Thursday, 26 March 2015
Tuesday, 24 March 2015
Sunday, 22 March 2015
Wednesday, 18 March 2015
Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን ሃይማኖተ አበው ...
Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን ሃይማኖተ አበው ...: ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው ክፍል ሁለት ...
በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን ሃይማኖተ አበው እልመስጦግያ ምዕራፍ 3
ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and
Preaching Ministry ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው
ክፍል ሁለት
ጥንተ አንቀጽ መካነ ሕይወት ፈውስነ ሲሳይነ ስቴነ መኮንንነ
ትርጉም ፦ በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን
የሚፈርድልን መጠጣችን ነው
ሃይማኖተ አበው
እልመስጦግያ
ምዕራፍ 3
ኢየሱስም ደግሞ አላቸው እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ
ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም
በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል
የዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 1 _ 15 ፤ 7 _ 10
ይህ የክፍል ሁለት መልዕክት ነው በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ኢየሱስ የበጎች በር በመሆኑ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል በማለት ነግሮናል በመሆኑም እርሱ መንገድና እውነት ሕይወትም ስለሆነ
የዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 እርሱ ሕይወት መሆኑን አውቆ በእርሱ መንገድ ላይ የመጣ ሁሉ እርሱ ወደ እውነትና ወደ ሕይወት የሚወስድ መንገድ ብቻ ሳይሆን የበጎችም በር ነውና በዚህ በር በሆነው በእርሱ በኩል ይገባል ገብቶም አይቀርም ይድናል ይወጣልም መሠማርያም ያገኛል ስንል ዛሬም ይህን የቃሉን እውነት አምኖ በዚህ መንገድ ላይ የመጣ መጥቶም ሳይቀር በዚህ የበጎች በር በኩል ገብቶ በበሩ የገባ መዳኛና መሰማርያም የማግኘት ዕድሉም ለእርሱ እንደሆነ በሰፊው በቃሉ ተማምረናል ክርስቶስ ኢየሱስ የበጎች በር መሆኑን አውቆ በበሩ የገባ የሚድን ነውና የሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንደነገረን እርሱ የሕይወት መገኛ ነው ከዚህ ጌታ ጋር በበሩ በኩል ገብቶ ላልተገናኘ ግን ሕይወት የሚገኝ አይሆንም መዳንም የለም እንግዲህ የሃይማኖተ አበው ጸሐፊ እንዳለው ክርስቶስ ኢየሱስ የበጎች በር መሠማርያ የሚያድን ብቻ ሳይሆን ምግባችን የሚፈርድልን መጠጣችን መሆኑን ይነግረናል ታድያ ወደ ጌታ መጥተን በበሩ ስንገባ የሕይወት መገኛችን ሆኖ የሚያድነን መሠማርያም የሚሰጠን ብቻ ሳይሆን ምግባችን የሚሰጠን እንደ አስፈላጊነቱም የሚፈርድልን ጌታ ነው ስለዚህ ወደ ክርስቶስ የመጣ ክርስቶስ ኢየሱስ ለእርሱ ሁሉ በሁሉ ነው ወደ ጌታ መጥተን እርሱ በር ነውና በበሩ ገብተን ድነንና መሠማርያ አግኝተን የምንቀር ብቻ አይደለንም እንድናድግ የሚያስችለንን መንፈሳዊ መብልንና መንፈሳዊ መጠጥን ከዚሁ ጌታ እናገኛለን በዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 54 _ 58 ላይ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል ጌታችን ኢየሱስ እዚህ ጋር ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል ብሎ ሲናገር በመንፈሳዊ ቃል ሊገልጸው የፈለገው ነገር አለ እርሱም በዚሁ በዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 63 ላይ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው በማለት የሕይወት እንጀራ መንፈስ ያለበት ቃሉ እንደሆነ ይናገረናል ቃሉን ስንበላ እርሱ ሕያው እንደሆነ ሁሉ እኛም ከእርሱ የተነሳ ሕያዋን እንሆናለን ሕያውነት ሁልጊዜ ቃሉን ከመብላት የተነሳ የሚመጣ ነው ኢየሱስ ከሰማይ የወረደ
የሕይወት እንጀራ ሆኖ ቃሉን ሰጥቶናል ራሱንም ሰጥቶናል ስለዚህ ሕያውነታችን እርሱን በመብላትና እርሱን በመጠጣት የበዛ ይሆናል ቃሉን ዕለት ዕለት በግላችን በምናጠናው የመጽሐፍቅዱስ ጥናት በቤተክርስቲያን ባሉን አገልጋዮቻችን በሕብረት ባላ የእርስ በእርስ የመጽሐፍቅዱስ ጥናት እና በመሳሰሉት እንመገባለን ሕያዋንም እንሆናለን ከዚህም ባሻገር በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 23 _ 31 በተጻፈው ቃል መሠረት የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ሕብረት ያለው አይደለምን ? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? አንድ እንጀራ ስለሆነ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና እያለ ይናገራል ይህ የሚያመለክተን የጌታን እራት በምንወስድ ጊዜ የሚሆነውን አንድነትና የበረከት መካፈል ነው የምንባርከው የበረከት ጽዋና የምንቆርሰው እንጀራ ከክርስቶስ ጋር ኅብረትን የሚሰጠን ነው እንደገናም እርስ በእርሳችን ሳይቀር ኅብረታችንንና አንድ ሥጋ መሆናችንን ሳይቀር የሚያሳይ ነው ነገር ግን በዚህ ውስጥ የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ በአንድ ላይ ልናስኬድ አንችልምና ለይተን ልናውቅ እኛም ከጌታ ጋር ብቻ መሆናችንን በማወቅ ኅብረታችንን የጌታን ጽዋና እንጀራውንም በመቁረስ በጽኑ ከእርሱ ጋር ልናረጋግጥ ይገባል ስለዚህ ቃሉን መብላታችን የጌታን ጽዋና እንጀራውንም መቁረሳችን እርሱ አንድ ነውና አንዱን ጽዋ ስንጠጣ አንዱንም እንጀራ ስንቆርስ ከአንዱ ጌታ ጋር ኅብረት ማድረጋችንንና አንድነታችንንም ጭምር የሚገልጽ ሲሆን የእርስ በእርስ አንድነታችንንም ይህ የምንካፈለው ነገር የሚጠብቅልንና የሚያሳየን ነው ምስጢሩ እንግዲህ በአጭሩ ይህንን ሲመስል የቆላስያስ መጽሐፍ ደግሞ ይህንን እውነት ይበልጥ ያጐላዋል ቆላስያስ 2 ፥ 16 _ 20 ላይ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል ይለናል መንፈሳዊ ዕድገትን የሚሰጥም ሆነ የሚያሳድግ እግዚአብሔር ብቻ ነው በበሩ ገብተን መሠማርያ ስናገኝ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር ይሰጡናል መንገድ እና በር ሆኖን በበሩ ያስገባን ኢየሱስ ያዳነን የሚያወጣን የሚያገባን የሚያሰማራን ብቻ ሳይሆን የሕይወት እንጀራ ነውና ቃሉን ሰጥቶ ሕያውነታችንን የሚያበዛ የአካሉ ብልት አድርጎም እርሱ በሚሰጠን ዕድገት የሚያሳድገንም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም አለን 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 6 እና 7 በመሆኑም መንገድና እውነት ሕይወትም ኢየሱስ ነውና የዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 መንገዱን አውቀን የበጐች በር በሆነው በኢየሱስ በኩል በበሩ ስንገባ መሠማራቱ ሕያውነታችንን ማብዛቱ የአካሉ ብልት ሆነንና ተገጥመን እግዚአብሔር በሚሰጠን ዕድገት ማደጉ ሁሉ እኛን የሚጠብቅ ነገር ይሆናል ማለት ነው በመሆኑም እነዚህ ነገሮች በሕይወታችን እንዲጠናቀቁና እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ኤፌሶን 4 ፥ 12 እና 13 መንገድ እውነትና ሕይወት በሆነልን በኢየሱስ በኩል እንመጣ በበሩም በኩል እንግባ ያን ጊዜ የዘረዘርኳቸው እነዚህ ነገሮች በሙሉ በሕይወታችን ይሆናሉ አለበለዚያ ግን መንገድና እውነት ሕይወትም የሆነን እንደገናም ወደ መንግሥቱ መግቢያ በር ሆኖን የሚያድነን የሚያወጣንና የሚያገባን መሠማርያም የሚሆነን የሕይወት እንጀራ የሆነውን ቃሉ አብልቶ ሕያውነታችንን የሚያበዛ አካሉና የአካሉ ብልትም አድርጎ እርሱ በሚሰጠን ማደግ የሚያሳድገን ኢየሱስ እያለልን እንደገና ኢየሱስ ለእኛ እንዳልመጣልን አድርገን እና ጥላ ወደሆነው አገልግሎት ተመልሰን በሰንበት በወር መባቻ በበዓላት ሕይወትና አክብሮት ተይዘን ስንፈርድ ስንፈራረድ በኢየሱስ የተሰጠን አሁን ላይ ያለው የመዳን ቀን ያመልጠናል ሕይወትም ይጨልምብናል ማለት በሚያድነው ጌታ በኢየሱስ ሳንድን እናንቀላፋለን የሥጋን ሞት እንሞታለን ኢየሱስ የሌለው ሰው ደግሞ ሞትን በሥጋ ሞት ብቻ የሚገላገለው ሳይሆን ከሥጋ ሞት ባሻገር ዘላለማዊ ሞት አለና በዚያም ለዘላለም የሚሰቃይበት ነው ስለዚህ ማምለጫው የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 2 ቶሎ ብለን ቀን ሳንሰጥ አሁን ላይ ባለው ሕይወታችን ኢየሱስን መቀበል
ነው ኢየሱስ ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን ጌታዬና አዳኜ ነህ እቀበልሃለሁ ሕይወቴንም ላንተ እሰጣለሁ ስንል መወሰንና መቀበል አለብን ያን ጊዜ ከሞት ወደ ሕይወት እንሻገራለን ከሰይጣን መንግሥት እናመልጣለን የእግዚአብሔርም ልጆች እንሆናለን ስማችንም በሕይወት መዝገብ ይጻፋል እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ወደዚህ ሕይወት እንድንመጣ ይርዳን ይባርከንም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Posts (Atom)