Sunday 25 January 2015

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምዕራፍ ሁለት ክፍል አስራ አንድ ...

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምዕራፍ ሁለት ክፍል አስራ አንድ ...: የቤተክርስቲያን ተልዕኮ       ምዕራፍ ሁለት       ክፍል አስራ አንድ       እግዚአብሔርን አለማወቅ ...

የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምዕራፍ ሁለት ክፍል አስራ አንድ እግዚአብሔርን አለማወቅ


የቤተክርስቲያን ተልዕኮ

 

 

 

ምዕራፍ ሁለት

 

 

 

ክፍል አስራ አንድ

 

 

 

እግዚአብሔርን አለማወቅ

 

 

እግዚአብሔርን አለማወቅ ከብዙ ነገር ጋር ይያያዛል ከካህናት ከባለ ኦሪቶች ከገዢዎች ከነቢያት ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ ካለው ሕዝብ ጋር ይያያዛል ለዚህ ነው መጽሐፍቅዱሳችንም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ይህንን እውነታ በሰፊው የሚነግረን በትንቢተ ኤርምያስ 2 8 ላይ ካህናቱም እግዚአብሔር ወዴት አለ ? አላሉም ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ገዢዎችም አመጹብኝ ነቢያትም በበዓል ትንቢት ተናገሩ የማይረባንም ነገር ተከተሉ ይለናል ይህ የሚያሳየን እንግዲህ በጥቅሉ የሁሉም እግዚአብሔርን ያለማወቅ ሁኔታን ነው በትንቢተ ኤርምያስ 5 30 _ 31 ላይም የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ትሆናለች ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወዳሉ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ ? ይለናል አንዱ ከሌላው ይልቅ የተሻለ ነገር ኖሮትና የተሻለ ነገር ይዞ ሌላውን መመለስ ማቃናትና ማስተካከል ካልቻለ እንደገናም ሁሉም ያው ዓይነት ሕይወትና ያው ዓይነት መረዳት ካለው ጸሐፊው በፍጻሜው ምን ታደርጋላችሁ ? ሲል በጥያቄ ምልክት እንዳስቀመጠልን ዛሬም ቢሆን በዘመናችን በዚህ ጉዳይ ላይ የምናደርገው ነገር የለም ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ በእርሱ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ሲያይ አንድ ዓይነት እና ተመሣሣይ የሆነ ሕይወት የተመለከተ በመሆኑ ተዉአቸው ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ በማለት የተናገረው የማቴዎስ ወንጌል 15 14 እንዲህ ማለቱ ከዕውርነት ወይም ካለማየት የተነሳ አንዱ አንዱን መምራት ስለማይችል አንዱ ሌላውን መታደግ አይችልም ለማለት ነው አንድ ዓይነት ሕይወት ያላቸውን ሰዎች መለየትና አንዱ ከሌላው ይሻላል ብሎ መገመትም ሆነ አስተያየት መስጠት በጣም ያዳግታል አያይዞም ሰው በመጀመርያ ሲያይ ራሱን ነውና የሚያየው ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ጉዳይ ላይ በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ ? በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለምን አትመለከትም ? ወይም ወንድምህን ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ ? እነሆም በዓይንህ ምሰሶ አለ አንተ ግብዝ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ በማለት ሲናገር እንመለከታለን የማቴዎስ ወንጌል 7 3 _ 5 ሐዋርያው ጳውሎስም ከዚህ ሃሳብ ጋር ተመሣሣይነት ያለው ሃሳብ በመግለጽ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን ? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሠርቃለህን ? አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን ? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተመቅደስን ትዘርፋለህን ? በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን ? በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና በማለት ጽፎልናል ሮሜ 2 17 _ 24 እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ የሚረዱን እውነተኛ አስተማሪዎችና እውነተኛ ካህናት ናቸው ለዚህም ነው እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ ያለ አስተማሪም ካህን ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር ካለን በኋላ በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረም በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ነበረ እግዚአብሔር በመከራ ሁሉ ያስጨንቃቸው ነበርና ወገን ከወገን ጋር ከተማም ከከተማ ጋር ይዋጋ ነበር የሚለን 2ኛ ዜና 15 3 _ 7 ዛሬም ታድያ ይሄ ሁኔታ በይበልጥ  በቤተክርስቲያን  ብሶና ከፍቶ አንዱን ከሌላው እያነካከሰ ሰላም አሳጥቶ ድንጋጤም ፈጥሮ ያለው ነገር እውነተኛውን እግዚአብሔርን ከአለማወቅ እና እውነተኛ አስተማሪ  ካህንም ከመጥፋቱ የተነሣ ነው በትንቢተ ኤርምያስ 50 6 እና 7 ላይ ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል እረኞቻቸው አሳቱአቸው በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉዋቸው ከተራራ ወደ ኮረብታ አለፉ በረታቸውንም ረሱ የሚለን ከዚህ የተነሳ ነው ዛሬም በእኛ ዘመን ስናይ ብዙ በጌታ ስም በየመንደሩ ሳይቀር የተከፈቱ ቤተክርስቲያኖች አሉ ብዙ እረኞች ብዙ ነቢያት እና የመሣሠሉት አገልጋዮች ስመ ጥር ሆነውና ቦታውን ይዘው ተቀምጠዋል ነገር ግን አሁንም በኤርምያስ ዘመን እንደነበረው ዓይነት የእግዚአብሔር ሕዝቦች የጠፉ በጎች ሆነዋል በተራሮችም ተቅበዝብዘዋል በረታቸውንም ረስተዋል ይህ ታድያ በአገልግሎት ስም የሆነና እየተሠራ ነው እየተባለ ነገር ግን ሳይሠራ የቀረ እንሸፍነው ብንል እንኳ ልንሸፍነው የማንችል የአደባባይ ምስጢር  ሆኗል  በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ጌታ እግዚአብሔር እውነተኛ የሆነውን ፈውስ እንዲያመጣ የሁላችንም ጸሎት ሊሆን ይገባል እንደውም ይህንን ሁኔታ አስተውለን ስንመለከተው ሕዝባችን በእግዚአብሔር እውቀት ልህቀት ከተገነባበት ማንነቱ ይልቅ ድካሙ ጎልቶ እየታየ ያለ በመሆኑ በትንቢተ ኤርምያስ 6 13 _ 14 በትንቢተ ኤርምያስ 8 10 _ 11 ላይ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ ሰላም ሳይሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን ? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር ይልና በትንቢተ ኤርምያስ 8 ላይ የተጻፈውም ሃሳብ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ይገልጸዋል ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ በማለት ይናገራል ይህንን የነቢዩን ሃሳብ ስንመለከት እንግዲህ እግዚአብሔር የተናገረው በመሆኑ ከአገልግሎቱ ይልቅ ውጤቱ እጅግ አስፈሪ ነው ስለዚህ ታዲያ ምን ይደረግ ? እንግዲህ ተሰጥቶኛል በቃ የእኔ ነው አገለግላለሁ ደግሞም እያገለገልኩ ነው ስለምንለው አገልግሎት ከሁሉ በፊት  እንዲህ ከምንል ይልቅ በብዙ ልናስብበት ልንጸልይ ልንመክርበት ማስተካከልና መስተካከል ካለብንም ፈጥነን ልናስተካክልና ልንስተካከል እንደሚገባ ከክፍሉ አስተውላለሁ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በሕይወታችን እና በኑሮአችን ሁሉ ብዙ ሰላም ይሆናል እግዚአብሔር ደግሞ በሕይወት ጉዞአችን ባለ ነገር ሁሉ ማዳኑን ያሳየናል ረጅሙንም ዕድሜ ያጠግበናል ተባረኩልኝ ቅዱሳን የምናነበውን እንድናስተውለው እንድንጠቀምበትም ጌታ ይርዳን

 

የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን፥ ሰይፉንም ከደም የሚከለክል ርጉም ይሁን  

                 ትንቢተ ኤርምያስ 48 : 10

 

 

ከፊቴም ከጣልሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም

                        2 ሳሙኤል 7 15

                   

 

               ወንድማችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ