Saturday, 31 October 2015
Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Topic Teaching የትምህርት ርዕስ They must remain fai...
Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Topic Teaching የትምህርት ርዕስ They must remain fai...: ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች እየተዘጋጀ የሚቀርብ ተከታታታይ ትምህርት ነው ...
Topic Teaching የትምህርት ርዕስ They must remain faithful People በእርግጠኝነት የቀሩ ታማኝ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው ትምህርት ስምንት
ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and
Preaching Ministry ሥር በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች እየተዘጋጀ የሚቀርብ ተከታታታይ ትምህርት ነው
Topic Teaching
የትምህርት ርዕስ
They must remain faithful People
በእርግጠኝነት የቀሩ ታማኝ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው
ትምህርት ስምንት
ጌታ እግዚአብሔር አቅርቦትና ዕድል የሰጣቸው ሰዎች በሰጣቸው ጊዜ ጌታን እንዲያገለግሉት ነው ምርጫውም የእነርሱ ነው ( ምርጫውም በቀላሉ የአንድ ቀን ምርጫ ወይም ውሳኔ አይደለም ) በእርግጠኝነት ቃል የሚገቡትና የሚመርጡት እስከመጨረሻው ነው መጽሐፉም
እስከመጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል በማለት ነው የሚነግረን የማቴዎስ ወንጌል 24 ፥ 13 እንደገናም ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ እነዚህ አንድ ሃሳብ አላቸው ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ እነዚህ በጉን ይወጋሉ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ እነርሱን ድል ይነሣል ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ በማለትም የራዕይ መጽሐፍ ይናገረናል ራዕይ 17 ፥ 12 _ 14 ስለዚህ በዚህ ውስጥ የተጠራንና የተመረጥን ሆነን እስከመጨረሻው ለመቅረትም ሆነ ለመጽናት መታመን ለሁላችንም የግድ ይሆናል ይሁን እንጂ ሁላችንም የተጠራነው መታመናችንን ለማረጋገጥ ፣ ፈተናዎቻችንን በትዕግስት ለማሸነፍ ፣ መሰናክሎቻችንንም አልፈን ወደፊት በእምነት ለመቀጠል ፣ ማስረጃዎቻችንም እግዚአብሔርን ለማገልገል ቃል የገባንበት ነው እውነተኛው የተለወጠው የእግዚአብሔር ሕዝብ በመጽሐፉ ቃል መሠረት የተወሰነው ለክርስቶስ አካልነት የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ለመሆን ነው ሐዋርያው በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፥ 27 ላይ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ ይለናል በ1ኛ ጢሞቴዎስ 3 ፥ 15 ላይ ደግሞ ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደርያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ ቤቱም የእውነት አምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነው ይለናል በመሆኑም በመጽሐፉ ቃል በተወሰነው ሃሳብ መሠረት እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለክርስቶስ አካልነት የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ለመሆን የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች የሆንን ብቻ ሳንሆን ቤቱ የእውነት አምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነውና በእግዚአብሔር ማደርያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድናውቅ የተጻፈልን ፣ በዚያው በተጻፈልንም ልክ ልንኖር የተገባንና ወደፊትም የሚገባን ነን ነገር ግን ቤቱ የእግዚአብሔር ቤት ነው በሚል ሰበብ ባልተጻፈልን ነገር መኖር ግን የክርስቶስ የአካሉ ብልት መሆናችንንም ሆነ በእግዚአብሔር ቤት ማደርያ መኖራችንን እንደገናም ማገልገላችንንም ሳይቀር ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል ማገልገልም ሆነ በቤቱ መኖር የጥቂቶች ሳይሆን የብዙዎቻችን ዕጣ ፈንታ ሆኖ ሳለ ሕይወታችን ግን በእነዚህ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች ያልተቃኘና ተፈትኖም ያላለፈ
በመሆኑ ምልልሳችንም ሆነ አገልግሎታችን ከምልልስና ከአገልግሎት አላለፈም ብዙ ሰዎች በአገልግሎት ስም ተቀምጥዋል በቤቱም ለእንደዚህ ያክል ዓመታት ተመላልሰናል እና እኛ የቅርብ ክርስቲያኖች አይደለንም ሲሉ በጌታ ቤት በአገልግሎት ሳይቀር የቆዩ ለመሆናቸው ብዙ ነገሮችን አስረጂ አድርገው አድርገው ሲያቀርቡና ሲናገሩ ይስተዋላሉ እኛም የምንለው ትክክለኛ መሆናቸውን በመንገር እውነት ብላችኋል ልክ ናችሁ በማለት ነው መልስ የምንሰጣቸው እነዚህ ሰዎች ግን እንደተናገሩት ለዓመታት በቤቱ ተመላልሰዋል በአገልግሎት ሳይቀር በቤቱ የቆዩ ናቸው ብቻ ሳይሆን እንደውም
የአንድ አገልግሎት ክፍል ሃላፊዎችና
የቤቱም መሪዎች ናቸው ብንል የተሳሳትን አንሆንም ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸው ከዚህ ከተነገረው ቃል ጋራ እንደሚገባ የተገናኘ
ባለመሆኑ እነዚህ የተባሉት ነገሮች እና እነርሱም ለዓመታት እንዲህና እንዲያ የሆንን ነበርን አሁንም ነን ሲሉ የዘረዘሯቸው ሁሉ ዋጋን የማያሰጡአቸው አይሆኑም
በቤቱ መመላለስና ማገልገል
ሃላፊነትን ተረክቦም ቤቱን መምራትና ማስተዳደር መልካምና ክፋት የሌለው ቢሆንም በእነዚህ በጠቀስኳቸው ሁለት ቃሎች ሕይወት
የተቃኘ ካልሆነ ግን ሁሉም ነገር ዋጋ ቢስና በነበረ የሚቀር ነው ይልቁንም ዛሬ ከዚህ በተለየ መልኩ የብዙ ሰው ትግልና ትንቅንቁ ያለው አገልግሎት ላይ ነው አብዛኛው ሕዝባችን ጌታን ቢያገለግል ፣ ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች ቢከፍት ሃላፊ መሪ እረኛ አስተዳዳሪ ቢባል አይጠላም
ጌታን ማገልገል ፣ ቤተክርስቲያን መክፈትና አገልጋይ ፣ መሪ ፣ እረኛ እና የመሣሠሉትን መባል ጌታን ለማስከበር እና ለጌታም የሆነውን ክብርን ለማምጣት ከሆነ እሰየው ግን በአብዛኛው አይደለም እንደገናም ቤተክርስቲያን የከፈተውም ሆነ በተከፈተው ቤተክርስቲያን በሃላፊነት የተቀመጠው በትክክል አገልጋይ
፣ እረኛም ሆነ ሃላፊ ለመሆኑና ላለመሆኑ እንኳ በራሱ ሳይቀር ራሱን ተጠራጣሪ ፣ ወንድሙንም ጠርጣሪ የሆነ ነውና እርግጠኛ ባልሆነበት አገልግሎት እረኝነትም
ሆነ መሪነት ውስጥ ገብቶና ተቀምጦ ቤተክርስቲያን ባለቤት ያላት ባለቤቷም ክርስቶስ መሆኑን እያወቀ
ያራሱ ኪዮስክና የሸቀጥ ሱቅ አድርጎ በመቁጠር በግል ፍላጎትና ጥቅም ተይዞ ከእኔ
ወዲያ እረኛ ፣ አስተዳዳሪና መሪ ለአሳር እያለ ይገኛል እንደውም በአብዛኛው
ማለት ይቻላል የምንጣላውና የምንጠላላው በነዚህ ጉዳዮች ነው የሕይወት ነገር ገብቶን የአካሉ ብልት መሆናችን ግድ ብሎን ይሄ ብልት ተሰቃየ ያ ብልት ደግሞ ተጎዳ
ብለን፣ ቤቱንም በተመለከተ ቤቱን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ከማሰብ ተነስተን ቤቱ የእውነት አምድና መሠረት የሕያው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነው ስንል የምንቆረቆርና የምንጋጭ ግድም የሚለን አይደለንም
በአጠቃላይ ነገራችን ሁሉ እንደቃሉ ባለመሆኑ በጊዜያዊ ጥቅሞች ተይዘን የምንራኮትና የምንሯሯጥ ነንና የሚያጋጩንን ጉዳዮች ሰዎች በቀላሉ ለመረዳት የቻሉ በመሆናቸው ትዝብት ላይ ወድቀናል ጌታ በብዙ ይድረስልን እውነተኛ ደቀመዛሙርት እነማን ናቸው ?ሲል እግዚአብሔር መግለጫ ሰጥቶአል የመጽሐፉን ትምህርት ለመረዳት ፍጹም የሆነ የተከፈተ አዕምሮ አግኝተው በመጀመርያ ለንስሐ የተጠሩ ናቸው በምርጫቸው ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ፈቃድ አስገዝተው ምላሽ ሲሰጡ የእርሱ መንፈስ በልባቸው ውስጥ ታምቆ ያለውን ክፉ ባሕርይ በመለወጥና በመግራት ወደ ትክክለኛው የራሱ ሃሳብ መምራት ይጀምራል ለደኅንነትም ይመርጣቸዋል የእርሱ የዘላለም መንግሥቱ ክፍል ለመሆን ለእርሱ በእውነት የተጠራን በታማኝነትና በእርሱ ምርጫ ለእርሱ የምንታዘዝ ነን መጠራታችንንና መመረጣችንንም በታማኝነት እስከ ፍጻሜ እንድናጸና ጌታ እግዚአብሔር ሁላችንንም ይርዳን አሜን
በመቀጠልም የተወዳጁ ዘማሪ ወንድማችን ተስፋዬ ጫላ አገለግልሃለሁ የሚለውን መዝሙር በመጋበዝ እሰናበታችኋለሁ ተባረኩ
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Posts (Atom)