Monday, 29 October 2018
በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 2 ) እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ? I - እግዚአብሔር ፍቅሩን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶ ተቀበለን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር 1ኛ ) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ( የዮሐንስ ወንጌል 3 : 16 ) 2ኛ ) ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ( ሮሜ 5 ፥ 8 ) 3ኛ ) ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፥ በጸጋ ድናችኋልና ፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 : 4 - 7 ) 4ኛ ) በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል ( 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 9 - 11 ) II - ሰዎች ሊለማመዱት ፣ ሊገልጹትና ሊያሳዩት ያልቻሉት የእግዚአብሔር ፍቅር የማቴዎስ ወንጌል 18 ፥ 23 _ 35 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት
ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ትርጉም ፦ አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን ( ምንጭ ከቅዳሴ እግዚእ የተወሰደ)ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ትርጉም ፦ አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን ( ምንጭ ከቅዳሴ እግዚእ የተወሰደ) የቀደመችዋ ኦርቶዶክስ የያዘቻቸውን መጽሐፍቅዱሳዊ እውነቶች ለማሳየት ቅዳሴ ለኢየሱስ በሚል አርዕስት ከወንድማችን አባ ተክለማርያም ጋር በየሳምንቱ ቅዳሜ ባለን ፕሮግራም ጀምረን ቅዳሴ ሐዋርያትን በማጠናቀቅ ቅዳሴ እግዚእ ላይ ደርሰናል በዛሬው ዕለት የለቀቅነው ቪዲዮ ደግሞ በጣም አስደናቂና በውስጡም ትልቅ መልዕክት ያለው በመሆኑ ሰምታችሁ እንድትባረኩበት እነሆ ብለናል ትምህርቱ በየሳምንቱ ሳይቋረጥ ይቀጥላል ተባረኩ ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ ወአዕዛንነሂ ቃለ ዘባሕቲትከ ይስምዓ አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን ዘወትር አንተን ያዩ ዘንድ ጆሮዎቻችንም ያንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ ( ምንጭ ከቅዳሴ እግዚእ የተወሰደ) በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው የሉቃስ ወንጌል 24: 45 ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1 : 18 - 19 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት
Zemary hawaz newest song MECHE NEW መቼ ነው መቼ ነው ያለቅድመ ሁኔታ መቼ ነው በእምነት የምሰብክህ ጌታ መቼ ነው የዙርያዬን ረስቼው መቼ ነው ስለ እውነት የማደላው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኔን እግዚአብሔር ይባርከው ወገኞቼስ ለእኛስ መቼ ነው ያለቅድመ ሁኔታ ጌታን የምንሰብከው ዘመኑ እኮ አጭር ነው የትኩረት አድማሶቻችንን ከሳበው ከንቱና ተራ ከሆነው ነገር ወጥተን እባካችሁ ይህንን ጌታን እንስበከው ኢየሱስ ያድናል እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ? I - እግዚአብሔር ፍቅሩን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶ ተቀበለን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር  1ኛ ) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ( የዮሐንስ ወንጌል 3 : 16 ) 2ኛ ) ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ( ሮሜ 5 ፥ 8 ) 3ኛ ) ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፥ በጸጋ ድናችኋልና ፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 : 4 - 7 ) 4ኛ ) በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል ( 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 9 - 11 ) II - ሰዎች ሊለማመዱት ፣ ሊገልጹትና ሊያሳዩት ያልቻሉት የእግዚአብሔር ፍቅር የማቴዎስ ወንጌል 18 ፥ 23 _ 35   አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት
እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ?
I - እግዚአብሔር ፍቅሩን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶ ተቀበለን
በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር
1ኛ ) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና
( የዮሐንስ ወንጌል 3 : 16 )
2ኛ ) ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል
( ሮሜ 5 ፥ 8 )
3ኛ ) ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፥ በጸጋ ድናችኋልና ፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 : 4 - 7 )
4ኛ ) በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል
( 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 9 - 11 )
II - ሰዎች ሊለማመዱት ፣ ሊገልጹትና ሊያሳዩት ያልቻሉት የእግዚአብሔር ፍቅር
የማቴዎስ ወንጌል 18 ፥ 23 _ 35
አባ ዮናስ ጌታነህ
ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት
Saturday, 27 October 2018
አጠር ያለ የግጥም መነባንብ :- የተክለ ሃይማኖት ወዮታ የተክለ ሃይማኖት ወዮታ የገድሉን ሐሰተኝነት በሚያጋልጥ መልኩ ከተክለሐይማኖት ገድል ተውጣጥቶ እና በወንጌሉ እውነት ተቃኝቶ የቀረበ የግጥም መነባንብ መልካም የንባብ ጊዜ ይሁንልዎት!!! ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ ለሰዎች ብርሃን ያበራሁኝ መስሎኝ በጨለማ ኖሬ ለራሴ ጨለምኩኝ ከንቱ ግብዝነት ይዞኝ ስንቀባረር ክህነቴን በሰማይ አድርጌው ለመኖር ክንፎችን ገጥሜ በግራና በቀኝ የሰማይ ካህን ነው ራሴን አስባልኩኝ ነገር ግን ክንፎቹ የውሸት ነበሩ ለይምሰል ተስለው ተሰክተው የቀሩ እንደ ዶሮ ላባ ድንገት ሲነቀሉ በወንጌሉ እውነት ዳግም ላያበቅሉ እኔም ተሳቅቄ ወዮልኝም አልኩኝ ሥራዬን ገልጠውት ከሹመት ሲሽሩኝ የሰዎችን ኃጢአት ይቅርም ለማስባል የሚንበረከክ ነው ሲጸልይ የሚውል ማንም ያልሰራውን ሰርተኸዋል ሲሉኝ ተብዬ ስወደስ ሰዎች ሲያሞካሹኝ በጌቴሴማኒ የተንበረከከው ሥርየት ለማሰጠት ደሙን ያፈሰሰው ደም ሳይፈስ ሥርየት ፍጹም አይገኝም በመንበርከክ ጸሎት ማንም አያመጣም ብሎ ተናገረኝ ውሸታም ነህ ብሎ ሥራዬን አጋልጦ ተንኮሌን ፈንቅሎ ላሞች ባልዋሉበት የኩበት ለቀማ ራሴን ሰቅዬ በጸሎቱ ማማ እግሬ የተቆረጠው ስጸልይ ነው አልኩኝ በገድል በድርሣኑ ራሴን ከመርኩኝ እውነቱ ሲነገር ታሪክ ሌላ ሆነ እኔም ተጋለጥኩኝ ስሜም ተኮነነ መንግሥትን ከላስታ ወደ ሸዋ ምድር ለማዞር ፈልጌ ስዶልት ስመክር ገድለህ ንገሥ ብዬ ንጉሡን ሳሳብር የዶሮውን ጩኸት ትርጉሙን አውቃለሁ እያልኩ ስቀሰቅስ ሳዳምቅ እያለሁ ድንገት በጦርነት እግሬ ተሰበረ የጸሎት ሰው ሲሉኝ ስሜም የከበረ ዛሬስ ተዋረድኩኝ ገበናዬም ወጣ ብዬ አለቀስኩኝ ባመጣሁት ጣጣ የመጨረሻዬ የተቅማጥ በሽታ የመጨረሻዬ የወባ በሽታ ከዚህ ምድር ይዞኝ ሊወስደኝ በአንድ አፍታ እስቲ ስሜን ላድስ በፍጻሜው ሰዓት በዚህ በተቅማጡ ከመሞቴ በፊት ብዬ አሰብኩና ኪዳኑን በሰማይ ከኢየሱስ ደም ጋራ ላያይዘው በላይ መዋሸት ጀመርኩኝ ዳግመኛ ሳላፍር እንደ ስቅለቱ ደም ተቅማጤን ላስቆጥር በገዳም የሞተ በወባ በሽታ ይድናል አይጠፋም ይኖራል በደስታ በመላዕክት ዓለም በሆታ በእልልታ በመንግሥተ ሰማይ በላይኛው ጌታ ነገር ግን አንዳንዱ አቃሎት ነገሬን ከሰማኝ በኋላ የባልቴት ተረቴን በያደባባዩ ደግሞ ሊያሳፍረኝ መደበቅያ ሥፍራ ቦታም አሳጥቶኝ በወንጌሉ እውነት በርብሮ ገለጠኝ የመቀበርያዬም ጊዜያቱ ደረሰ ሳልፈልገው በግድ ጉድጓዴ ተማሰ እኔም ከዚህ ወዲያ ይበቃኛል አልኩኝ ዳግም ላልተነፍስ መቃብር ወረድኩኝ እፎይ ያለው ትውልድ ይኸው ተቀስቅሶአል የወንጌል ደመራው ችቦው ተለኩሶአል ጆሮ ያለው ይስማ ኢየሱስ ያድናል ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ለግጥሞቹ የተጠቀምኩበት መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው ያንብቡአቸው ዕብራውያን 12 ፥ 24 , ቅዳሴ ሐዋርያት ገጽ 122 ፥ 106 , የተክለ ሐይማኖት ስብሐተ ፍቁር ገጽ 214 , የተክለ ሐይማኖት ስብሐተ ፍቁር ገጽ 2116 , ዕብራውያን 10 ፥ 29 - 31 , በ13ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በላስታ ያለውን የዛጉዬን መንግሥት ወደ ሸዋ ለመመለስ ባካሄደው መፈንቅለ መንግሥት , ገድለተክለሐይማኖት ምዕራፍ 27 ፥ 15 ፣ 17 , 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 7 ፣ ኤፌሶን 1 ፥ 7 , ኅዳር 24 ፥ ገጽ 78 , ዕብራውያን 9 ፥ 22 ፣ ኤፌሶን 1 ፥ 7 ፣ ሮሜ 5 ፥ 6 _ 10 , ገድለ ተክለሐይማኖት ምዕራፍ 57 , ገድለ ተክለሐይማኖት ትንሣኤ የመጻሕፍት አሳታሚ ድርጅት ሦስተኛ እትም 1973 የታተመ ምዕራፍ 56 ቊጥር 1 - 3 ገጽ 175 ,
Thursday, 25 October 2018
በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 1 ) እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ? ስለ ወደደን ተቀበለን :: ሀ ) መወደድ ( ትንቢተ ሚልክያስ 1 ፥ 2 ፤ ትንቢተ ዘካርያስ 10 ፥ 6 ) የዛሬው ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ የሚናገረው ስለ መወደድ ነው በማስተዋል ተከታተሉ :: መወደዱ የገባው ሰው ደግሞ በቅዱስ አጠራሩ ጠርቶ ያዳነውን ጌታ ይጠራል እንጂ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1 : 9 እንደገና ወደኋላ ተመልሶና የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ መውደድ ረስቶ ወይንም በእግዚአብሔር እንዳልተወደደ አድርጎ ራሱን በመቊጠር ነይ ነይ እምዬ ማርያም ፣ ናና ሚካኤል ፣ ናና ገብርኤል ፣ ናና ኡራኤል እና የመሣሠሉትን እያለ ሲጣራ አይገኝም :: ነይ ነይ እምዬ ማርያም ፣ ናና ሚካኤል እና ሌሎችንም ቅዱሳን መላዕክትንም ሆነ ቅዱሳንን ሰዎች አለመጥራት እነርሱን መጥላትና እነርሱንም አለመፈለግ እንዳልሆነ ሕዝባችን ሊረዳ ይገባዋል :: እኛ አምላክ ያለን እና አምላካችንም ልጆቹ አድርጎ የተቀበለን ሕዝቦቹ ስለሆንን ( 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 16 _ 18 ) ማርያምን ቅዱሳን ሰዎችንና ቅዱሳን መላዕክትን ሁሉ ስማቸውን አድሬስ በማድረግ እየተጣራን ወደ ማርያም ወደ ፍጡራን ሰዎችና ወደ መላዕክቱም ጭምር እንድንጸልይ መጽሐፍቅዱስ አያስተምረንም ተባረኩ :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት
Sunday, 21 October 2018
Friday, 19 October 2018
Monday, 15 October 2018
የክፍል 3 መልዕክት ፦ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው ( መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7...የክፍል 3 መልዕክት ፦ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው ( መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7 : 19 ) የሚናዘዙና ንስሐ የሚገቡ ሰዎች ፦ ሀ ) ለእግዚአብሔር ክብር የሚሰጡ ናቸው ለ ) የሚቀኑ ሰዎች ናቸው ( ራዕይ 3 ፥ 19 ) የማይናዘዙ ሰዎች ፦ ሀ ) የሌላውን ሰው ሕይወት ብቻ ሳይሆን የራሳቸውንም ሕይወት ጉዳት ላይ የሚጥሉ ናቸው
Sunday, 14 October 2018
የተክለ ሃይማኖት ወዮታ
የገድሉን ሐሰተኝነት በሚያጋልጥ መልኩ ከተክለሐይማኖት ገድል ተውጣጥቶ እና በወንጌሉ እውነት ተቃኝቶ የቀረበ የግጥም መነባንብ
መልካም የንባብ ጊዜ ይሁንልዎት!!!
ወዮልኝ
ወዮታ አለብኝ
ለሰዎች ብርሃን ያበራሁኝ መስሎኝ
በጨለማ ኖሬ ለራሴ ጨለምኩኝ
ከንቱ ግብዝነት ይዞኝ ስንቀባረር
ክህነቴን በሰማይ አድርጌው ለመኖር
ክንፎችን ገጥሜ በግራና በቀኝ
የሰማይ ካህን ነው ራሴን አስባልኩኝ
ነገር ግን ክንፎቹ የውሸት ነበሩ
ለይምሰል ተስለው ተሰክተው የቀሩ
እንደ ዶሮ ላባ ድንገት ሲነቀሉ
በወንጌሉ እውነት ዳግም ላያበቅሉ
እኔም ተሳቅቄ ወዮልኝም አልኩኝ
ሥራዬን ገልጠውት ከሹመት ሲሽሩኝ
የሰዎችን ኃጢአት ይቅርም ለማስባል
የሚንበረከክ ነው ሲጸልይ የሚውል
ማንም ያልሰራውን ሰርተኸዋል ሲሉኝ
ተብዬ ስወደስ ሰዎች ሲያሞካሹኝ
በጌቴሴማኒ የተንበረከከው
ሥርየት ለማሰጠት ደሙን ያፈሰሰው
ደም ሳይፈስ ሥርየት ፍጹም አይገኝም
በመንበርከክ ጸሎት ማንም አያመጣም
ብሎ ተናገረኝ ውሸታም ነህ ብሎ
ሥራዬን አጋልጦ ተንኮሌን ፈንቅሎ
ላሞች ባልዋሉበት የኩበት ለቀማ
ራሴን ሰቅዬ በጸሎቱ ማማ
እግሬ የተቆረጠው ስጸልይ ነው አልኩኝ
በገድል በድርሣኑ ራሴን ከመርኩኝ
እውነቱ ሲነገር ታሪክ ሌላ ሆነ
እኔም ተጋለጥኩኝ ስሜም ተኮነነ
መንግሥትን ከላስታ ወደ ሸዋ ምድር
ለማዞር ፈልጌ ስዶልት ስመክር
ገድለህ ንገሥ ብዬ ንጉሡን ሳሳብር
የዶሮውን ጩኸት ትርጉሙን አውቃለሁ
እያልኩ ስቀሰቅስ ሳዳምቅ እያለሁ
ድንገት በጦርነት እግሬ ተሰበረ
የጸሎት ሰው ሲሉኝ ስሜም የከበረ
ዛሬስ ተዋረድኩኝ ገበናዬም ወጣ
ብዬ አለቀስኩኝ ባመጣሁት ጣጣ
የመጨረሻዬ የተቅማጥ በሽታ
የመጨረሻዬ የወባ በሽታ
ከዚህ ምድር ይዞኝ ሊወስደኝ በአንድ አፍታ
እስቲ ስሜን ላድስ በፍጻሜው ሰዓት
በዚህ በተቅማጡ ከመሞቴ በፊት
ብዬ አሰብኩና ኪዳኑን በሰማይ
ከኢየሱስ ደም ጋራ ላያይዘው በላይ
መዋሸት ጀመርኩኝ ዳግመኛ ሳላፍር
እንደ ስቅለቱ ደም ተቅማጤን ላስቆጥር
በገዳም የሞተ በወባ በሽታ
ይድናል አይጠፋም ይኖራል በደስታ
በመላዕክት ዓለም በሆታ በደስታ
በመንግሥተ ሰማይ በላይኛው ጌታ
ነገር ግን አንዳንዱ አቃሎት ነገሬን
ከሰማኝ በኋላ የባልቴት ተረቴን
በያደባባዩ ደግሞ ሊያሳፍረኝ
መደበቅያ ሥፍራ ቦታም አሳጥቶኝ
በወንጌሉ እውነት በርብሮ ገለጠኝ
የመቀበርያዬም ጊዜያቱ ደረሰ
ሳልፈልገው በግድ ጉድጓዴ ተማሰ
እኔም ከዚህ ወዲያ ይበቃኛል አልኩኝ
ዳግም ላልተነፍስ መቃብር ወረድኩኝ
እፎይ ያለው ትውልድ ይኸው ተቀስቅሶአል
የወንጌል ደመራው ችቦው ተለኩሶአል
ጆሮ ያለው ይስማ ኢየሱስ ያድናል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል
ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት