Monday, 31 December 2018
የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን ክፍል አንድ ትምህርት የትምህርት ርዕስ ፦ የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን ( ክፍል አንድ ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖችና የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ ተባረኩ እንደሰማችሁትና እንደተከታተላችሁት ጌታ አጃቢዎች እንድንሆን ሳይሆን ትክክለኛ የራሱ ደቀመዛሙርት እንድንሆን ስለፈለገ ይህንን መሠረታዊ ትምህርት በትምህርቱ የመነሻ ክፍለጊዜያችን ላይ ሰጥቶናል :: ዓለምን እንደኖህ በጽድቅ የምንኮንን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንድንሆን ራሳችንን ለጸጋው ባለቤት ለእግዚአብሔር በማስገዛት ጸጋውን ተቀብለን ወደዚህ ሕይወት ልንመጣ እንደምንችል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካኝነት በጽኑ ተናግሮናል :: ያገለገለንን የእግዚአብሔር ሰው መምህር ጌታቸው ምትኩን ጌታ እግዚአብሔር ይባርከው ለማለት እፈልጋለሁ ትምህርቱ እንግዲህ ሰኞ ሰኞ ሁልጊዜ በዚሁ ሰዓት ይቀጥላል :: ይህንንም ትምህርት ለሰዎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ :: ሰዎችን መጋበዝ አትርሱ :: ጌታ እግዚአብሔር የሳምንት ሰው ይበለን ቸር እንሰንብት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከተሃድሶ አገልግሎት
Friday, 28 December 2018
Thursday, 27 December 2018
የመልዕክት ርዕስ ፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!! ከዚህ በመቀጠል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ምክንያት በማድረግ አሁንም በድጋሜ መልዕክትን ወደ እናንተ ይዤ ቀርቤያለሁና ተከታተሉ የመልዕክት ርዕስ ፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና የዕለቱ የምንባብ ክፍል ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ( የማቴዎስ ወንጌል 2: 1 - 2 ) 1ኛ ) እነዚህ ሰዎች ሊሰግዱ መጥተው የቀሩ አልሆኑም ፣ ንጉሥ ሄሮድስም አላስቀራቸውም ፣ ኢየሱስ ጋር መጥተው ሰገዱለት ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት ( የማቴዎስ ወንጌል 2 : 11 ) 2ኛ ) ኢየሱስ ከተወለደ ጀምሮ ንጉሥ ነው ደግሞም የሚሰገድለት ነው :: ከሞት ተነስቶና ሞትን አሸንፎ ብቻ አይደለም የተሰገደለት በታንኳይቱም የነበሩት፦ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት ( የማቴዎስ ወንጌል 14 : 33 ) እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት ( የማቴዎስ ወንጌል 28 : 9 ) እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ( የሉቃስ ወንጌል 24 : 52 ) በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ ( ራዕይ 5 : 11 - 14 ) 3ኛ ) ኢየሱስን አንጠራጠረው ፣ ንጉሣችንና አዳኛችንም ነውና አንካደው ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ ( የማቴዎስ ወንጌል 28 : 17 ) ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት ( የማርቆስ ወንጌል 15 : 19 ) ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል 2ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 12 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
Thursday, 20 December 2018
በመምህር ጌታቸው የተዘጋጀ ትምህርት ነበረ በኮኔክሽን ምክንያት ቢቁዋረጥም ጌታ በመንፈሱ ያካፈለን መልዕክት ነበረ ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን መምህር ጌታቸው ምትኩ የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት ለመስጠት በሰዓቱ ተገኝቶ ነበር ነገር ግን በኮኔክሽን ችግር ምክንያት በዕለቱ ሊያስተላልፍልን ይዞት የመጣውን ትምህርት ማስተላለፍ አልቻለም በሚቀጥለው ጊዜ ጌታ ረድቶን በሚኖረን ፕሮግራም ያለምንም ችግር ለተከታታይ ሳምንታት ሳይቋረጥ እናስተላልፋለን ብለን እናምናለን ወንድማችን እንደምታውቁት ለማስተማር ከኢትዮጵያ ነውና የሚገባው የሃገራችንን የኔት ወርክ ሁኔታ ደግሞ ታውቁታላችሁና በጣም አስቸጋሪ ነው ለወደፊቱም ያለምንም ችግር የተዘጋጁበትን ትምርቶች እንደሚገባ እንዲያስተላልፉ ከኢትዮጵያ ለሚገቡ አገልጋዮችም ሆነ እዚሁ ላለነው ለእኛም ጭምር አብዝታችሁ ጸልዩልን ለማለት እወዳለሁ ይሁን እንጂ ጌታ መልዕክት ስለነበረው በሚደንቅ ሁኔታ ቃሉን በመንፈስቅዱስ አማካኝነት አስተላልፎልናል መልዕክቱ የሚጠቅማችሁ ስለሆነ ደጋግማች በማስተዋል ስሙት ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ
Wednesday, 19 December 2018
Ethiopia:{ እጅግ አሳዛኝ መረጃ } አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ተደበደቡ! ግን ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እስኪገሎቸው ነው...ይህቺ ናት ርትዕቷና ቀጥተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ተብላ የሚፎከርላት እንግዲህ :: መጨረሻዋ ይሄ ሆነ :: ጉድ አይሰማም አይባልምና አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት የማይከበሩባት ፣ ጉሮሮአቸው ታንቆ የሚደበደቡባት ፣ መንፈሳዊ መሪዎች የማይከበሩባት እና የማይደመጡባት ፣ ሊያውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አረጋዊ አባትና የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የተደበደቡባት ቤት ሆነች :: ወገኖቼ የእስራኤል መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ፣ አናቂ ቁጥር 1 ሽፍቶች መነኮሳትን እስር ቤት ባይወስድ ፣ በቤተመቅደሱ ውስጥም የነበረውን ድብድብ ባያስቆም ፣ ጉሮሮአቸው የታነቀው ምስኪኑ አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ለሕልፈተ ሕይወት በተዳረጉ ነበር :: ወገኖቼ እስቲ አንድ ጊዜ ይህንን ሁኔታ ቆም ብላችሁ አስቡት የራስ ሀገር ባልሆነ በኢየሩሳሌም ከአንድ ትልቅ ገዳምና የኃይማኖት ተቋም ይሄ ድርጊት ሊፈጸም ይገባልን ? የሦስት ሺህ ዓመት ክርስትና አለኝ የምትለዋ ይህቺ ቤተክርስቲያንስ በዚህ አሳፋሪ ጉዳይ ስሟ በዓለም ዙርያ ሊናኝና ሊነሳስ ይገባ ነበር ? ታድያ ለዚህ እኮ ነው እኛም አፋችንን ሞልተን አሁን ላይ ላለችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ ያስፈልጋታል የምንለው :: በሆሴዕ 4 ፥ 6 - 8 በተጻፈው ቃል መሠረት ከምዕመኖችዋ በፊት ያሉት ካህናትዎችዋ በደሙ የተገኘውን የኃጢአት ሥርየት ለማግኘት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በነፍስ ወከፍ የግል አዳኛቸው አድርገው ዛሬ ነገ ሳይሉ እና ሳይሞቱ በምድር ላይ አሁኑኑ ድህነትን ተቀብለው ቢገኙ ፣ የዳነ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላኩም መንፈስ የታጠበ ፣ የተቀደሰና የጸደቀ ስለሆነ ዓመጸኛ ተሳዳቢ ሴሰኛ ነጣቂ ተደባዳቢ ገዳይና የመሣሠሉትን አይሆኑም በ2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 9 - 11 የተጻፈውን ቃል በማስተዋል እናንብበው :: ቀራጩ ዘኬዎስ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ በቀረጥ ሰብሳቢነቱ አሁን ከዘረዘርኳቸው ተርታዎች የተመደበ ሰው ነበር :: ነገር ግን ኢየሱስን ይዞ ወደ ቤቱ በመግባት ዘኬዎስ ግን ቆሞ ይለናል ቃሉ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆነ አራት እጥፍ እመልሳለሁ ሲል ልባዊ ኑዛዜውን እንዳቀረበና ኢየሱስም አሁን ለቤቱ መዳን እንደሆነለት አውጆ የአብርሃም ልጅ ነህ እንዳለው እንመለከታለን የሉቃስ ወንጌል 19 ፥ 1 - 10 :: ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል እንደሚል ቃሉ ሮሜ 4 ፥ 5 የሚያስደንቀው እውነት ኢየሱስ ስለበደላችን የሞተ እኛንም ስለማጽደቅ የተነሣ ነውና በእርሱ በማመናችን ምክንያት ብቻ እምነታችንን ጽድቅ አድርጎ ይቆጥረዋል ሮሜ 4 ፥ 22 - 25 :: ለዚህም ነው ዘኬዎስን እውነተኛ ንስሐ በመግባቱ ብቻ ተቀብሎ መዳንን የሰጠው :: ወገኖቼ ሆይ ጽድቃችን ወይም ሥራችንማ ይኸው አረጋዊ ጳጳስ ሳይቀር እስከ መደብደብ ደርሶ በእግዚአብሔር ፊት አላቆመንም :: ይኸው ታየ ኦኮ በቃ ! ስለዚህ ትምክህታችን ጽድቃችን ቅድስናችንና ቤዛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 30 እና 31 ን እንመልከት :: መልዕክቴን ስጠቀልለው አሁን ላይ ያለሽው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሚበጅሽ አንድና አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ነውና ወደ እግዚአብሔር ቃል ፊትሽን መልሺ ስል በወንድማዊና አባታዊ ምክሬን ልሰጥሽም ሆነ ላስገነዝብሽ እወዳለሁ:: በኢሳይያስ መጽሐፍ እንደተጻፈው በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ በማለት ይናገራል ትንቢተ ኢሳይያስ 2 ፥ 2 - 5 ይመልከቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት ከወንድሞቼ ጋር በመነጋገር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መሪነትን አገልግሎትንና ክህነትን ሌሎችንም ጉዳዮች መሠረት ያደረገ ሰፋ ያለ ትምህርት ይዘን በቪዲዮ ልንቀርብ እንችላለን :: እስከዚያው ግን ይህቺን መልዕክት በማንበብ እንድትጠቀሙ ለእናንተ ለወገኖቼ ትቻለሁ :: ሌላው መናገር የምፈልገው ወንድምህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ ነውና ይሄ ውሽንፍር ወደ ወንጌላውያኑም ቤተክርስቲያን ከሞላ ጎደል ጎራ ያለ በመሆኑ ይፋ ሆኖ ባይገለጥም በአንዳንድ ደካማና ያልበሰሉ ፓስተሮችም ሆነ ነቢያት እየታየ ያለ ክስተት ሆኗል ስለዚህ በአጠቃላይ የክርስቶስ ስም በእኛ ምክንያት እንዳይሰደብ ሁላችንም ልናስብበት ይገባል የሚለውን ምክር ልሰጥ እፈልጋለሁ :: ጌታ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት
Ethiopia:{ እጅግ አሳዛኝ መረጃ } አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ተደበደቡ! ግን ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እስኪገሎቸው ነው...