Monday, 7 September 2015

እውነተኛ የጌታ ተከታይ ማነው ? Who are God`s True Followers? ክፍል ሁለት

እውነተኛ የጌታ ተከታይ ማነው ?


Who are God`s True Followers?


ክፍል ሁለት


እነዚህ በጉን ይወጋሉ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ እነርሱን
ድል ይነሣል ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑ ደግሞ ድል ይነሳሉ

ራዕይ 17 14




እነዚህ በጉን የሚወጉ ቢሆንም በጉ ግን የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ እነርሱን ድል ይነሣል በመሆኑም ይህ የሚያሳየን እንግዲህ የበጉን ሉዓላዊነት እና ሁሉን ቻይነት በአጽንዖት የሚገልጽ መሆኑን ነው በዘዳግም 10 17 ላይ እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም በፍርድ የማያደላ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ ይለናል በትንቢተ ዳንኤል 2 47 ላይ ደግሞ ንጉሡም ዳንኤልን ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት የነገሥታትም ጌታ ምሥጢርም ገላጭ ነው ብሎ ተናገረው ይለናል በ1ኛ ጢሞቴዎስ 6 15 ላይ ደግሞ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዢ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል እርሱ ብቻውን የማይሞት ነው ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያየውም አይቻለውም ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን አሜን ይለናል ስለዚህ ጌታችን እንደዚህ ዓይነት ጌታ ስለሆነ ሉዓላዊና አሸናፊ ጌታ  ሁሉን ቻይ የሆነም ጌታ ነው ከዚህም ሌላ በራዕይ መጽሐፍ ላይ አስደናቂ የሆነ ቃል እናገኛለን እርሱም እንዲህ ይላል ሰማይ ተከፍቶ አየሁ እነሆም አምባ ላይ ፈረስ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል ስሙም የእግዚአብሔር ቃል በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቅያ ይረግጣል በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው ይለናል ራዕይ 19 11 _ 16 ታድያ ከዚህ ድል ነሺ ጌታ የተነሳ የእኛም ሕይወት በድል የተሞላ ነው  ምክንያቱም ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ ይለናልና ስለዚህ እውነተኛ የጌታ ተከታዮች የተጠሩ የተመረጡ የታመኑ ተብለው የተጠሩ ብቻ ሳይሆኑ እነርሱም የዚህ ጌታ ነገር ገብቶአቸው መጠራታቸውን ያጸኑ ይህንኑ ጌታ የመረጡና በታማኝነትም ከእርሱ ጋር ያሉ ናቸው ጌታ እግዚአብሔር የእያንዳንዳችንን እድል ፈንታ እንደዚህ ያድርገው መጽሐፍ ሲናገር በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 7 21 ላይ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም ይለናል አያይዞም በዚሁ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 7 23 ላይ ደግሞ የዚያን ጊዜም ከቶ አላውቃችሁም እናንተ አመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ ይለናል ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ነው እርሱ ተነስቶአል በዓለምም ላይ ተጽዕኖን አምጥቷል አብዛኛው ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ቤተሰብ ነው ነገር ግን ምን ያህሉ ያውቀዋል ? እርሱ ያስተማረውና የእርሱ ተልዕኮ ምን ነበር ? የእርሱስ እውነተኛ ተከታዮች ልዩነታቸው ምንድርነው ?ማንስ ነው እርሱን በትክክል የሚወክል?  መጽሐፍቅዱሳችን በማቴዎስ ወንጌል 22 14 ላይ የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና ይለናል በዮሐንስ ወንጌል 16 33 ላይ ደግሞ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬያችኋለሁ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ይለናል   ስለዚህ ከተጠሩት ብቻ ሳይሆን ከተመረጡት ወገን ሆነን በዓለም ሳለን መከራ ቢሆንብንም ክርስቶስ ግን ዓለምን አሸንፎታልና በዚህ ደስ ይበለን ዋናው ነገር በክርስቶስ ሳለን ሰላም እንዲሆንልን ጌታ ተናግሮናል ኢየሱስ ቤተክርስቲያኔን እገነባለሁ አለ የማቴዎስ ወንጌል 16 18 የግሪኩ ቃል ቤተክርስቲያንን ሲተረጉመው ኤክሌሽያ ይለዋል ትርጉሙም  Assembly ማለት ሲሆን ስብሰባ መሰብሰብ ማለትን ያመለክታል በትክክልና በግልጥ ሲነገር ደግሞ " A calling out "or " called out ones " ተጠርቶ የወጣ ወይንም አንድ ጊዜ ተጠርቶ የወጣ ማለትን የሚያመለክት ነው The meaning of the word Akklesia is " from ek " out of " and klesis a calling (kaleo, "to call ")ማለት ነው  በሐዋርያት ሥራ 19 39 ላይ Assembly ወይንም ስብሰባ የሚለውን ቃል ሲተረጉመው ስለሌላ ነገር እንደሆነ ግን አንዳች ብትፈልጉ በተደነገገው ጉባኤ ይፈታል ይለናል የሐዋርያት ሥራ 19 39 የዕብራውያን መጽሐፍ የአማኞችን አካልነት የበኩራት ማኅበርና የቤተክርስቲያን ጠቅላላ ስብሰባ ይለዋል ዕብራውያን 12 23 ከዚህ የተነሳ ቤተክርስቲያን የሕያው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእውነት ዓምድና መሠረት የሆነች ቤተክርስቲያን ናት 1 ጢሞቴዎስ 3 15 Paul describes it as " The Church of the living God the Pillar and ground of the truth "



ጌታ እግዚአብሔር የምናነበውን ቃል ይባርክልን


Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry
አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ተባረኩልኝ ለዘላለም



No comments:

Post a Comment