሳን የእግዚአብሔር ቃል እውነትን በማስታጠቅ ደቀመዝሙር የሚያደርግና ለአገልግሎት ጭምር የሚያበቃ ነው ጥንታዊቷ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእምነት መግለጫዋ ላይ ተጽፎ በሚገኘው ጸሎተ ሃይማኖት ወይም የሃይማኖት ጸሎት ተብሎ በሚጠራው የእምነት መግለጫ ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን የሚል ቃል ተጽፎአል ጌታም የሚፈልጋት አንዲቱን ቤተክርስቲያንን ነው ታድያ በዚሁ መሠረት ክርስቶስ ኢየሱስ የፊት መጨማደድና ነውር የሌላትን ቤተክርስቲያን ለራሱ ሊያቀርብ የፈለገ በመሆኑ የበጉ ሠርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጎናጸፍ ተሰጥቶአታል ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ሥራ ነውና ይለናል ራዕይ 19 ፥ 7 እና 8 በመሆኑም አሠራር ልዩ ልዩ ቢሆንም የወንጌልን ሥራ ስንሠራ ግን በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ገብተን የምንሠራው ለአንዲት ቤተክርስቲያን ነውና ከዚህ በመቀጠል በነዚሁ ቃሎች መሠረት እኛም ይህቺኑ አንዱዋንና ነውር የሌላትን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ እናዘጋጃለን ቅዱሳን ወገኖች ይህ አገልግሎት በሚኒስትሪ መልክ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ራዕዩ ትልቅ ስለሆነ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ አገልግሎት ነውና ይህንን ራዕይ ሊደግፉ የሚችሉትን አብያተክርስቲያናትንም ሆነ ቅዱሳንን ያሳትፋል እንጂ በሌሎች ሥር ሆኖ የሚንቀሳቀስ አገልግሎት አይደለም ስለዚህ ከዚህ ራዕይ ጋር አብራችሁ መቆም የምትፈልጉ ሁሉ ይህንኑ አውቃችሁ ከዚህ ራዕይ ጋራ በመተባበር እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እንወዳለን ነገር ግን ይህ ራዕይ በአግባብ ቀጥሎ ግቡን እንዲመታ ማበረታታትና መደገፍ ሲገባ ራዕዩ ከግብ እንዳይደርስ ለማኮላሸት መነሳት ትልቅ የሆነ ስሕተትና የሰይጣን ተቃውሞ ስለሆነ ይህን የሚያደርጉ ማናቸውንም ሰዎች ከዚህ ክፉ ተግባራቸው እንዲመለሱ በቅድሚያ ልንመክር እንወዳለን እንቢ አሻፈረኝ በዛው በተቃውሞዬ እቀጥላለሁ የሚሉ ከሆነ ደግሞ እንጸልይላቸዋለን ከጀርባቸው ሆኖ የሚሰራውንም ክፉ መንፈስ በጌታ በኢየሱስ ስም እንገስጻለን፣ እንቃወማለን በተረፈ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ተባረኩ የሁልጊዜ ጸሎታችሁ አይለየን ልንላችሁ እንወዳለን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ የተወደዳችሁ ወገኖች የዚህን ሚኒስትሪ ራዕይ በንባብ መልክ ያቀረብነው ብቻ ሳይሆን በጽሑፍም ጭምር ለእናንተ ለአድማጮች ያደረስነው በመሆኑ በሚገባ አንብባችሁ ከዚህ ራዕይ ጋር እንድትቆሙ በብዙ ልናበረታታችሁ እንወዳለን

Monday, 19 October 2015

M2U00031 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የመልዕክት ርዕስ ብቸኛ የመዳኛ መንገድ የሆነውን የኢየሱስን መንገድ እንምረጥ የተወደዳችሁ አበው መምሕራን የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ እግዚአብሔር ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ የሰንበት ተማሪዎችና አስተማሪዎች እንዲሁም ሕዝበ እግዚአብሔር ምዕመናን በሙሉ የአምላካችን የእግዚአብሔር ቸርነቱና ምሕረቱ በዝቶልን እዚህ ላደረሰን ለእርሱ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምሥጋና ይግባው አሜን የዛሬው ትምህርታችን በመጽሐፈ ሰዓታት ላይ የተዘገበ ቃል ሲሆን ቃሉንም እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ ፍኖት ለኀበ አቡሁ አንቀጽ ዘመንገለ ወላዲሁ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚል ነው ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ፦ ወደ አባቱ የሚያደርስ መንገድ ወደ ወላጅ አባቱም የሚያስገባ በር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይለናል ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 122 ) ይህ የመጽሐፈ ሰዓታት መጽሐፍ ሁላችንም እንደምናውቀው የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት መምሕራንና ሊቃውንት በቤተክርስቲያኒቱ በሚታወቁት የአጽዋማት ጊዜያቶች ሌሊት እየተነሱ የሚጸልዩበት የሚያዜሙትና ምሥጋናም የሚያቀርቡበት የጸሎት መጽሐፍ ነው ይህንንም የሚያደርሱት አጽዋማቱን ተከትለው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በአብዝሆተ ፍቅር በንቅሐ ልቡና ስለሆነ ጸሎቱ ብቻ ሳይሆን ጣዕመ ዜማው ሳይቀር ልብን የሚመስጥ ፣ እጅግ አስደሳችና ማራኪም ነው ነገር ግን የዚህን የመጽሐፈ ሰዓታት የውስጥ ሃሳብ በማስተዋል ሆነን ስንመለከተው ከቅዱስ መጽሐፋችን መጽሐፍቅዱስ ጋር ሊጋጩ የማይችሉ ሃሳቦችን አግኝተንበታል ፦ አንደኛው ሃሳብ እንግዲህ በመግቢያ ትምህርታችን ላይ የጠቀስነው ዛሬ የምንመለከተው ሃሳብ ነው እርሱም እንዲህ የሚል ነው ፍኖት ለኀበ አቡሁ አንቀጽ ዘመንገለ ወላዲሁ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ወደ አባቱ የሚያደርስ መንገድ ወደ ወላጅ አባቱም የሚያስገባ በር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚል ትርጉም ይዟል የእናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንጋፋ መጽሐፍ ነው ተብሎ በሚታመነውና በሚጠራው የሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ላይ ከመጽሐፈ ሰዓታት ጋር በተዛማጅነት የሚሄድ ተመሣሣይ ቃል እናገኛለን ቃሉም እንዲህ የሚል ነው ፦ ጥንተ አንቀጽ መካነ ሕይወት ፈውስነ ሲሳይነ ስቴነ መኮንንነ ይላል ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ፦ በር አማጋ መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን የሚፈርድልን መጠጣችን የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል ( ሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 3 ይመልከቱ ) እነዚህን ሃሳቦች እንግዲህ እንደ ቃሉ ስንመለከታቸው ብዙ ሃሳቦች ያሉባቸው ቢሆኑም ለዛሬ ግን መጽሐፈ ሰዓታት የነገረንን ወደ አባቱ የሚያደርስ መንገድ ወደ ወላጅ አባቱም የሚያስገባ በር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚለውንና በሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 3 ላይ የተጠቀሰውን በር አማጋ መሠማርያ የሚሉትን ሃሳቦች ከመጽሐፍቅዱስ ጋር በማገናኘት ትክክለኛውን እውነት ለማወቅና ለመያዝ በዚያም ላይ ለመሄድ እንዲያስችለን እንመለከታቸዋለን መጽሐፍቅዱሳችንን አውጥተን ስናይ ደግሞ ከጠቀስናቸው የመጽሐፈ ሰዓታትና የሃይማኖተ አበው ቃሎች ጋር አንድ ዓይነት ሃሳቦች ይዘውና ተጽፈውልን ያሉ ቃሎች እናገኛለን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቊጥር 6 ላይ በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ፦ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ አነ ውእቱ ፍኖተ ጽድቅ ወሕይወት ወአልቦ ዘይመጽእ ኀበ አብ ዘእንበለ እንተ ኀቤየ ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ፦ ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ማለቱ ነው በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቊጥር 1 ላይ ደግሞ አሁንም በግዕዙ ቃል ፦ አማን አማን እብለክሙ ዘኢቦአ እንተ አንቀጽ ውስተ ዐፀደ አባግዕ ወአርገ እንተ ካልእ ገጽ ሰራቂ ወጒሕልያ ውእቱ ይለናል ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በሮች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው የሚል ትርጉም ይሰጠናል በሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 3 ላይ ጥንተ አንቀጽ መካነ ሕይወት በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በር አማጋ መሠማርያ እንደሆነ ጠቅሶልናል ይህንንም በመጽሐፍቅዱሳችን የቃሉ መስታወት ስንመለከተው በግዕዙ ቃል እንዲህ ሲል ተጽፎ እናገኘዋለን ፦ አነ ውእቱ አንቀጸ አባግዕ ዘበአማን ዘቦአ ብዕሲ እንተ ኀቤየ ይድኅን ወይበውእ ወይወጽእ ወይረክብ ምርዓየ ትርጉም ፦ እውነተኛ የበጎች በር እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል ይገባልም ይወጣልም መሠማርያም ያገኛል የሚል ነው የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቊጥር 9 እንግዲህ የመጽሐፈ ሰዓታት መጽሐፍም ሆነ የሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 3 ክፍል እንደገናም በመጽሐፍቅዱሳችን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቊጥር 6 እና አሁንም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቊጥር 1 ቊጥር 9 ላይ በተጻፉት ሃሳቦች መሠረት ኢየሱስ ወደ አባቱ የሚያደርስ መንገድ ወደ ወላጅ አባቱም የሚያስገባ በር ሆኖ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ካለ ከዚህም ሌላ እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው ካለን እንደገናም ኢየሱስ ወደ አባቱ የሚወስድ መንገድ ፣ እውነተኛ የበጎች በርና መግቢያ ፣ መውጫ ፣ መዳኛ ፣ መሠማርያ ከሆነ ስለምን ሌሎች መግቢያዎች ሌሎች መዳኛዎችና የመዳኛ መንገዶች እንዲሁም መሠማርያዎች አስፈለጉን ? ዛሬ ሕዝባችንን መውጫ ፣ መግቢያ ፣ መዳኛና የመዳኛ መንገድ ይህ ነው ስንል ያሠማራንበት ብዙ የሆኑ ወደ አብ መንግሥት ያስገቡሃል ስንል የከፈትንለት መንገዶች አሉ ኢየሱስ ግን አሁንም እኔ መንገድ እኔ እውነት እኔ ሕይወት እኔ የበጎች በር እኔ መውጫ እኔ መግቢያ እኔ መዳኛ እኔ መሠማርያ ያለ ብቻ ሳይሆን በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎናል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቁጥር 6 ስለዚህ ወደ አብ መንግሥት ለመምጣትና የመንግሥቱም ባለቤት ለመሆን በኢየሱስ በኩል መምጣት ሁላችንንም ግድ ይላል አለበለዚያ አብ አያውቀንም የመንግሥቱም ባለቤት ሊያደርገን አይችልም ኢየሱስም በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ያለ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ተብሎም የተነገረለት ጌታ በመሆኑ በእርሱ በኩል ካልመጣን አያውቀንም(ወደ ዕብራውያን የተጻፈ መልዕክት ምዕራፍ 7 ቊጥር 25 ) እንግዲህ ይህንን መልዕክትና ትምህርት የሰማን ያነበብንም የእግዚአብሔር ሕዝቦች አረጋውያን አባቶች እና እናቶች እህቶችና ወንድሞች ፣ ወጣቶች አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ መዘምራን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሙሉ ብዙ ብዙ ደክመን በፍጻሜው ዘመናችን እንዳናዝን ዛሬውኑ ወደ አብ መንግሥት ወስዶ የሚያድነንን ፣ የሚያገባንን ፣ የሚያወጣንን ፣ መሠማርያም የሚሰጠንን ብቸኛ መዳኛና የመዳኛም መንገድ የሆነውን የኢየሱስን መንገድ እንምረጥ ኢየሱስ መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎናል የሰማነውን በልቡናችን ያሳድርልን አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው አሜን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ