Monday 27 April 2015

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Seeking Guidance የሚመራ መፈለግ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ት...

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Seeking Guidance የሚመራ መፈለግ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ት...: Seeking Guidance  የሚመራ መፈለግ  በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ ክፍል ስድስት የእግዚአብሔ...

Seeking Guidance የሚመራ መፈለግ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ ክፍል ስድስት






Seeking Guidance 



የሚመራ መፈለግ 



በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ


ክፍል ስድስት


የእግዚአብሔር ቃል በመዝሙር 34 8 ላይ እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ  እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው አለ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለመቅመስ የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ አማራጭ የሌለው ነገር ነው በ1ኛ ዮሐንስ 3 22 ላይ የእግዚአብሔር ቃል የሚለን እንደዚህ ነው ወዳጆች ሆይ ልባችን ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን ይለናል በመሆኑም እንግዲህ ለቃሉ በመታዘዝ ውስጥ የሚፈለገው ነገር ሁሉ ከተገኘ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች እንዳሉን በዚሁ በተገለጠው በእግዚአብሔር ቃል መረዳት እንችላለን በትንቢተ ሚልክያስ 3 10 ላይም በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ  በዚህ ፈትኑኝ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይለናል እኛ ጌታ በሚያዘን ነገር ሁሉ ታማኞች ሆነን ለቃሉ ከታዘዝን እግዚአብሔር በረከቱን ሁሉ ሊያፈስልን የታመነ ነው ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስም እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸው መጣሁ ያለው ዮሐንስ ወንጌል 10 10 የሚበዛ ሕይወት ቃሉን ከመታዘዝ የተነሳ በእግዚአብሔር በረከት የተጎበኘና የተጥለቀለቀ ሕይወት ነው ስለዚህም በመዝሙር 111 10 ላይ የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ለሚያደርጓትም ደኅና ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል ይለናልና እግዚአብሔርን ፈርተን የእግዚአብሔርን ቃል በማስተዋል ብናደርግ ማለት ብንታዘዝ  በረከታችንም ሆነ ማስተዋላችን በዚያው ልክ እየጨመረ ይመጣል ጌታ እግዚአብሔር በዚህ በረከት ይባርከን ከዚህ በመቀጠል ከዚሁ ጋር የተያያዘ ጥቂት ሃሳቦችን በእንግሊዝኛ ለማቅረብ እወዳለሁ ይህን የማደርገው ሃሳቡን ይበልጥ ስለሚደግፍልኝና የተሻለ ማብራርያ ስለሚሰጠው ነው 
                  
Obey God's Word AND Prove it right


Put God's word to the test by practicing the things you are learning Acknowledge how his ways bring positive change in your life. The best way to determine that God's commands and teachings bring true peace and blessings is by living them.

God bless all People of God 

God  servant Preacher and Teacher Yonas Asfaw

Sunday 12 April 2015

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: ሀ _ የቃሉ ተማሪ መሆን ...

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: ሀ _ የቃሉ ተማሪ መሆን ...: የሚመራ መፈለግ     Seeking Guidance       ሀ   _   የቃሉ ተማሪ መሆን       Become a studen...

ሀ _ የቃሉ ተማሪ መሆን Become a student of the word Take not ክፍል አራት


የሚመራ መፈለግ

 

 

Seeking Guidance

 

 

 

  _  የቃሉ ተማሪ መሆን

 

 

 

Become a student of the word

 

 

 

Take not

 

 

 

ክፍል አራት

 

 

 

እግዚአብሔር የቃሉ ተማሪ እንድንሆንለት ይፈልጋል በዘጸአት 4 12 ላይ እንግዲህ አሁን ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ አለው ይለናል በመጽሐፈ ኢዮብ 33 33 ላይ ደግሞ ያለዚያም እኔን ስማ ዝም በል፥ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ በመዝሙረ ዳዊት 32 8 ላይም አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ ይለናል ጌታ እግዚአብሔር ሊያስተምረን ሲፈልግና ሲያስተምረን ማድረግ የሚገባን ነገር በቅድሚያ ዝም ማለት ነው እንደገናም እርሱን መስማት ነው ያንጊዜ ከዚሁ ጌታ ጥበብን መማር ይሆንልናል ይህ በሚሆንበት ጊዜ በምንሄድበት መንገድ ሁሉ ይመራናል ዓይኖቹንም በእኛ ላይ ያጸናል ይህ ካልሆነ ግን ማለት እርሱ ሊያስተምረን ሲፈልግ እኛም ከእርሱ ልንማር ስንል  ዝም ማለት ካልቻልንና እርሱንም ለመስማት ካልወደድን ፍጹም የምንማረው ነገር አይኖርም እርሱም ዓይኖቹን በእኛ ላይ አያጸናም ማለት እንደ መልካም ተማሪም ሊከታተለን አይወድም ለዚህ ነው ዘማሪ ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ ማለዳ እየመጣህ ስታነቃኝ ጆሮዬን ከፍተህ ስትናገረኝ በማስተዋል መንገድ ስትመራኝ ከሕይወት ምንጭ ውሃ ስታረካኝ ለምልሞ ነበር ሕይወቴ እንዲህ አልዛለም ጉልበቴ እባክህ አስበኝ አንተ ነህ መድኃኒቴ መቼ ነው ነቅቼ ድምጽህን የምሰማው ለነፍሴ መጎብኘት መጽናናት የሚመጣው በሌሊት ስነሳ ከእንቅልፌ ስምህ ነው የሚመጣው ፈጥኖ በአፌ ሕመሜን ለአንተ እናገራለሁ ድምጽህን አሰማኝ እማራለሁ ጌታ ሆይ መቃተቴን ስማ ነፍሴ እንደዚህ ተዳክማ እንደምን ትዘልቃለች ትካዜን ተሸክማ እያለ ይህን አስደናቂ መዝሙር የዘመረልን ሙሉውን ስንኝ እናንተ ፈልጋችሁ በማግኘት ዘምሩት መዘመር ብቻም አይደለም ተማሩበት ለሌሎችም አስተምሩት ዘማሪውና መጋቢው እንደዘመረልን አንዳንድ የምናልፍባቸው የማይመቹ የሚመስሉ የሕመም መንገዶች ፈቅደን ሳይሆን ሳንፈቅድና ግድም ሆኖብን ድምጹን ወደ መስማት የምንመጣበት ብሎም የምንማርበት መንገዶች ናቸው  ከጌታ ለመማር በማንፈቅድበትና የመማርያ ጊዜም ሙሉ በሙሉ  በምናጣበት ሰዓት እነዚህ ነገሮች የግድ በሕይወታችን ይሆናሉ  በሆሴዕ መጽሐፍ ላይ ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ ይለናል ትንቢተ ሆሴዕ 2 16 ያን ጊዜ ነው እንግዲህ ለነፍሳችን መጎብኘትና መጽናናት የሚመጣው ከዚያ ውጪ ግን መጽናናት የሚባል ነገር ከቶ የማይታሰብ ነውና ብንፈልግም  አናገኝም በዚህ አጋጣሚ እንግዲህ ስለዚህ የተባረከው አስተማሪ ስለሆነው መዝሙሩ ወንድማችንን ጌታ አብዝቶ ይባርከው ለማለት እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር ጆሮ ከፍቶ እንደሚናገር በትንቢተ ኢሳይያስ 50 4 _ 9 መመልከት እንችላለን እንግዲህ የቃሉ ተማሪ በምንሆንበት ጊዜ በመጀመርያ ማድረግ የሚገባን ማስታወሻ መውሰድ ነው ይህ የሚረዳው ቁልፍ ሃሳቦችን ፣ ተገናኝ የሆኑ ጽሑፎችን ለማስታወስ ነው  አንዳንድ ሰዎች በቁልፍ ሃሳቦች ላይ ማስመርን ይጠቀማሉ ይህም የሚረዳው ዋና ዋና ሃሳቦችን ይበልጥ ለመረዳት ነው በመሆኑም በማንኛውም የክፍል ትምህርት ሙሉ እርዳታን ይሰጣል ማስታወሻ በምንወስድበት ጊዜ በቂ መረጃን እናገኝበታለን በእንዲህ ዓይነት መንገድ የእግዚአብሔርን የቃሉን እውነት በምንከታተልበት ጊዜ እውነተኛ የሆነ የደቀ መዝሙር ሕይወት እንይዛለን በማቴዎስ ወንጌል 28 19 _ 20 ላይ መጽሐፍቅዱሳችን እንዲህ በማለት ይናገራል እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ እንግዲህ ሰዎችን እያጠመቅን ጌታ ያዘዘንንም ሁሉ  እንዲጠብቁ እያስተማርን ደቀመዛሙርት ስናደርግ እንዲሁ ሊሆን አይገባን የተማሩትን በትክክል እንዲይዙ የማስታወሻ ደብተር እንዲኖራቸውና ማስታወሻም እንዲጽፉ ልናደርጋቸው ይገባል ይህን ስናደርግ ነው እንግዲህ ሰዎችን የተማሩትን የሚጠብቁ እውነተኛ የጌታ ደቀመዛሙርት የምናደርጋቸው የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብና ለማጥናት ኃይልን አጠናክሮ ትልቅ ጥረት ማድረግ መጽሐፍቅዱስ የሚነግረንና የሚደግፈው አጠቃላይ የሕይወታችን መመርያ ነው ታድያ ይህንን መመርያ በሕይወታችን የምንተረጉም የተማርነውንም በማስታወሻ ደብተራችን ለመጻፍ ለማጥናት ለማሰላሰል ሰፊ ጊዜ የምንሰጥ እና ማስታወሻ ደብተሩም ያለን ስንሆን ነው ታድያ ይህን የምናደርግ ስንቶች እንሆን ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢዎች እተዋለሁ በመጽሐፈ መክብብ 9 10 ላይ አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ ይለናል ስለዚህ ማወቅም ሆነ ጥበብ ማግኘት ካለብን እጃችንም ለማድረግ የምናገኘውን ሁሉ እንደ ኃይላችን ማድረግ የምንችለው አሁን ነው

 

With the right approach strive to become a dedicated student of the word of God it is a matter of applying what you learn

 

ጌታ ይባርካችሁ

 

 


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ